የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር የምዕራብ ሪጅን ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት በሥሩ ለሚገኙ ቅ/ጽ/ቤቶችና ለመስክ ጽ/ቤቶች የጽሕፈት መሳሪያ የቢሮ ቋሚ ዕቃዎች የጽዳት ዕቃዎች ደንብ ልብስ ቋሚ አላቂ ዕቃዎች የሥልጠና መስተንግዶ የህትመት ሥራ የመኪና እና የሞተር ሳይክል ጎማና ካለመዳር ግዥ የማሽነሪ ጥገና የአጥር እና የቤት ጥገና እጅ ዋጋ የደንብ ልብስ ስፌት እጅ ዋጋ የጭነት አገልግ
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ-ቁጥር 01/2019
የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር የምዕራብ ሪጅን ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት በሥሩ ለሚገኙ ቅ/ጽ/ቤቶችና ለመስክ ጽ/ቤቶች የጽሕፈት መሳሪያ የቢሮ ቋሚ ዕቃዎች የጽዳት ዕቃዎች ደንብ ልብስ ቋሚ አላቂ ዕቃዎች የሥልጠና መስተንግዶ የህትመት ሥራ የመኪና እና የሞተር ሳይክል ጎማና ካለመዳር ግዥ የማሽነሪ ጥገና የአጥር እና የቤት ጥገና እጅ ዋጋ የደንብ ልብስ ስፌት እጅ ዋጋ የጭነት አገልግሎት የተሽከርካሪ እና ሞተር ሳይክል ጥገና የእጅ ዋጋ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማግባት ይፈልጋል።
1. በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ በአገር ውስጥ ገቢ የድጋፍ ደብዳቤ የአቅራቢዎች የምዝገባ የምስክር ወረቀት እና የቫት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ እንዲሁም ለጨረታ ማስከበሪያ ከተ.ቁ 7, 10 እና 12 በስተቀር ለእያንዳንዱ ብር 3,000.00 (ሦስት ሺህ) በሰርቲፋይድ ቼክ (CPO) ለማስያዝ የሚችሉ ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ ለእያንዳንዱ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ) በመክፈል ከቢሮ ቁጥር 7(ሰባት) በመውሰድ ማስታወቂያዉ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ እስከ 11፡00 ሰዓት የጨረታ ሠነድ ዋጋቸዉን በታሸገ ኤንቨሎፕ በሁለት ኮፒ በማሸግ በተዘጋጀው ሣጥን ዉስጥ ማስገባት ይችላሉ።
2. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በ11ኛው ቀን ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በ8፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡ 11ኛው ቀን ቅዳሜ እሁድ ወይም በዓል ከሆነ በቀጣዩ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ ይከፈታል።
3. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት በጽዳት ዕቃዎች፣ በጽሕፈት መሳሪያዎች፣ በቋሚ አላቂ ዕቃዎች እና በደንብ ልብስ ናሙና ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን በቋሚ የቢሮ ዕቃዎች ላይ የዕቃውን ናሙና በፎቶ ግራፍ ማቅረብ አለባቸው።
4. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ያለመገኘት የጨረታውን ሂደት አያስተጓጎልም።
5. ተጫራቾች ባሸነፉት የዕቃ ዋጋ ለዉል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ የሚችሉ መሆን አለባቸዉ።
6. መ/ቤቱ የተሻለ የአሰራር ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ምስራቅ ወለጋ ዞን ፖሊስ መመሪያ ፊት ለፊት የዱሮ ወገን ሆቴል አጠገብ ነው።
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 0576612054/0576615178
የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ምዕራብ ሪጅን
