የጨረታ መለያ ቁጥር 01/2019 ዓ.ም የመንግስት ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር የደቡብ ሪጅን ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር 01/2019 ዓ.ም የመንግስት ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር የደቡብ ሪጅን ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የግዥው ዓይነት
ሎት 1. ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች
ሎት 2. የጽህፈት መሣሪያዎች
ሎት 3. ሌሎች አላቂ የፅዳት ዕቃዎች
ሎት 4 የደንብ ልብስ
ሎት 5. የተሽከርካሪ ጎማና መለዋወጫዎች
ሎት 6. ሌሎች አላቂ ዕቃዎች
ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለፀው መሰረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።
በስራው ዘርፍ ቀጥተኛ እና ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉና
የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያላቸው።
ተጫራቾች የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
ተጫራቾች የአቅራቢነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡ ተጫራቾች የግብር ክሊራንስ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
ተጫራቾች በሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውንና ሙሉ አድራሻቸውን በመሙላት በማህተም ማረጋገጥ አለባቸው።
ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከሪጅን ጽ/ቤት በማይመለስ ብር 200.00(ሁለት መቶ ብር ብቻ) በመግዛት መውሰድ ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሎት የጨረታ ማስከበሪያ የሚመለስ ብር 5,000.00(አምስት ሺህ ብር) በሲፒኦ (cpo) ብቻ ማስያዝ አለባቸው ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ከቫት ጋር መሆን ወይም አለመሆኑን መግለጽ ይኖርባቸዋል፡፡ካልተገለጸ ግን ቫትን እንዳካተተ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡ ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በመሙላት ኮፒ እና ኦርጂናል በማድረግ በታሸገ ኤንቨሎፕ/ፖስታ/ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት አንስቶ እስከ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት እስከ 11፡00 ሰዓት ሀዋሳ ከተማ በሚገኘው የመንግስት ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር የደቡብ ሪጅን ጽ/ቤት በተገለፀው ቀን ለዚሁ ጨረታ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ በሚገለፀው መሰረት ናሙና እንዲቀርብ በተጠየቁት ዕቃዎች ላይ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
ጨረታው የሚከፈተው ጨረታው በጋዜጣ ላይ በወጣ በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 04፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዛው ዕለት ከጠዋቱ 05፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
ሪጅን ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ሀዋሳ ቤተሰብ መምሪያ አጠገብ
ስልክ 046-221-43-17/046-221-41-40/046-221-79-18
የመንግስት ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር
የደቡብ ሪጅን ጽ/ቤት
