Tender Detail

Tender Details


የሀላባ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለሀላባ ዞን ትምህርት መምሪያ ለ2019 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች 1-8 ኛ ከፍል የተማሪዎች መጽሀፍት የህትመት ግዥ በጨረታ አወዳድሮ ማሳተም ይፈልጋል።


የጨረታ ማስታወቂያ

 

የሀላባ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለሀላባ ዞን ትምህርት መምሪያ 2019 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች 1-8 ከፍል የተማሪዎች መጽሀፍት የህትመት ግዥ በጨረታ አወዳድሮ ማሳተም ይፈልጋል።

በዚሁ መሰረት ተጫራቾች አግባብነት ያለው በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ የንግድ ምዝገባ የምስከር ወረቀት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር(Tin) ሰርተፊኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለበትን ማስረጃ (ታክስ ከሊራንስ) ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ እንዲሁም በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር የአቅራቢዎች ዝርዝርውስጥ መመዝገብ ይኖርባቸዋል። እንዲሁም ተጨማሪ መቅረብ ያለባቸው ሰነዶች በጨረታ ሰነዱ በተገለፀው መሠረት ይሆናል፡፡

1. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት 15 ተከታታይ የስራ ቀን ውስጥ የጨረታ ሰነዱን እያንዳንዱን በብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በመግዛት መውሰደ

2. ጨረታው 16 ተኛ ቀን የጨረታው ሳጥን 400 ሰዓት ታሽጎ 430 ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል ሆኖም ግን በመክፈቻው ቀን የተጫራቾች ያለመገኘት መምሪያው ጨረታውን ከመክፈት የሚያስተጓጉለው ነገርአይኖርም።

3. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ብር10,000 /አስር ሺህ ብር/ በባንከ ዋስትና በታወቀ ባንክ የተረጋገጠ የከፍያ ማዘዣ (CPO) ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርበታል፡፡

4. የጨረታው አሸናፊ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ 10% የውል ማስከበሪያ (CPO) ወይንም አንኮንዲሽናል ባንከ ጋራንት ማስያዝ ይኖርበታል፡፡

5. የጨረታው መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ጨረታው የሚከፈት ይሆናል።

6. መምሪያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው::

 

የሀላባ ዞን ፋይናንስ መምሪያ

Save Tender