የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የጉምሩክ ህግን ተላልፈው የተያዙ የተለያዩ የኮንትሮባንድ እቃዎችን በቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት 06/12/2018 እና 09/12/2018 በግልጽና በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የጉምሩክ ህግን ተላልፈው የተያዙ የተለያዩ የኮንትሮባንድ እቃዎችን በቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት 06/12/2018 እና 09/12/2018 በግልጽና በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቶች የጨረታ ሰነዱን በእዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በአካል በመገኘት በመግዛት ወይም በአዋሽ ጉምሩከ ቅ/ፅ/ቤት ስም በተከፈተ ቀጥታ አካውንት የማይመለስ 100 (መቶ) ብር በማስገባት የጨረታ ሰነድ ባሉበት ቦታ በቴሌግራም እንዲላከሎት በማድረግ ለጨረታ የቀረቡትን የእቃዎችን ዝርዝር ከጨረታ ሰነዱ በማየትና እና በማረጋገጥ የሚከተሉትን ዝርዝር መስፈርቶች በሟሟላት በጨረታው መሳተፍ የሚቻል ሲሆን የእታዎችን ሳምፕል ከቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ከአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት እና በቴሌግራም ማየት የሚቻል መሆኑንና ወደ ቃሊቲ እንዲመጣሎት የምትፈልጉት የእቃ ናሙና ካለ የጨረታ ማስታወቂያ በወጣበት ቀን በስልክ ቁጥር 022-224-1402 በመደወል ወደ ቃሊቲ ጉምሩከ ቅ ጽ/ቤት እንዲመጣሎት ማድረግ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡
1. ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመሳተፍ የሚያስፈልጉ ተጫራች በጨረታ በሚሸጡ ዕቃዎች ጋር በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርትፍኬት የዘመኑን ግብር የከፈለ ሰለ መሆኑ ከልራንሰ (Clearance) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ እንቅሰቃሴያቸውን ለታከሰ ማዕከሉ ያላወቁበት በቅርብ ጊዜ የተሰጣቸው የምሰከር ወረቀት እና የመለያ ቁጥሩን ከመጫረቻ ሰነዱ ጋርእያይዞ ማቅረብ የሚችል፡፡
2. ተጫረቾች የጨረታውን ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ ቀን 06/12/2018 እና 09/12/2018 ዓ/ም እስከ ጠዋቱ 3፡45 የኢታውን ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ አዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በአካል በመኘት በመግዛት ወይም በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት ስም በተከፈተ ቀጥታ እካውንት የማይመለስ 100 (መቶ) ብር በማስገባት የጨረታ ሰነድ ባሉበት ቦታ በቴሌግራም እንዲላከሎት ማድረግ ይችላሉ።
3. ለግልጽ ጨረታ ለማሳተፍ ተጫራቶች ለጨረታ ማስከበሪያ (CPO) የሚወዳደሩበት እቃ ኮድ 5 በመቶ እንድሁም ለአራጅ ጨረታ ለሚወዳደሩበት እቃ ኮድ ብር 100,000(አንድ መቶ ሽህ ብር) በባንክ አሰርተዉ በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
4. ተጨረቶች በሚከተለዉ የጨረታ ቀናት (እስከጁል) መሰረቲ በቃሊቲ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት በመገኘት በጫረት ይችላሉ።
|
ተ.ቁ |
የጨረታ ቦታ |
የጨረታው ዓይነት
|
ለጨረታ የቀረቡ እቃዎች
|
የዕቃዎች መመልከቻ ቀን የጨረታው የመዝጊያ እና የመከፈቻ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ
|
የጨረታ የመዝጊያ እና የመከፈቻ ቀንና ሰዓት
|
|
1 |
ቃሊቲ ጉ/ቅ/ጽ/ ቤት
|
ግልጽ ጨረታ እና በሐራጅ
|
ጫማዎች፣ አልባሳት፣ የመኪናመለዋወጫ፣የሞባይል ቀፎና አክሰሰሪ፣ ኤሌከትሮኒክስ፣ምግብ ነክ የስፖርት እቃዎች፣ የእጅ ሰዓት ኮስሞቲከስ መነፅር ጌጣ ጌጦች፣ ጠፍጣፋ ብረት ላሜራ የወዳደቁ ብረቶችና ጥላስቲኮች እና ሌሎች ልዩ ልዩ እቃዎች |
ለግልጽና ለሐራጅ ጨረታ 06/12/2018 09/12/2018 እስከ ጠዋት 3:45
|
ለግልጽ ጨረታ 06/2/2018 እና 09/12/2018 ዓም ከጠዋቱ 4:00 ሲሆን የሐራጅ ጨረታ የመጀመሪያ ጊዜ 06/12/2018 እና 09/12/2018 ዓ.ም 5:00ሰዓት ይሆናል።
|
5. የጨረታው መከፈቻ ቦታ- በቃሊቲ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት የሚካሄድ ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወከሎቻቸው ባሉበት ወይም በታዛቢዎች ፊት ይከፈታል::
6. ለጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋሰትና ያስያዙት (c.p.o) ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፈ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታ ውጤት ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ በ3 የሰራ ቀናት ውሰጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
7. ከአሸፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸው በደብዳቤ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውሰጥ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን በመረከብ ከመጋዝን ማውጣት ይኖረበታል፡፡
8. ከላይ በተቁ በተገለጹት ቀናት ውሰጥ ከፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረከበው ያልወሰዱ ተጫራቶች ያሰያዙት ገንዘብ እና ለንብረቱ የከፈሎት ዋጋ ለኮሚሸኑ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሜ ለሽያጭ ይቀርባል፡፡
9. ቅ/ጽ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት
