የጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 አፄ ነአኩቶ ለአብ ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 001/2019
የጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 አፄ ነአኩቶ ለአብ ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል።
ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ
ሎት 2 የጽዳት ዕቃ
ሎት 3 የደንብ ልብስ
ሎት 4 የደንብ ልብስ ስፌት
ሎት 5 ህትመት አገልግሎት
ሎት 6 የትራንስፖርት አገልግሎት
ሎት 7 ቋሚ ዕቃ
ሎት 8 የካፌ አገልግሎትና መስተንግዶ ግዥ
ሎት 9 የኮምፒውተር፣ ፕሪንተር እና ፎቶ ኮፒ ጥገና ሞንታርቦ ጥገና
ሎት 10 የጥገና ዕቃዎች
በዚሁ መሰረት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ድርጅቶች በጨረታው እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል።
1. በሚወዳደሩበት የንግድ ዘርፍ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ በመንግስት ዕቃ ግዥ በአቅራቢነት የተመዘገበበትን የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ።
2. የጨረታ ማስከበሪያ በየሎቱ ሎት 1. የጽህፈት መሳሪያ 9000 ብር /ዘጠኝ ሺህ ብር/ ሎት 2. የጽዳት ዕቃ 20,000 /ሃያ ሺህ ብር/፤ ሎት3. የደንብ ልብስ 20,000 (ሃያ ሺህ ብር) / ሎት 4. የደንብ ልብስ ስፌት 2000 /ሁለት ሺህ ብር/ ሎት 5. ህትመት 2000 ብር /ሁለት ሺህ ብር/፤ ሎት 6. የትራንስፖርት አገልግሎት 2000 / ሁለት ሺህ ብር / ሎት 7. ቋሚ ዕቃ 28000 (ሃያ ስምንት ሺህ ብር) ሎት 8 .የካፌ አገልግሎት መስተንግዶ 26000 (ሃያ ስድስት ሺህ ብር) ሎት 9. የኮምፒውተር ፕሪንተር ፎቶ ኮፒ ጥገና 4,000 (አራት ሺህ ብር ) ሎት 10. የጥገና ዕቃዎች 18000 (አስራ ስምንት ሺህ ብር) በባንክ ሲፒኦ ማስያዝ አለባቹ። እንዲሁም ጥቃቅንና አነስተኛ ከሆነ ልዩ አስተያየት የሚኖረው አምራች በሆኑበት ዕቃዎች ላይ ብቻ ከአደራጃችሁ አካል የዋስትና ደብዳቤ ማስያዝ ይኖርበታል።
3. ጨረታውን ያሸነፉ ተጫራቾች ከመ/ቤታችን ጋር የውል ማስከበሪያ ላሸነፉባቸው ዕቃዎች የጠቅላላ ዋጋውን 10% በባንክ በተመሰከረ /cpo/ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይጠበቅባችኋል። ይህ ባይሆን ግን በጨረታ ያስያዙት ሲፒኦ በቀጥታ ለመንግስት ገቢ ይሆናል።
4. የሚያቀርቡት የዕቃው ዋጋ በሁለት ፖስታዎች ኦርጅናልና ኮፒ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 አፄ ነአኩቶ ለአብ ቅድመ አንደኛ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 03 በመምጣት ለዚሁ በተዘገጀው ስጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
5. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት በ10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ11ኛው ቀን 3፡00 ሰዓት ቢሮ ቁጥር 03 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል የመክፈቻው ቀን በዓል ወይም እረፍት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል።
6. የጨረታውን ዝርዝር የሚገልጽ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100 ብር /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 3 መውሰድ ይችላሉ።
7. ተጫራቾች ለመወዳደር በመረጡት ዕቃ ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ በፊት በትምህርት ቤቱ ፋይናንስ ማቅረብ አለባቸው።
8. የሚያቀርበው የእያንዳንዱ ዕቃ ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን ይኖርባታል።
9. የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት እና የአቅራቢነት ማስረጃ ኮፒ የሚታይ መሆን አለበት።
10. አቅራቢ ድርጅት በራሱ ትራንስፖርት የጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 አፄ ነአኩቶ ለአብ ቅድመ አንደኛ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ንብረት ክፍል ማድረስ ይኖርበታል።
11. አሸናፊ ድርጅት የውል መስከበሪያ 10% ማስያዝ ይኖርበታል። አስተዳደሩ ባወጣው ጨረታ ላይ ከውል በፊት የዕቃውን ብዛት 20% መጨመርና መቀነስ ይችላል እንዲሁም ከውል በኋላ ደግሞ 25% የዋጋው መጨመር መቀነስ ይችላል በጨረታ መወዳደሪያ የሚቀርብ ዋጋ ለስድስት ወር ፀንቶ ይቆያል።
12. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታው በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
13. ማብራሪያ ቢያስፈልግ በስልክ ቁጥር 011 126 1411 መደወል ይቻላል።
14. የእያንዳንዱ ዕቃ ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን ይኖርበታል።
ማሳሰቢያ፡- ለጥቃቅን እና አነስተኛ ተጫራቾች ቅድሚያ እንሰጣለን በተጨማሪም መወዳደር የሚችሉት አምራች በሆኑበት የንግድ ዘርፍ ብቻ ነው።
አድራሻ፡- አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጀርባ አፍንጮ በር አደባባይ ወደ ሽሮ ሜዳ በሚወስደው 200 ሜትር ገባ ብሎ።
የአፄ ነአኩቶ ለአብ ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
