የቶሌ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2019 ዓ.ም. በወረዳው ለሚገኙት የመንግስት መስሪያ ቤቶች ቋሚ የቢሮ እቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፤ አላቂ እቃዎች /እስቴሽነሪ/ የመኪና እና የሞተር ጎማዎች ፤ የጽዳት እቃዎች፣ የደንብ ልብስ ግዥ እና ስፌትን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ግልጽ የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
የቶሌ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2019 ዓ.ም. በወረዳው ለሚገኙት የመንግስት መስሪያ ቤቶች ቋሚ የቢሮ እቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፤ አላቂ እቃዎች /እስቴሽነሪ/ የመኪና እና የሞተር ጎማዎች ፤ የጽዳት እቃዎች፣ የደንብ ልብስ ግዥ እና ስፌትን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት ማሟላት የምትችሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን፤
1. ከሚያቀርቡት ዕቃ ጋር የተዛመደ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፤የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የተጨማሪ እሴት ተከስ ተመዝጋቢ መሆኑን ማስረጃ የሚያቀርብ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል
2. በዕቃ አቅረቢዎች ዝርዝር (suppliers list) ውስጥ መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ የምዝገባ ወረቀት ፎቶ ኮፒውን ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
3. በሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ኮፒውና ኦርጅናሉን በማቅረብ ስም ፈርማና አድራሻቸውን ማስቀመጥ አለባቸው።
4. በጨረታ ሰነድ ከተገለፀው የዕቃ ፕሮፖዛል ውጭ ተመሳሰዩን ማቅረብ እንደማይቻልና ደረጃውን ያልጠበቀ ዕቃ በስህተት ቢቀርብ መቀየር የሚችል።
5. የሚጫረቱበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ አድርገው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን 28/11/18 ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት ከ2፡30 እስከ 11፡30 ድረስ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጃው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የሚችሉ ሲሆን ጨረታው በ15ኛው ቀን 18/12/18 ከቀኑ 11፡30 ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ 16ኛው ቀን 19/12/18 ከጠዋቱ 3፡00 በቢሮ ቁጥር 7 ይከፈታል የጨረታ ማስከበሪያ የሚመለስ በባንክ የክፍያ ማዘዣ (CPO) 10000.00 /00 /_አስር ሺህ/ ወይም በካሽ ከጨረታው ሠነድ ጋር ብር 10000.00 /አስር ሺህ/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
6. ጨረታውን ማሸነፋቸው ከተረጋገጠ በኃላ የውል ማስከበርያ ጠቅላላ ካሸነፈው ዕቃ የሚመለስ 10% ማስያዝ አለበት
7. ያሸነፈውን ዕቃ ናሙና ማቅረብ ይኖርበታል
8. ጨረታውን ማሸነፋቸው ከተረጋገጠና ዕቃውን ጽ/ቤቱ ድረስ በራሳቸው ወጪ አምጥተው ካስረከቡ በኃላ ክፍያው ይፈፀማል
9. የጨረታውን ሠነድ የማይመለስ ብር 100.00 /መቶ ብር/ ለአንድ ሎት በቶሌ ወረደ ገቢዎች ባለስልጣን ፅ/ቤት ከፍሎ መግዛት ይችላሉ።
10. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድረሻችን የቶሌ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ፤ አ/ሽ አስጎሪባንቱ በሰበታ መስመር 83 ኪሜ ከአ. አ
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡-0945737302/ 0908739411/0983166736
መደወል ይችላሉ:
የቶሌ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
