ሐምሊን ፊስቱላ አትዮጵያ ቀጥሎ በተዘረዘሩት ምድቦች ግዢ በሚፈፅምባቸው ልዩ ልዩ መገልገያዎች እና አገልግሎቶች ጨረታ ላይ መሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶችን በዚህ ማስታወቂያ ይጋብዛል፡- ምድብ ሀ፡- የመድኃኒት እና ሕክምና መገልገያዎች፤
ሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ
የጨረታ ማስታወቂያ
ሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ በወሊድ ወቅት ችግር የሚገጥማቸውን እናቶች ከስድሳ አመታት በላይ የነፃ ሕክምና እየሰጠ የሚገኝ በጎ አድራጎት ድርጅት ሲሆን፣ ከነፃ ሕክምናው በተጨማሪ በሐምሊን አዋለጅ ነርሶች ት/ቤት በመጀመሪያና በሁለተኛ ዲግሪ፤ እንዲሁም በቡራዩ ልዩ ዘን በሚገኘው የደስታ መንደር መልሶ ማቋቋም ማዕከል፡ በምንሰጠው ሕክምና ለዳኑና ተጨማሪ የቅርብ ክትትል ለሚያስፈልጋቸው እናቶች የራስ-አገዝ የሙያ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል፡፡
በዚሁም መሠረት ሐምሊን ፊስቱላ አትዮጵያ ቀጥሎ በተዘረዘሩት ምድቦች ግዢ በሚፈፅምባቸው ልዩ ልዩ መገልገያዎች እና አገልግሎቶች ጨረታ ላይ መሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶችን በዚህ ማስታወቂያ ይጋብዛል፡- ምድብ ሀ፡- የመድኃኒት እና ሕክምና መገልገያዎች፤
ምድብ ለ፡- ልዩ ልዩ የፅዳት መገልገያ ቁሣቁሦች፤
ምድብ ሐ፡- የህትመት እና ልዩ ልዩ ድርጅታችን ሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያን የሚያስተዋውቁ ቁሣቁሦች/PROMOTIONAL MATERIALS/ ግዢ እና ሥራ፤
ምድብ መ፡- የዘጋቢ ፊልም ዝግጅት/DOCUMENTARY VIDEO PRODUCTION/፤
ተጫራቾች ከላይ ለተዘረዘሩት ለእያንዳንዳቸው ምድቦች የተዘጋጁትን ሰነዶች የማይመለስ ብር 300.00/ሦስት
መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ከሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ የፋይናንስ ክፍል መውሰድ ይችላሉ፡፡
የምድብ ሀ እና ለ ጨረታ እስከ አርብ ነሐሴ 8፣ 2018ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰአት ድረስ የሚቆይ ሲሆን፣ ተጫራቾች ወይንም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በማብቂያው ቀን (ነሐሴ 8፣ 2018ዓ.ም) ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ይከፈታል፤ የምድብ ሐ እና መ ጨረታ እስከ ነሐሴ 12 2018ዓ.ም ጠዋት 4፡00 ሰአት ድረስ የሚቆይ ሲሆን፣ ተጫራቾች ወይንም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በማብቂያው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል፤
በተጨማሪም ሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ ታጠቅ የኢንዱስትሪ መንደር በሚገኘው የመልሶ ማቋቋሚያ ማዕከል ውስጥ የሚገኙ አስር/10/ ጊደሮች እና ላሞችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ስለሚፈልግ፡ ፍላጎቱ ያላቸው ድርጅቶች እና ግለሰቦች ይህ ጨረታ በሪፖርተር የአማርኛው ዕትም ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስራ-አራት/14/ ቀናት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዐት እስከ ቀኑ 9፡00 ሰዓት ታጠቅ የኢንዱስትሪ መንደር በሚገኘው የደስታ መንደር የመልሶ ማቋቋሚያ ማዕከል በአካል በመገኘት ለቀረቡት ለአንዱ ወይንም እንደፍላጎታቸው ከአንድ በላይ ከብቶች የመወዳደሪያ ዋጋቸውን እስከ ማክሰኞ ነሐሴ 12፣ 2018 ጠዋት 4፡00 ድረስ እንዲያስገቡ እየጠየቅን፣ ፍላጎቱ ያላቸው ድርጅቶች/ግለሰቦች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00/ሁለት መቶ ብር ብቻ/ መግዛት የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፤ የከብቶቹ ሽያጭ ጨረታ ነሐሴ 12፣ 2018ዓ.ም ከቀኑ በ 8፡00 ሰዓት አዲስ አበባ በሚገኘው ዋናው የድርጅቱ የስብሰባ አዳራሽ የሚከፈት መሆኑን በተጨማሪ እንገልፃለን፡፡
ከላይ የተዘረዘሩትን የጨረታ ምድቦች በከፊል ወይንም በሙሉ ለመሰረዝ ሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ መብቱ
በሕግ የተጠበቀ ነው፡፡
ሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ
ስልክ ቁጥር +251-113716544/45/46-የውስጥ መስመሮች፡ 125/139/182/199፤ በተጨማሪም ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቹ ላይ በተገለፁት የስልክ ቁጥሮች ደውለው የሚያስፈልጋቸውን ማብራሪያ ማግኘት ይችላሉ
