Tender Detail

Tender Details


Sale of seized POLYTHONLINE factory raw plastic and new woolen clothes by public auction


የጨረታ ማስታወቂያ ግልጽ ጨረታ ቁጥር 7-03/2018/19 ዓ.ም

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የአዳማ ቅ/ጽ/ቤት በህገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ ተይዘው የተወረሱ ብዛት ያለውን POLYTHONLINE የፋብሪካ ጥሬ ፕላስቲክ እና አዳዲስ አልባሳት የሱፍ ጨርቆችን በግልጽ ጨረታ ለበት ሁኔታ ለወዳዳሪዎች ለመሸጥ ይፈልጋል። ማሳሰቢያ፡- ጨረታው ሙሉ በሙሉ የሚካሄደው በኦክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ብቻ ሲሆን መተግበሪያውንም ከAT ስቶር ወይም ኘላይ ስቶር (Auction Ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም www.auction.et ላይ መመዝገብ እና መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን፥ በነዚህም መሠረት ከዚህ የተዘረዘሩትን የጨረታ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ግለሰብም ሆነ ድርጅቶች በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን፥

  1. ጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈለገው ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር ተዛማጅነት ያለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከራ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ እንቅስቃሴዎችን ያሳወቁበት በቅርብ ጊዜ የተሰጣቸው የምስክር ወረቀት እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥሩን እንዲሁም ስድ የተመዘገቡትን ደረሰኝ ጨምሮ በኦክሽን ኢትዮጵያ ኦንላይን መተግበሪያ ላይ ማያያዝ ይኖርባቸዋል። ማንኛውም ተጫራች 100 ብር በመክፈል ከኦክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ላይ የጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላል።
  2. በተራ ቁጥር 1 ላይ የተጠቀሱት መስፈርቶች ቢኖሩም መነሻ ዋጋቸው ከ300.000 (ሦስት መቶ ሺህ) ብር በታች የሆኑ ዕቃዎችን ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አያስፈልግም።
  3. የጨረታ ሰነዱን የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ የዕቃዎችን ዝርዝር፣ ዓይነት እና ብዛት የያዘውን ሰነድ የኦክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ ከገብረቶቹ መግለጫ ስር ተያይዞ የሚገኝ ለሆነ አውርደው መመልከት ይኖርባቸዋል። ተጫራቾች በኦክሽን ኢትዮጵያ ላይ ተመዝግበው የጨረታ ሰነዱን ካነበቡ በኋላ ንብረቶቹን በአካል ለመመልከት ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ ሙሉ ቀን በስራ ሰዓት እና ቅዳሜ ጠዋት 100-6:00 ሰዓት መመልከት ይቻላል፡፡
  4. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ የሚወጣበት ቀን እንዲሁም ጨረታው የሚዘጋበት ቀን እና ሰዓት የሚያሳይ ሰንጠረዥ
ተ.ቁ የእቃው ዓይነት የጨረታው ዓይነት በአዲስ ዘመን ጋዜጣ የታተመበት ቀን ጨረታ የሚካሄድበት ቀን ጨረታው የሚጀመር ጨረታው የሚከፈት ስልክ ቁጥር
1 አዳዲስ አልባሳት (የሱፍ ጨርቆች) ግልጽ 02/11/2018 09/11/2018 4:00 8:00 022-111-84-29 022-210-89-25
2 Poly (Ethylene Terphthalate) ግልጽ 02/11/2018 09/11/2018 4:00 8:00  
  1. በግልጽ ጨረታ የሚሳተፉ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ለእያንዳንዱ ምድብ እቃዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተመሰከረለት (CPO) (Customs Commission Adama Branch Office) ስም ብቻ ሲ.ፒ.ኦ በማሰራት በኦንላይን ወይም በአካል ወደ ኦክሽን ኢትዮጵያ ቢሮ ሄደው በማስያዝ የሚጫረቱበትን ዋጋ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  2. በጨረታው ሽያጭ የእቃዎቹ አስመጪ ቤተሰብ ወይም ባለቤት የሆኑ ሰዎች መሳተፍ አይችሉም፡፡ ነገር ግን በጨረታው ተሳትፈው ቢገኙ በህግ ተጠያቂ ይሆናሉ፡፡
  3. በግልጽ ጨረታ ለመሸጥ የወጡት አዳዲስ አልባሳት (የሱፍ ጨርቆች) በአዳማ ከተማ በሬቻ አካባቢ መ/ቤቱ በተከራየው የውርስ መጋዘን ቁጥር 1 እና 2 እንዲሁም፤ ብዛቱ 556 ፓኬት አዳዲስ አልባሳት (የሱፍ ጨርቆች) እና POLYPROPYLENE (የፋብሪካ ጥሬ ፕላስቲክ) አዳማ ቆርቆሮ መ/ቤቱ አዲስ በተከራየው መጋዘን ቁጥር 3 ውስጥ ስለሚገኙ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ከዋለ በኋላ በስምንተኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ጨረታው ይዘጋል፡፡
  4. አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት CPO ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር ተደምሮ የሚታሰብላቸው ሲሆን፤ ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታው ውጤት በተገለጸ በ3 (ሶስት) የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
  5. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በማስታወቂያ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ እቃውን መረከብ ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ከላይ በተ/ቁ 9 ላይ በተገለፁት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት (CPO) ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል፡፡
  7. ለጨረታ የቀረቡት እቃዎች ሽያጫቸው የሚፈጸመው ባሉበት ሁኔታ ስለሆነ ተጫራቾች ሌላ ተመሳሳይ ወይም ተጨማሪ እቃ መጠየቅ አይችሉም፡፡
  8. ቅ/ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  9. ለጨረታ ማስከበሪያ የምታሰሩት CPO ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ መሆን እንዳለበት እና የሌላ ባንክ የማንቀበል መሆኑን እናሳስባለን፡፡ የኦክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ በተመለከተ የጥሪ ማዕከሉን ለማግኘት በስልክ መስመር 09-05-11-5511/011-66-68-828 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።

ለተጨማሪ መረጃ፡- የአዳማ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት የውርስ መጋዘን የስራ ሂደት ስልክ ቁጥሮች 0221118429 እና 0222118925 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የአዳማ ቅ/ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
- Public auction for seized new woolen clothes (556 packets) and factory raw plastics, including polypropylene and poly(ethylene terephthalate). - Issued by the Ethiopian Customs Commission, Adama Branch Office. - Submission deadline is 15/8/2026 at 10:00 AM; opening is at 02:00 PM on the same date. Bidding is conducted only via the Auction Ethiopia app/website. - Bid document price is 100 Birr; bid bond is 5% of the offered price via CPO from the Commercial Bank of Ethiopia. Bidders must submit a renewed trade license, tax clearance certificate, and tax ID; VAT registration certificate is not required for items with a base price below 300,000 Birr.
Save Tender