Tender Detail

Tender Details

  • Company በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ስልጠና ማዕከል
  • Address Addis Ababa, Phone: 0114397220
  • Website
  • Deadline24 Aug 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን ጋዜጣ
  • Bid Document Priceብር 500/ አምስት መቶ ብር /
  • opening dateበ11ኛውቀን በተገኙበት 4፡30
  • Categories Cleaning & Janitorial , Food And Beverage , Finishing Work

የተለያዩ ግዥዎች ግዥ (ምግብ ዝግጅት ግብዓቶች፣ የጽዳትና የጽሕፈት መሳሪያ እቃዎች፣ የሕንጻ ፊኒሽንግ ሥራ፣ የስፖርት መገልገያ እልባሳት፣ የህትመት አገልግሎት)


የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር እ.አ.ስ.ስ.አ.ከ.ስ.ማ.001/2019

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ሥልጠና ማዕከል ለ2019 ዓ.ም አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ግዥዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በዘርፉ ከተሰማሩ ሕጋዊ ድርጅቶች ግዥ መግዛት ይፈልጋል ፡፡

  • ሎት 1፡- የምግብ ዝግጅት ግብዓቶች ምርት ግዥ
  • ሎት 2፡- አላቂ የጽዳትና የጽሕፈት መሳሪያ እቃዎች ግዥ
  • ሎት 3፡- የሕንጻ ፊኒሽንግ ሥራ
  • ሎት 4፡- የሠልጣኞች የስፖርት መገልገያ እልባሳት ግዥ
  • ሎት 5፡- የህትመት አገልግሎት ግዥ

በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች-

  1. በዘርፉ ሕጋዊና የታደሰ ንግድ ፍቃድ የንግድ ምዘገባ ምስከር ወረቀት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምስከር ወረቀት የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (Tim) ምስክር ወረቀት ግብር ከፋይነትን የሚያረጋግጥ ከሀገር ውስጥ ገቢ ሰርተፍኬት (ታከስ ከሊራንስ) እና በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
  2. የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ለእያንዳንዱ ሎት ብር 500/ አምስት መቶ ብር /በመከፈል ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ እየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ የሥራ ቀናት ከሰኞ እሰከ ዓርብ ከጠዋቱ 2፡30-11፡30 ድረስ ብቻ አዲስ አበባ ከተማ አቃቂ ቃሊቲ ከ/ከተማ የእሳትና አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ሥልጠና ማዕከል አስተዳደርና ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 1 ክፍያ በመፈጸም የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላል::
  3. ማስታወቂያው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ 11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ ስልጠና ማዕከለ ግዥ ከፍል ለዚሁ ሲባል በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ የጨረታ ሰነዳችሁን ማስገባት ይኖርባችዋል፡፡
  4. ጨረታው በ11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ተጫራቶች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4፡30 ሥልጠና ማዕከሉ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ዕለቱ በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  5. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የእሳትና አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ሥልጠና ማዕከል ስም የተዘጋጀ የገንዘብ መጠን ለእያንዳንዱ ሎት ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰርተ የባንክ ዋሰትና ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ተጫራቾች የቴከኒክና ፋይናንሽያል ሰነዶች ተለይተዉ በተለያዬ - ፖስታ ፋይናንሽያል ኦርጅናል እና ኮፒ እንዲሁም ቴከኒካል ኦርጅናል እና ኮፒ ተብሎ በአራት ፖስታ በማድረግ ኮፒ እና አርጅናሉ በጉልህ ተጽፎ መቅረብ ይኖርበታል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያው በቴክኒካል ኦርጅናል ስነድ ጋር በአንድ ላይ ታሽጎ መቅረብ አለበት::
  7. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

አድራሻ አዲስ አበባ አቃቂ ቃሲቲ ክፍስ ከተማ ሰታዲየም ጎን ነው::

ለበለጠ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፤0114397220/0114622379 ደውስው ማነጋገር ይችላሉ::

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር የእሳትና አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ሥልጠና ማዕከል

✨ messages.ai_summary
Open tender for various procurements by Addis Ababa Fire and Disaster Risk Management Commission Training Center, including food preparation inputs, cleaning and office supplies, building finishing works, sports equipment, and printing services across five lots. Bidders must hold valid licenses, tax clearance, and supplier registration.
Save Tender