የጽሕፈት መሳሪያ ግዢ እና የኮብልስቶን መንገድ እና የጎርፍ ማስወገጃ ቦይ ግንባታ
የጨረታ መለያ ቁጥር 01/2019
በሲዳማ ብ/ክ/መንግሥት ሁላ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በኩል 2019 በጀት ዓመት ለሁላ ወረዳ ለተለያዩ ሴክተር መ/ቤቶች የጽሕፈት መሳሪያ ፣ ለሀገረ ሰላም ከተማ ማዘጋጃ ቤት በሰቻ ዐ/ቀበሌና ሽቆ 01 ቀበሌያት አጠቃላይ 555.5ሜትር በጌጠኛ ድንጋይ (ኮብልስቶን) መንገድ እና በእነዚሁ ቀበሌያት በከተማው የተለያዩ ቦታዎች አጠቃላይ 659 ሜትር የመንገድ ዳር ጎርፍ ማስወገጃ ቦይ (ዲች) በተለያዩ ሎቶች ከፋፍሎ በጨረታ አወዳድሮ ለማሠራትና ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ
- በየዘርፉ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ገብረው ያሳደሱ
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያላቸውና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ
- ለግንባታ ሥራ ዘርፍ ደረጃ 5 እና ከዚያ በላይ
- ለግንባታ ሥራ ለእያንዳንዱ LOT 200,000 ብር (ሁለት መቶ ሺህ) ብር CPO ከታወቁ ባንኮች በሁላ ወረዳ ፋይናንስና ኢ/ል/ጽ/ቤት ስም ማቅረብ የሚችል፡፡
- አንድ ተጫራች ከአንድ LOT (ሎት) በላይ መወዳደር አይችልም፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ለአላቂ የቢሮ ዕቃ 20,000 ብር CPO ከታወቁ ባንኮች በሁላ ወረዳ ፋይናንስና ኢ/ል/ጽ/ቤት ስም ማቅረብ የሚችል ፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 20 ቀናት ማለትም ከ8/12/18 ዓ/ም እስከ 5/13/18 ዓ.ም ድረስ ባለው ጊዜ የጨረታ ሰነድ መግዛት ይቻላል፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በኦሪጂናልና በኮፒ በፖስታ በማሸግ ፖሰታው ላይ የድርጅቱን አድራሻ፤ ህጋዊ ማህተምና ፊርማ በማኖር በአንድ ትልቅ ፖስታ በማሸግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ21ኛው የሥራ ቀን ረፋድ 4፡00 ሰዓት 21ኛው ቀን በዓል (የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በሁላ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 በአካል በመገኘት ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ በማስገባት ታሽጎ ከቀኑ 4፡10 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ጨረታው ላይ ምንም ዓይነት ስርዝ ድልዝ ሊኖር አይገባም፡፡
- ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም የጨረታውን ሂደት አያስተጓጉልም፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
በሲዳማ ብ/ክ/መንግሥት ሁላ ወረዳ ፋ/ኢ/ል ጽ/ቤት
✨ messages.ai_summary
Tender for office equipment purchase and construction of cobblestone roads and drainage ditches in Hulla District, Sidama. Includes 555.5m cobblestone road and 659m drainage ditch across multiple lots. Bidders need valid licenses, tax clearance, VAT registration, and construction grade 5 or higher. One lot per bidder.
