የተለያዩ የአጋዥ መጽሃፍት፣ የቧንቧ እቃዎች፣ የቤት እና የቢሮ እቃዎች፣ ኬሚካሎች እና የጽዳት እቃዎች ግዥ
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ወሎ አስተዳደር ዞን የላስታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለላስታ ወረዳ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል፡- ሎት1 የተለያዩ የአጋዥ መጽሃፍት ፤ ሎት2 የቧንቧ እቃዎች ፤ ሎት3 የቤት እና የቢሮ እቃዎች፤ ሎት4 ለተለያዩ ላብራቶሪዎች የሚያገለግሉ ኬሚካሎች እና ሎት 5 የተለያዩ የጽዳት እቃዎች፣ በሂውማን ካፒታል በጀት እና በመደበኛ በጀት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው፡፡
- በአዲሱ የንግድ አዋጅ መሠረት በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/ቲን ነምበር/ ሰርተፍኬት ያላቸውና፣ የሚሞሉት ዋጋ ከ200,000/ከሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ሰርተፍኬት ማቅርብ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ የኢት.ብር 200 /ሁለት መቶ ብር /በመክፈል ላስታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁ 3 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው እቃዎች በጥሬ ገንዘብ ወይም ከባንክ በተረጋገጠ CPO 1.5%/አንድ ነጥብ አምስት ፐርሰንት/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያው ከፖስታው ውስጥ አብሮ መግባት ወይም ጨረታው ከመከፈቱ በፊት በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት የመጀመሪያው ቀን አንስቶ የሚቆጠር 15 ተከታታይ ቀናት ድረስ ከፍት ሆኖ ይቆይና በ16ኛው ቀን፡- ሎት 01 የተለያዩ አጋዥ መጽሃፍት ፤ሎት 02 የቧንቧ እቃዎች፤ ሎት 03 የቤት እና የቢሮ እቃዎች፤ ሎት 04 የተለያዩ ላብራቶሪዎች አገልግሎት የሚሰጡ ኬሚካሎች/ ጠዋት 3፡30 ታሽጎ 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- የተጠቀሰው ቀን ቅዳሜ፣ እሁድ ወይም በካላንደር ዝግ ከሆነ ለሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ይተላለፍና ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ላስታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 2 ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሠነዳቸውን ኮፒና ኦርጅናል በተለያየ ፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ ለዚሁ ሲባል በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- አሸናፊው አካል እቃዎችን በራሱ ትራንስፖርት ላስታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ አጓጉዞ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- የጨረታ መዝጊያ ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታ ራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
- ተጫራቾች በአንድ ሎት ውስጥ የተዘረዘሩትን የእቃ አይነቶች ከፋፍሎ መሙላት አይቻልም ውድድሩ በየሎት ምድቡ ጥቅል ብር ወይም ድምር ስለሆነ የሁሉም ዋጋዎች መሞላት አለበት፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች ተጨማሪ መረጃ ወይም ማብራሪያ ከፈለጉ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 03333601249 ወይም 0911579138 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የላስታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
✨ messages.ai_summary
Open tender for procurement of supplementary books, pipe fittings, home and office supplies, laboratory chemicals, and cleaning items across five lots for Lasta district sector offices. Bidders need valid trade license, registration, TIN, and VAT certificate if applicable. Delivery by bidder's transport to Lasta district finance office.
