የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ለ8ኛው ዙር የቡና ቤተሰብ ዓመታዊ ሩጫ የመሮጫ ቲሸርትን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ለ8ኛው ዙር የቡና ቤተሰብ ዓመታዊ ሩጫ የመሮጫ ቲሸርትን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘረውን የምታሟሉ ድርጅቶች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
- የሩጫ ማሊያው ክለቡ በሚያቀርበው ዲዛይንና ቀለም ሆኖ ደረጃውን በጠበቀ ፓሊስተር መሰራት አለበት ፡፡
- የሩጫው ማሊያ የክለቡ እና የስፖንሰሮች ሎጎ ያረፈበት መሆን ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቹ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ እንዲሁም የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ የብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 5,000 (አምስት ሺህ ብር) በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት ሜክሲኮ በሚገኘው የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ህንጻ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 114 መግዛት ይችላሉ፡፡ ስለማሊያው ክብደትና ስለሚሰራበት ግብዓት እንዲሁም ዲዛይን በተመለከተ ዝርዝር መረጃ ከጨረታ ሰነዱ ጋር የሚሰጥ መሆኑን እናስታውቃለን፡፡
- ተጫራቹ ቲሸርት ሊሰሩ የሚችሉበትን ዋጋ በስም በታሸገ ኢንቨሎፕ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን በመግዛት ከማይመለስ ናሙና ጋር እስከ ነሐሴ 19 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ነሀሴ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በክለቡ ፅ/ቤት ይከፈታል፡፡
- ክለቡ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0911 48 10 72 በስራ ሰዓት ደወለው መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
ኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ
