Tender Detail

Tender Details

  • Company የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት (FDRE Refugees and Returnees Service)
  • Address የእንቁላል ፋብሪካ አደባባይን ሳይሻገሩ ከፌዴራል ፖሊስ ክበብ ፊት ለፊት : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011 813 21 93
  • Websitehttps://rrs.et/
  • Deadline28 Aug 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceብር 200 (ሁለት መቶ)
  • opening dateበዚያው ዕለት ከቀኑ 4፡30 ይከፈታል፡፡
  • Categories Textile, Garment & Leather

የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ለሰራተኞቹ የሚሆን የደንብ ልብስ (ብትን ጨርቅ፣ ሸሚዝ፣ የወንድና ሴት ጫማዎች፣ ቱታ እና ሌሎችም) በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡


የጨረታ ማስታወቂያ

የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ለሰራተኞቹ የሚሆን የደንብ ልብስ (ብትን ጨርቅ፣ ሸሚዝ፣ የወንድና ሴት ጫማዎች፣ ቱታ እና ሌሎችም) በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ ተጫራቾች፡-

  1. የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ በጨረታ ለመወዳደር የሚያስችል ታክስ ከሊራንስ፣ ህጋዊና የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ያላቸውና በጨረታው ለመሳተፍ በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያሳይ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው መሆን አለባቸው፡፡
  2. የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) የስራ ቀናት ውስጥ በስራ ሰዓት ገንዘብ ያዥ ቢሮ ወይም ሂሳብ ከፋይ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡ ቅዳሜና እሁድ የመስሪያ ቤቱ የስራ ሰዓት አይደሉም፡፡
  3. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) የስራ ቀናት ውስጥ በጨረታ ሰነዱ ላይ ለተጠቀሱት ዕቃዎች ዋጋ ዝርዝር በመሙላት በአገልግሎቱ ዋና መስሪያ ቤት የግዥ ቡድን ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ ቀኑ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የተጫራቾች ዋጋ በግልፅ የሚነበብና ስርዝ ድልዝ የሌለው መሆን ይኖርበታል፡፡ ስርዝ ድልዝ ያለበት የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
  4. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ስራ ቀን ከቀኑ 4፡00 ተዘግቶ በዚያው ዕለት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከቀኑ 4፡30 ይከፈታል፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ተጨማሪ ዕሴት ታክስን ጨምሮ የሚቀርቡትን አጠቃላይ ዋጋ 2% (ሁለት በመቶ) ለስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት (Refugees and Returnees Service) በሚል የተዘጋጀ የባንክ ማዘዣ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የእቃ ናሙና የጨረታ ሰነዱ የሚገቡበት ወቅት የዞ በመምጣት የጨረታው መክፈቻ ቀንና ሰዓት በማለፍ በፊት በግዥ ቡድን ማስረከብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  7. የጨረታው አሸናፊ ውል በሚፈርምበት ወቅት የመልካም ስራ አፈፃጸም ማስከበሪያ /Performance Bond/ የጨረታውን አጠቃላይ ዋጋ 10% (አስር በመቶ) ለስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት (Refugees and Returnees Service) በሚል በተረጋገጠ የባንክ ማዘዣ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ (Unconditional Bank Guarantee) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  8. የጨረታው አሸናፊ ጥሪው በደረሰው በ10 ቀናት ውስጥ በአገልግሎቱ ዋና መስሪያ ቤት ቀርቦ የስራ ውል መፈረም አለበት፡፡
  9. አሸናፊው ጥሪ በደረሰው በአስር ቀናት ውስጥ በአገልግሎቱ ዋና መስሪያ ቤት ቀርቦ ውል ካልፈረመ አሸናፊነቱ ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለመስሪያ ቤቱ ገቢ ይሆናል፡፡
  10. አሸናፊ ተጫራች የሚያቀርበው እቃ በሰጠው ናሙና መስሪያ ቤቱ በሚመርጠው ቀለም (color) እና ልኬት (size) መሰረት መሆን ይኖርበታል፡፡
  11. አሸናፊ ሆነው የተመረጡ ድርጅቶች የሚያቀርቡት ልብስ ዓይነት ቢጠብ ወይም ቢሰፋ ለመቀየር የሚስማሙ መሆን አለባቸው፡፡
  12. አገልግሎት መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ

የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት
የእንቁላል ፋብሪካ አደባባይን ሳይሻገሩ ከፌደራል ፖሊስ ከበብ ፊት ለፊት
ስልክ ቁጥር፡ 09-97-23-66-31 / 09-43-01-29-44

የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ቁጥር 1

✨ messages.ai_summary
Procurement of staff uniforms (cotton fabric, shirts, men's and women's shoes, suits, and more) via open tender. Bidders must hold valid VAT registration, tax clearance, renewed trade license, business registration, professional competence certificate, and supplier registration.
Save Tender