ኢትዮ አግሪ ሴፍት ሃላ.የተ.የግ.ማህበር ጉመሮ 80 ግራም እና ውሽውሽ 100 ግራም የሻይ ማሸጊያ ወረቀት ግዥን በግልጽ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር EAC 040/2018
- ኢትዮ አግሪ ሴፍት ሃላ.የተ.የግ.ማህበር ጉመሮ 80 ግራም እና ውሽውሽ 100 ግራም የሻይ ማሸጊያ ወረቀት ግዥን በግልጽ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከነሐሴ 13 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ነሐሴ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 2:30 - 6፡30 እንዲሁም ከሰዓት በኋላ ከ7፡30 እስከ 10፡00 ድረስ "ኢትዮ አግሪ ሴፍት ሃላ.የተ.የግ.ማ" ጉርድ ሾላ ሴንቸሪ ሞል ፊት ለፊት ወይም ላሜ ዲያሪ ጀርባ ከኤልፎራ አግሮ ኢንዱስትሪ አጠገብ በሚገኘው የኢትዮ አግሪ ሴፍት ሕንጻ ላይ ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 106 በመቅረብ የማይመለስ ብር 200.00 ብር /ሁለት መቶ ብር/ በመከፈል እና የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር መለያ ቁጥር ያላቸው፣ የታክስ ክሊራንስ ሰርተፍኬት፣ የአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ እና የቫት ምዝገባ ሰርተፍኬት ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን በመያዝ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቶች የሚያቀርቡት
- አንድ ዋና /Original/ የጨረታ ሰነድ ለብቻው በሰም በታሸገ ፖስታ ታሽጎ
- አንድ ቅጂ /Copy/ የጨረታ ሰነድ ለየብቻው በታሸገ ፖስታ ታሽጎ እንዲሁም፤
- ሁሉም በአንድ ላይ በትልቅ ፖስታ ውስጥ ተካቶ የታሸገ መሆን አለበት፡፡
- በዋናውና በቅጂው መካከል ልዩነት ቢፈጠር ዋናው ተቀባይነት ይኖረዋል፡፡ ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፡፡ የተሰረዘ ሰነድ በፊርማ መረጋገጥ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቶች ጉመሮ 80 ግራም እና ውሽውሽ 100 ግራም የሻይ ማሸጊያ ወረቀት ግዥን የሚያቀርቡበትን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የጠቅላላ ዋጋ 2% /ሁለት ከመቶ/ የባንክ ክፍያ ማዘዣ /C.P.O/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ (Unconditional) የባንክ ጋራንቲ ለኢትዮ አግሪ ሴፍት ሃላ.የተ.የግ.ማ በሚል ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ቀን ነሐሴ 20 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ከጠዋቱ በ4፡30 ሰዓት ድረስ ቢሮ ቁጥር 208 ሲሆን፣ ጨረታውን የመክፈቻ ቀን ነሐሴ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተዘግቶ 4:45 ሰዓት ላይ ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 106 ይሆናል፡፡
- ከላይ የተገለጸውን መመሪያ ባልተከተሉ ተጫራቾች ላይ ወዲያውኑ ከጨረታው የሚሠረዝ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- ተጫራቶች ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0116676204 ፋክስ ቁጥር 0116732006 መጠቀም ይችላሉ፡፡
- ኢትዮ አግሪ ሴፍት ሃላ.የተ.የግ.ማ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ኢትዮ አግሪ ሴፍት ሃላ.የተ.የግ.ማህበር
✨ messages.ai_summary
Ethio Agri CErt PLC seeks bids to procure tea packaging paper for Gumero 80g and Wushwush 100g. Bidders must have renewed business licenses, tax ID, tax clearance, supplier registration, and VAT certificates.
