በደቡብ ኢት/ያ ክልል የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ ለ2019 በጀት ዓመት የተለያዩ እቃዎችን በሎት ከፋፍሎ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ኢት/ያ ክልል የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ ለ2019 በጀት ዓመት የተለያዩ እቃዎችን በሎት ከፋፍሎ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
- ሎት 1. ጽ/መሳሪያ ሎት-2. ህንጻ መሳሪያ ሎት 3 ኤልክትሮኒከስ ሎት 4, የተለያዩ ህትመቶች ሎት-5. የግንባታ ግብዓቶች ሎት 6. ሻይ ቡና መስተንግዶ ሲሆኑ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉት፡-
- በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉት በሚመለከታቸው መስሪያ ቤቶች በአቅራቢነት የተመዘገቡና ለ2019 በጀት ዓመት በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና በ EGP የተመዘገቡ፣ ከዚህ በፊት ላከናወናቸው ተመሳሳይ ሥራዎች / አገልግሎቶች ከአሠሪው አካል የመልካም ሥራ አፈጸጸም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መወዳደር ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት (አስራ አምስት ቀናት) ከታች ከተጠቀሰው አድራሻ መግዛት ይችላሉ።
- የተዘጋጀውን መደበኛ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 500.00 (አምስት መቶ ብር) በማቅረብ መግዛት ይችላሉ። የጨረታ ሰነድ የሚገኝበት ቦታ ወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ ግዥ ንብረት አስተዳደር ዋና ሥራ ሂደት ቢሮ ይገኛል።
- ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን አንስቶ እስከ 16ኛው ቀን ከቀኑ 4፡00 (አራት ሰዓት) ድረስ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ የጨረታ ሰነድ ማስገባት ይችላሉ። ዘገይቶ የሚቀርብ ጨረታ ተቀባይነት አይኖረውም ሳይከፈት ለተጫራቹ ይመለስለታል።
- ጨረታው የሚከፈተው ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸውና ሌሎች መገኘት የሚፈልጉ ባሉበት በ16ኛው ቀን ከቀኑ 4፡00 ላይ ታሽጎ በዕለቱ ከቀኑ 4፡30 የሚከፈት ይሆናል። 16ኛው ቀን የበዓላት ቀን ከሆነ (የሥራ ቀን ካልሆነ) በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
- ተጫራቾች የጨረታ ዋስትና ለእያንዳንዱ፡- ሎት-1 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) ሎት-2 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) ሎት -3 ኤልክትሮኒከስ 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) ሎት-4 40,000.00 (አርባ ሺህ ብር) ሎት-5 40,000.00 (አርባ ሺህ ብር) ሎት-6 40,000.00 (አርባ ሺህ ብር) በባንክ የተመሰከረለት ሲፒኦ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ርክብከብ የሚፈጸምበት ቦታ ወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ ቅጥር ግቢ ውስጥ ይሆናል።
- የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ 0461800863 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ።
የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ
✨ messages.ai_summary
Open tender for procurement of various goods in six lots: office equipment, building equipment, electronics, prints, construction inputs, and tea/coffee hospitality supplies. Bidders must be registered suppliers with renewed trade licenses, VAT registration, and EGP registration.
