Tender Detail

Tender Details

  • Company በኢሉባቦር ዞን አልጌ ሣቺ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት
  • Address ኢሉባቦር ዞን : ኦሮሚያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0913357097
  • Website
  • Deadline17 Sep 2026, 10:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price500 (አምስት መቶ ብር) በማይመለስ
  • opening dateበዚሁ ቀን በ4፡30 ሰዓት
  • Categories Electrical And Electromechanical , Office Supplies And Services , Vehicle

በኢሉባቦር ዞን አልጌ ሣቺ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡


የጨረታ ማስታወቂያ

በኢሉባቦር ዞን አልጌ ሣቺ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

  1. የጽሕፈት መሣሪያዎች
  2. የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች
  3. የመኪና እና የሞተር ጎማና የተለያዩ መለዋወጫ ዕቃዎች
  4. የፈርኒቸር ዕቃዎች
  5. የሠራተኞች ደንብ ልብስ እና የስፖርት ልብስ
  6. የግንባታ ዕቃዎች
  7. የተለያዩ ጀነሬተሮች እና ሞተር ሳይከል
  8. የምግብ አቅርቦት
  1. በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ ያለው የዘመኑን ግብር የከፈለና ማስረጃ አያይዞ ማቅረብ የሚችል እና የቫት /VAT/ ተመዝጋቢ የ2019 ዓ.ም መሆን አለበት፡፡
  2. በንግድ ሚኒስቴር በአቅራቢነት ዝርዝር የተመዘገበ፡፡
  3. ለጨረታ ማስከበሪያ 40,000.00/አርባ ሺህ/ ብር በሲፒአ / CPO/ ለእያንዳንዱ ዶክመንት ማስያዝ የሚችልና ጨረታውን ካሸነፈ በኋላ ለውል ማስከበሪያ ያሸነፈበትን ዕቃ ጠቅላላ ዋጋ 10% በባንክ በተመሰከረ ሲግኒ /CPO/ ማስያዝ አለበት፡፡
  4. ተጫራቹ ጨረታውን ካሸነፈ ቀርቦ ውል ለመፈረም ፈቃደኛ የሆነና ዕቃዎቹን በራሱ ሙሉ ወጪ በታዘዘ በ21 ቀን ውስጥ እስከ ጽ/ቤቱ ለማቅረብና ቆጥሮ ማስረከብ አለበት፡፡
  5. ተጫራቹ የዕቃውን ሞዴል ባልተገለጸበት ቦታ በጨረታው ዝርዝር ላይ አብራርቶ መግለጽ አለበት፡፡
  6. ተጫራቹ የተፈለገውን ዕቃ ጥራትና ብዛት አሟልቶ የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡
  7. በፈርኒቸር ዕቃዎች ላይ የሚወዳደሩ ድርጅቶች የፈርኒቸሮችን ዲዛይን ከዋጋው ጋር ማቅረብ እና ካሸነፈ ገጣጥሞ ማስረከብ የሚችል መሆን ይኖርበታል፡፡
  8. ተጫራቹ ለሚያቀርባቸው የደንብ ልብሶች:- የላፕቶፕ ቦርሳዎች ለመ/ቤቱ አስፈላጊ ለሆኑ ዕቃዎች ሳምፕል /ናሙና/ ማቅረብ አለበት፡፡ ተጫራቹ የሚያቀርበው ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን አለበት፡፡
  9. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን 21/12/2018-6/1/2019 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን 7/1/2019 ረቡዕ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተጠናቆ በዚሁ ቀን በ4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢሉባቦር ዞን አልጌ ሣቺ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ከግዥ ክፍል 13 ቁጥር በመቅረብ የዕቃዎቹን ዝርዝር እና ለዚሁ የተዘጋጀውን የተጫራቾችን መመሪያ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  10. ተጫራቾች እያንዳንዱን የጨረታውን ሰነድ በማይመለስ 500 (አምስት መቶ ብር) ከኢሉባቦር ዞን ገንዘብ አልጌ ሣቺ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዢ ክፍል 13 ቁጥር በመግዛት የሚጫረቱበትን መወዳደሪያ የአንዱን ዋጋ በመሙላት ለጨረታው በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል፡፡
  11. በሌላ ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ ከልክል ነው፡፡
  12. የሚወዳደሩበትን ሰነድ ስርዝ ድልዝ የሌለው እና የሚነበብ መሆን አለበት፡፡
  13. ተወዳዳሪዎች ዋጋን የሚገልጽ ሰነድ ኦርጅናል እና ኮፒ ለየብቻ ፍቃድንና የተለያዩ ተፈላጊ ሰነዶችን የሚገልጽ ኦርጅናል እና ኮፒ ለየብቻ እንዲሁም ሲፒአ/ CPO/ ለየብቻ በፖስታዎች በማሸግ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  14. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታው ሣጥን በግዥ ክፍል ቁጥር 13 ውስጥ ከፍት መሆኑን አውቃችሁ እስከ 22ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ፖስታዎችን በፈለጋችሁት በመንግሥት የሥራ ሰዓት ማስገባት ትችላላችሁ፡፡
  15. መብቱ የተጠበቀ ነው
  16. ተጫራቾች በኦሪጅናል ፋንታ ኮፒ አድርገው የተለያዩ የዕቃ ዓይነቶች መወዳደር ይችላሉ፤ (ለምሳሌ Computer Lap Top HP, Note Book lenevo)፤ ቀለሞችን፣ ጎማዎችን፣ የጽዳት ዕቃዎችን የመሳሰሉትን በተለያዩ ገጽ ፎቶ ኮፒ በመሙላት መወዳደር ይችላላችሁ፤
  17. VAT 7.5 % እና TOT 3% ከሚለው ዕቃ የሚቆረጥ ይሆናል
  18. ተጫራቾች የደንብ ልብስ ጨርቅ ናሙና ከፖስታው ጋር አሽጎ ማቅረብ አለበት፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0913357097 ወይም 0917273702

በኢሉባቦር ዞን አልጌ ሣቺ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
Open tender for procurement of office supplies, electronics, vehicle tires and spare parts, furniture, uniforms, sportswear, construction materials, generators, motor cycles, and food supplies. Bidders must have valid trade license, VAT registration, and supplier registration.
Save Tender