የነፃነት ጮራ አንደኛና መካከለኛ ደ/ት/ቤት ለ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት የሚያስፈልጉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የነፃነት ጮራ አንደኛና መካከለኛ ደ/ት/ቤት ለ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት የሚያስፈልጉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ
|
የዕቃው ዓይነት
|
የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሲፒኦ
|
|
ሎት 1
|
የደንብ ልብስ
|
15,000
|
|
ሎት 2
|
አላቂ የትምህርት ዕቃዎች
|
18,000
|
|
ሎት 3
|
አላቂ የቢሮ ዕቃዎች
|
6,230
|
|
ሎት 4
|
ሌሎች አላቂ ዕቃዎች /የፅዳት/
|
15,000
|
|
ሎት 5
|
መፅሐፍት
|
2,000
|
|
ሎት 6
|
ቋሚ እቃ ግዥ
|
5,000
|
|
ሎት 7
|
የስፖርት እቃዎች
|
5,000
|
|
ሎት 8
|
የህክምና እቃዎች
|
300
|
|
ሎት 9
|
የትምህርት መርጃ መሳሪያ
|
2,000
|
|
ሎት 11
|
መስተንግዶ(ቆሎ፣ውሃ፣)
|
1,236.59
|
|
ሎት 12
|
ህትመት
|
4,700
|
በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ የሚከተሉትን ቅድመ ሁኔታዎች ማሟላት አለባቸው።
1. ተጫራች ሙሉ ስማቸውን፤ አድራሻቸውን ፊርማቸውን በእያንዳንዱ ሰነድ ላይ ማስፈር ይኖርባቸዋል።
2. ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው የዘመኑን ግብር የከፈለና የታደሰ ንግድ ፈቃድ መረጃ ማቅረብ የሚችል።
3. የተጨማሪ እሴት ታከስ ከፋይነት ማስረጃ የማቅረብ የሚችል፤ከመንግስት ጨረታ አቅራቢነት ያልታገደ መሆኑን አለበት።
4. በሚወዳደርበት ዘርፍ በአቅራቢነት ዝርዝር ዌብ ሳይት የተመዘገበበት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
5. ጥራቱንና ደረጃውን የጠበቀ ዕቃ በውሉ ላይ በተፈቀደ ጊዜ ውስጥ ማቅረብ የሚችሉ።
6. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና / በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ/ሲፒኦ/ለእያንዳንዱ ሎት ማስያዝ ይኖርበታል።
7. ናሙና እንዲቀርብ ለተጠየቀባቸው ለእያንዳንዱ ዕቃ ከጨረታው መክፈቻ ቀን አስቀድሞ ናሙና ማቅረብ የሚችልና እና በተመረጠው ናሙና መሰረት የሚያቀርብ።
8. እቃዎችን በተቀመጠላቸው ስፔስፊኬሽን መሰረት ማቅረብ የሚችል።
9. አንድ ተጫራች በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችሉም።
10. በዚህ ጨረታ የሚሳተፍ ማንኛውም ተጫራች ከመንግስት ግዢ ያልታገደ መሆን አለበት።
11. የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00/ሦስት መቶ ብር/ በመክፈል ከቢሮ ቁጥር 03 መውሰድ ይቻላሉ
12. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን እቃ ዋጋ ቫቱን አጠቃሎ ት/ቤቱ ባዘጋጀው ሰነድ ላይ ሞልተው የድርጅታቸውን ማህተም እና ፊርማቸውን ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል።
13. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን እና የተጠየቁትን ማስረጃዎችን ዋናውን እና ኮፒውን በታሸገ ኢንቨሎፕ ለየብቻ በማድረግ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የስራ ቀናት ውስጥ ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
14. ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ወይም ባይገኙም በት/ቤቱ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል።
15. የጨረታው ውጤት ከታወቀ ከ7 ቀን በኋላ የጨረታ አሸናፊው ቀጣይ ባለት 5 ቀናት ውስጥ ቀርቦ ያሸነፈበትን ዕቃ ዋጋ 10 % በማስያዝ መዋዋል አለበት።
16. የጨረታ አሸናፊዎች ዕቃዎቹን በራሳቸው ትራንስፖርት ጭነውት/ቤቱ ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
17. ት/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
18. ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኃላ ባቀረቡት የመወዳደሪያ ዋጋ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ ወይም ከጨረታው እራሳቸውን ማግለል አይችሉም።
19. ጨረታውን ለማባዛት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታው የሚሰረዙ ይሆናል።
20. ተጫራቾዎች የዋጋ ዝርዝራቸውን በገዙት ጨረታ ሰነድ ላይ ብቻ ሞልተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ይህ ባይሆን ከጨረታ ይሰረዛሉ።
21. ተጫራቾች በንግድ ፍቃዳቸው በስተጀርባ ላይ የተዘረዘሩትን የንግድ ፍቃድ ዘርፍ አይነቶች ኮፒ አድርገው ማቅረብ አለባቸው የተጫራቾች ማህተብ እና የንግድ ፍቃድ ፍቃዳቸውን እንዲሁም የደረሰናቸውን ስያሜ አንድ አይነት መሆን ይኖርበታል።
በጨረታ መወዳደሪ የሚቀርብ ዋጋ ለስድስት ወር ፀናቶ የሚቆይ ይሆናል።
አድራሻ- ቄራ ከጎፋ ማዞሪያ ወረድ ብሎ ን/ስ/ላ/ክ/ከ ወረዳ 06 ውስጥ ሶፊያ ሞል በኩል ገባ ብሎ
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0114672575 ይጠይቁ
አዲስ አበባ
የነፃነት ጮራ አንደኛና መካከለኛ /ደ/ት/ቤት ፋይናንስ ግዥና ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት
የነፃነት ጮራ አንደኛና መካከለኛ /ደ/ት/ቤት
