የደራርቱ ቱሉ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት በ2017 ዓ.ም አገልግሎት ላይ የሚውሉ የተለያዩ እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል ፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር :-002/2017
የደራርቱ ቱሉ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት በ2017 ዓ.ም አገልግሎት ላይ የሚውሉ የተለያዩ እቃዎች ማለትም :-
- የደንብ ልብሶች
- አላቂ የቢሮ ዕቃዎች
- አላቂ የህክምና ዕቃዎች
- ቋሚ እቃዎችን
በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል ፡፡ በዚህ መሰረት ተጫራቾች፡-
- በመንግስት ዕቃ አቅራቢነት ተመዝግበው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ እና ቫት ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በዘርፉ ወይም በመስኩ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው መሆን አለባቸው::
- የዘመኑን ግብር የከፈሉና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት በትምህርት ቤቱ ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 10 ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቶች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረብያ ቦታ በግልጽ በመሙላት በመጨረሻ ቦታ ላይ ስም፣ ፈርማና ህጋዊ ማህተም በማኖር በታሸገ ኤንቨሎፕ ዋናውን እና ፎቶ ኮፒውን በማሸግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ከ2፡00-11፡00 ዋጋቸውን በመሙላት በተጠቀሰው የስራ ሰዓት የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
ለጨረታ ማስከበርያ የሚሆን የሚወዳደሩበትን ዋጋ በሲፒዮ ብር 2% (ሁለት ፐርሰንት) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ናሙና ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች ጨረታው ሊዘጋ አንድ ቀን እስከቀረው ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታውን እሸናፊ ሆነው ከተገኙ በኋላ 10% ባሸነፉበት ዕቃ መጠን መሰረት የውል መስከበሪያ ማስያዝ ይኖርቦታል፡፡
- ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክር ከጨረታው ውጪ እንደሚሆንና የጨረታውን ማስከበርያ CPO እንደሚወረስባቸው ማወቅ አለባቸው::
- ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች እና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በተዘጋ በቀጣዩ የስራ ቀን ከቀኑ በ5፡00 ሰዓት በትምህርት ቤቱ የግ/ፋይ/ንብ/አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 10 ይከፈታል።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0114343278/ 0114715349
አድራሻ፡- በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ ስምንት ከቃሊቲ ቶታል ዝቅ ብሎ ከአሮጌው አስፓልት 200 ሜትር ገባ ብሎ
የደራርቱ ቱሉ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት
