Tender Detail

Tender Details


የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኀበር የሰብአዊ አገልግሎቶች አቅም ግንባታ ማዕከል ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ሥራዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል::


 

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኀበር

የሰብአዊ አገልግሎቶች አቅም ግንባታ ማዕከል

በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

 

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኀበር የሰብአዊ አገልግሎቶች አቅም ግንባታ ማዕከል ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ሥራዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል::

 

የሎት ቁጥር

የሥራው ዓይነት

ዝርዝር መግለጫ

1

የጅም ማሽኖች ጥገና

ብስክሌቶች እና የተለያዩ ማሽኖች

 

የደረት መደገፊያ አዲስ የሚሰራ

 

2

የስቲም ማሽን የሚጠገን

 

3

የድንኳን ብረቶች በማስተካከል ሸራ መሥራት እና ያረጁ ድንኳኖችን ሸራ መቀየር፣

የሸራውን ዓይነት ሳምፕል በማቅረብ

4

የተበላሸ የዳቦ መጋገሪያ ኦቭን፣ የልብስ ማጠቢያ ፣ የልብስ ማድረቂያ እና መተኮሻ ማሽኖችን መጠገን እና ስርቪስ ማድረግ፣

 

5

በማዕከሉ የእህል መጋዘን እና የተለያዩ ክፍሎች የተባይ ማጥፊያ መድኃኒት መርጨት፣

የሚረጨውን ቦታ በመለካት ዋጋውን በካሬ ማስቀመጥ በየሣምንቱ አገልግሎቱን መስጠት

6

ለሠራተኞች የተለያዩ ዩኒፎርሞችን መሥራት::

በሚገዙት ሰነድ መሠረት የጨርቁን አይነት ማስያዝ አለባችሁ

 

ለተለያዩ ወንበሮች ልብስ ጨርቅና ስፌትን ጨምሮ መሥራት፤

የጨርቁ ዓይነት ነጭ ሆኖ ሳምፕል ይቀርባል

 

በዚሁ መሠረት ከላይ በተቀመጠው ዝርዝር መሠረት የእያንዳንዱን ዋጋ የያዘው ፖስታ ላይ የሎት ቁጥሩን በመፃፍ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ::

  1. ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የሥራ ፈቃድ ፤ የግብር ከፋይ  ሰርተፍኬት እና ሌሎች መረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዶች ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፤
  2. ተቋሙ ድረስ በመምጣት የሚሰሩትን ሥራዎች አይቶ ዋጋ መስጠት፣
  3. በጨረታው ለመወዳደር ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ 2% ባንክ በተረጋገጠ ... አዘጋጅቶ ማስያዝ ይኖርበታል፣
  4. በሎት1,2 እና 6 ስር ላሉት የሥራ ትእዛዞች የተዘጋጀውን ሰነድ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሠነዱን በመግዛት ይኖርባችኋል፤
  5. የጨረታ ሰነዱን በፖስታ አሽጎ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በግንባር ቀርቦ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ከስኞ እስከ ቅዳሜ ዘወትር በሥራ ሰዓት ሳሪስ አደይአበባ ገባ ብሎ በሚገኘው የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኀበር ሰብአዊ አገልግሎቶች አቅም ግንባታ ማዕከል ማስገባት ይኖርባችኋል፣
  6. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስን የሚያጠቃልል መሆኑን መግለጽ ይኖርባችኋል፤
  7. ተጫራቾች ከላይ የተዘረዘሩትን ሥራዎች ውል በመግባት ዋስትና መስጠት ይኖርባችኋል፣
  8. ጨረታው ግንቦት 8 ቀን 2017 . ከቀኑ 800 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ እለት ከቀኑ 830 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል፣
  9. ተቋሙ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

ለበለጠ መረጃ- 0114421130/0114407460 ላይ መደወል ይቻላል።

 

Save Tender