ድርጅታችን ሆራይዘን ፕላንቴሽንስ ቡና ማዘጋጃና ማከማቻ በቡና ኤክስፖርት ዝግጅትና ክምችት አገልግሎት የተቆላና የተፈጨ ቡና በማምረትና በማከፋፈል፤ የብሪኬት ከሰል ምርት እንዲሁም ጆንያ በማምረት ስራ ላይ የተሰማራ ተቋም ነው፣ ስለሆነም ከአዲስ አበባ ውጭ ባሉ የክልል ከተሞች ላይ የቡና ምርት ሽያጭ በወኪል አከፋፋዮች በኩል ለማከናወን ስለፈለገ ከዚህ በታች የቀረበውን መስፈርት የሚያሟሉ ወኪል አከፋፋዮችን ይጋብዛል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡- 04/2017
ድርጅታችን ሆራይዘን ፕላንቴሽንስ ቡና ማዘጋጃና ማከማቻ በቡና ኤክስፖርት ዝግጅትና ክምችት አገልግሎት የተቆላና የተፈጨ ቡና በማምረትና በማከፋፈል፤ የብሪኬት ከሰል ምርት እንዲሁም ጆንያ በማምረት ስራ ላይ የተሰማራ ተቋም ነው፣ ስለሆነም ከአዲስ አበባ ውጭ ባሉ የክልል ከተሞች ላይ የቡና ምርት ሽያጭ በወኪል አከፋፋዮች በኩል ለማከናወን ስለፈለገ ከዚህ በታች የቀረበውን መስፈርት የሚያሟሉ ወኪል አከፋፋዮችን ይጋብዛል፡፡
ሎት 1 (የቡና ምርት ማከፋፈል)
-
- ከአዲስ አበባ ውጪ በዘርፉ የታደስ ንግድ ሥራ ፈቃድ ፣ የብቃት ማረጋገጫ፣ የታክስና የግብር ከፋይነት ምዝገባ ሠርተፍኬት ያላቸው መሆን ይገባቸዋል።
- በአከፋፋይነት አቅራቢነት ልምድ ያለው መሆን ይኖርበታል፡፡
- በውል መሰረት በጋራ ለመስራት ፈቃደኛ መሆን ይጠበቅበታል፡፡
ሎት 2 (ያገለገሉ ንብረቶች ሽያጭ)
|
ተ.ቁ |
የንብረት ዓይነት |
መለኪያ |
|
1 |
ያገለገሉ የማሽን ክፍሎች |
ኪሎ |
|
2 |
ቁርጥራጭ ብረቶች |
ኪሎ |
|
3 |
ጥቅም ላይ የዋለ ወረቀት |
ኪሎ |
|
4 |
የቢሮ መገልገያዎች |
ባሉበት |
- ከ
- ለጨረታው የተዘጋጀውን ዝርዝር የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 ደብረ ዘይት መንገድ ከቅዱስ ዮሴፍ ቤተ-ክርስቲያን ፊት ለፊት ወደ ብሄረ ጽጌ መናፈሻ መንገድ 200 ሜትር ገባ ብሎ በመገኘት መግዛት ይችላል።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን በሚወዳደሩበት የንብረት ዓይነት ከ50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) ብር ጀምሮ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) ብቻ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ሎት አንድ የጨረታ መወዳደሪያ ዋጋቸውን ከላይ ከተጠቀሱት ህጋዊ ሠነዶች ጋር በታሸገ ኤንቨሎፕ አንደ አሪጅናል እንዲሁም አንድ ኮፒ በማድረግ እስከ ግንቦት 23 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ ይችላሉ።
- ጨረታው በተመሳሳይ ግንቦት 23 ቀን 2017 ዓ.ም 4:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ሎት ሁለት ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ቀናት ክፍት ሆኖ በ16ኛው ቀን ተዘግቶ በቀጣዩ ቀን 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ተወካዮቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- የጨረታው አሸናፊ በጨረታው ማሸነፉ በተነገረው በአጭር ቀናት ውስጥ ገንዘቡን ከፍሎ እቃውን ማንሳት ይኖርበታል።
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ሳሪስ ዮሴፍ ቤተ-ክርስቲያን ፊት ለፊት የድሮው ቡና ቦርድ
ስልክ ቁጥር ፡-09-01-77-74-44/09-08-66-65-55
ሆራይዘን ፕላንቴሽንስ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር
