ድርጅታችን የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኤጀንሲ ያወጣውን የጥራት መስፈርት የሚያሟሉ እና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ሸቀጦች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የሸቀጥ ግዥ የጨረታ ማስታወቂያ
(ቁጥር 001/2018)
ድርጅታችን የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኤጀንሲ ያወጣውን የጥራት መስፈርት የሚያሟሉ እና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ሸቀጦች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
1. የበለፀገ እንደኛ ደረጃ የዳቦ ዱቄት፣ 2. ሩዝ፣ 3. ፓስታ፣ 4. ማካሮኒ፣ 5. የልብስ ማጠቢያ ሳሙና፣ 6. ፈሳሽ የልብስ ማጠቢያ ሳሙና፣ 7. የገላ መታጠቢያ ሳሙና፣ 8. ስፖንጅ ፍራሽ እና ትራስ፣ 9. ከጥጥ የተመረተ እንሶላ፣ 10. የብርድ ልብስ፣ 11. ፎጣ፣ 12. የግድግዳና ቆርቆሮ ሚስማር፣ 13. የቤት ክዳን ቆርቆሮ 14. የአርማታ ብረት፣ 15. የፕሪንተር ወረቀት በጨረታው መካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች:-
- ለሁሉም ምርቶች በጨረታው ላይ መሳተፍ የሚችሉት አምራች ድርጅቶች ብቻ ሲሆኑ በፕሪንተር ወረቀት ጨረታ ለመሳተፍ አምራች፣ አከፋፋይ ወይም አስመጪ መሆን ይችላሉ፡፡
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ፈቃድ፤ ተጨማሪ ዕሴት ታክስ የተመዘገቡ፣ የግብር ከፋይነት ምዝገባ ሠርተፍኬት እና የግብር ክሊራንስ ያላቸው መሆን ይገባቸዋል፡፡
- ለጨረታ የተዘጋጀውን ዝርዝር የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ቢስ መብራት ከሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት የኢንዱስትሪ ውጤቶች ግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ለእያንዳንዱ ምርት በጨረታ ሰነዱ ላይ በተጠቀሰው መሰረት) ለብቻው በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የጨረታ መወዳደሪያ ዋጋቸውን (financial)ና ከላይ ከተጠቀሱት ህጋዊ ሠነዶች (technical) በተለያየ የታሸገ ኤንቨሎፕ አንድ ኦርጅናል እንዲሁም አንድ ኮፒ በማድረግ እስከ ሐምሌ 18 ቀን 2017 ዓ.ም ከረፋዱ 5፡00 ሠዓት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ጨረታው በተመሳሳይ ሐምሌ 18 ቀን 2017 ዓ.ም ከረፋዱ 5፡10 ሠዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ከጨረታ መዝጊያ ሰዓቱ በኋላ የሚቀርብ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስልክ ቁጥር 0111-28-15-29
www.eiide.com.et.com.et
የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት የኢንዱስትሪ ውጤቶች ግዥ ዳይሬክቶሬት
