Tender Detail

Tender Details


በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከዚህ በታች በዝርዝር የተቀመጡትን እቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በሀራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡


 

በገቢዎች ሚኒስቴር ጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ /ቤት የተተው ዕቃዎች የሀራጅ ጨረታ ቁጥር ሐ-01/2018 ጨረታ

 

በኢትዮጵያ ጉምሩ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩ ቅርንጫፍ /ቤት በጉምሩ አዋጅ 859/2006 መሰረት በጉምሩክ ቁጥጥር ሥር ያለ ንብረቶች ስለሚወገዱበት ሥርዓት በወጣው መመሪያ ቁጥር 167/2012 እንቀጽ 10 መሠረት የተወረሱ ንብረቶችን ማለትም PRINTED ALUMINIUM FOIL & PRINTED ONE SIDE ALUMUNIUM LAMINATEDORS SACHET REEL:

DEXTROSE ANHYDROUS: PRINTED CARTON BOXES: BABY FEEDING SMALL ROUND TOWEL AND OTHERS: FAN FOR SINOTRUCK ON STICKER, COOPER ONSTICKER & OTHER: SKMEI IRON ADULT HAND WATCH: AIR FILTER: AIR IMPACT WRENCHKIT SPORT SHOES BRAND: LED UFO HIGHBAY LIGHT: 2IN IPOLYSTER TENT እና (TRAVELING) & POLYSTER TENT MAT: GLACIAL ACETIC ACID ANGLE VALVE እና ENGINE CERIA GUASCKET

እቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በሀራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በዚህም መሠረት ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለመረት የሚፈልጉና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

  1. ተጫራቾች የዕቃዎቹን ዝርዝር፤ ዓይነት እና ብዛት በማስታወቂያ ሠሌዳ እና በአካል ለመመልከት ዘወትር ከሰኞ እስከ ሐሙስ ከጠዋት 200 እስከ ቀኑ 600 ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 700 እስከ ቀኑ 1030 እና ዓርብ ከጠዋት 200 እስከ ቀኑ 500 ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 730 እስከ ቀኑ 1030 እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋት 200 እስከ ቀኑ 530 ድረስ ከቅ//ቤቱ ገቢ ሂሳቦች ቡድን ሰነዱን በመግዛት መመልከት ይቻላል፡፡
  2. ተጫራቾች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር በዘርፉ የፀና ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ /ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ሆኖም ግምታዊ ዋጋቸው ከብር 500,000.00 (አምስት መቶ ) በታች የሆነ ማንኛውንም ዕቃ ለመግዛት የተጨማሪ እሴት (VAT) ምዝገባ ሠርተፍኬት ማቅረብ ሳያስፈልግ መወዳደር ይችላሉ፡፡
  3. ማንኛውም ተጫራች ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆን የሚጫረትበትን ለሁሉም ዕቃዎች ዘርፉ በሚፈቅደው ብር 300,000.00 (ሶስት መቶ ሺህ) ብር ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክበተረጋገጠ CPO ጨረታ ከመከፈቱ በፊት በቅድሚያ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ተጫራቾች የሚያስይዙት CPO በቅርጫፍ /ቤቱ ሥም ETHIOPIAN CUSTOMS COMMSSON MODJO BRANCH OFFICE በሚል ሲሆን በኢትዮጵያ ንግድ ባን ከአዲስ አበባ፣ አዳማና ሞጆ በነዚህ ብቻ ከንግድ ባንክ ውጪ የማንቀበል መሆኑን ይታወቅ ቅርጫፎች መዘጋጀት አለበት፡፡
  4. የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 8ኛው የሥራ ቀን በዚሁ ዕለት ጠዋት 500 ሰዓት ላይ ተጫራቾቹ ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቅርንጫፍ /ቤቱ ለጨረታ በአዘጋጀው ቢሮ ውስጥ የሚከፈት ሆኖ ማንኛውም ተጫራች እስከ 445 ሰዓት የሚጫረትበትን ዕቃ ለይቶ እቃ አወጋገድ ቡድን ቀርቦ ማስመዝገብ ይኖርበታል፡፡
  5. ማንኛውም የጨረታ ሽያጭ የዕቃው አስመጪ ወይም ባለቤት እና ቤተሰብ የነበሩ ሰዎች በጨረታው መሳተፍ አይችሉም! ጨረታውን ከአሸነፈ በኋላ እራሱን ከጨረታው ውድድር ማግለል አይቻልም፤ የሰጠው የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታው ግምገማ ተጠናቆ ቅርንጫፍ /ቤቱ የጨረታውን ውጤት እስከሚያሳውቅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል፡፡
  6. የሐራጅ ጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ስለማሸነፋቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ 5 (አምስት) ቀናት ውስጥ የአሸነፉበትን ዕቃ ዋጋ ገቢ በማድረግ ዕቃውን መረከብ አለበት፡፡ 5 (አምስት) ቀናት ውስጥ ገንዘቡ ገቢ ካልተደረገ ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPO ያስያዙት ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል፡፡
  7. በተራ ቁጥር 06 በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ የአሸነፉበትን ዕቃ ዋጋ ገቢ አድርጎ ዕቃውን ያልተረከበ እንደሆነ ለሚቆይበት ለተጨማሪ ጊዜ የመጋዘን ኪራይ ይከፍላል። ሆኖም ዕቃው 2 (ሁለት) ወራት ውስጥ ካልወጣ እንደተተወ ተቆጥሮ በጨረታ ሽያጭ ይወገዳል።
  8. አሸናፊው ተጫራች ዕቃዎችን ለመረከብና ለማጓጓዝ የሚያስፈልጉ ወጪዎችን ሁሉ ራሱ ይሸፍናል።
  9. ቅርንጫፍ /ቤቱ ዕቃዎቹን ለመሸጥ የተሻለ አማራጭ ወይም ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  10. ለተጨማሪ ማብራሪያ በሥልክ ቁጥር 022-236-90-94 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

 

በገቢዎች ሚኒስቴር ጉምሩክ ኮሚሽን ሞጆ ጉምሩክ //ቤት

 

Save Tender