Tender Detail

Tender Details


በአ/ከ/ክ/ከተማ የወረዳ 5 ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለተለያዩ ሴክተር ጽ/ቤቶች ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል።


 

2018 በጀት አመት 1 ዙር ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

 

በአ///ከተማ የወረዳ 5 ፋይናንስ /ቤት 2018 በጀት ዓመት ለተለያዩ ሴክተር /ቤቶች ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል።

ሎት ቁጥር

የሎት ዝርዝር

ከጠቅላላ ዋጋ የሚያሲዙት የብር መጠን

ሎት 1

የደንብ ልብስ

27,349.18

ሎት 2

ቋሚ ዕቃዎች

20,000.00

ሎት 3

የቢሮ አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች

9,628.00

ሎት 4

አላቂ የፅዳት ዕቃዎች

29,224.00

ሎት 5

የኮምፒተር የፕሪንተርና የፎቶ ኮፒ ጥገናዎች

30,000.00

ሎት 6

የቢሮ መስተንግዶ

24,105.03

ሎት 7

የመኪና ኪራይ

15,243.73

ሎት 8

የልብስ ስፌት

10,000.00

ሎት 9

የተለያዩ የሕትመት ስራዎች

5000.00

ሎት 10

የተለያዩ የግብርና ዘሮች

5000.0

 

በመሆኑም ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶችን የምታሟሉ ተጫራቾች እንድትወዳደሩ ይጋብዛል።

  • የዘመኑ ግብር ከፍለው የታደሰ ንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉና የግብር መለያ ቁጥር ያላቸው።
  • የቫት /TIN NO/ ተመዝጋቢ የሆኑና በአቅራቢዎች ዝርዝር ስለመመዝገባቸው መረጃ የሚያቀርቡ ተጫራቾች ለመወዳደር የጨረታ ሰነድ ስታስገቡ ለተወዳደራችሁበት አላቂ ዕቃ እና የልብስ ስፌት ሳምፕል ማቅረብ ይኖርባችኋል።
  • ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ /cpo/ ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ 0.5% በማስላት በማስያዝ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፤ ይህን ካላቀረበ ክውድድር ውጪ ይሆናሉ።
  • ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት በማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ/ ብር በመክፈል በወረዳ 5 //ቤት 2ተኛ ፎቅ ወደ ቢሮው ሲገቡ በስተቀኝ በመግባት መግዛት ይችላሉ።
  • የጨረታ ሠነዱ በተጫራቾች መሞላት ያለባቸው ክፍሎች በሙሉ መሞላት አለባቸው።
  • በስራ ኢንተርፕራይዝ የተደራጃችሁ በራሳችሁ ምርት ላይ ልዩ አስተያየት ስለሚደረግ አምራች መሆናችሁን የሚገልፅ መረጃ ካደራጃችሁ አካል የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ አለባችሁ።
  • በስራ ኢንተር ፕራይዝ የተደራጃችሁ ከምታመርቱት ምርት ውጪ ባለ ዘርፍ እና ሰነድ ላይ እንደማንኛውም ተጫራች ድርጅት cpo ማስያዝ ይኖርባችኋል።
  • ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ ሲያቀርቡ ቫትን አካተው ዋናውንና ኮፒውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው። ጨረታው 11ኛው የስራ ቀን 400 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 430 ይከፈታል።
  • ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚቀርብ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
  • ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታ ራሱን ማግለል አይቻልም።
  • የተጫራቾችን አድራሻ የሚገልፅ ሙሉ መረጃ ከሰነዱ ጋር መያያዝ አለበት።
  • መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  • ተጫራቾች የውል ማስከበሪያ ካሸነፈው ዕቃ ከጠቅላላ ዋጋ 10% በባንከ የተረጋገጠ/cpo/ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  • ተጫራቾች የቢሮ መስተንግዶ ላይ የምትወዳደሩ የውሃና የቆሎ ሳምፕል ማቅረብ አለባችሁ።
  • ሳምፕል ያላቀረበ ተጫራች ድርጅት ከጨረታ ውጭ ይሆናል።
  • አሸናፊ ተጫራች ድርጅት የአሸነፋችሁትን ዕቃ በራሳችሁ ትራንስፖርት በማጓጓዝ ማቅረብ አለባችሁ።
  • አድራሻ፡- ከመድሃኒዓለም /ቤት ወደ አበበ ቢቂላ ስታዲየም መውረጃ 300 ሜትር ገባ ብሎ
  • ለበለጠ መረጃ፡- ስልክ ቁጥር 011-8-27-81-54 /09-27-60-26-30/

ማሳሰቢያ፡-

  • በተጫረታችሁበት ዕቃ ላይ ዋጋ ስታስገቡ ቫትን ያካተተ መሆን ይጠበቅበታል። መወዳደር የሚቻለው ንግድ ፍቃዱ ላይ በተሰጠው ስራ ዘርፍ ብቻ ነው።
  • ተጫራቾች ያስገባችሁትን ሳምፕል በቂ ማስቀመጫ ቦታ ስለሌለን አሸናፊና ተሸናፊ ከተለየ በኋላ 60 /ስልሳ የስራ ቀናት ውስጥ እንድትወስዱ እያሳሰብን በተቀመጠው ቀናቶች ውስጥ የማይወስድ ተጫራች /ቤቱ መስሪያ ቤቱ /ሃላፊነቱን አይወስድም።
  • ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዛችሁትን cpo ለውል ማስከበሪያ/ማዞር ማስያዝ አይቻልም።
  • ተጫራቾች ዋና የጨረታ ሰነድ ላይ ክፍል 6 /ስድስት/ በተጫራቾች የሚሞላውን ቅጽ መሙላት እና በየአንዳንዱ ገጽ ላይ ፊርማና የድርጅታችሁን ማህተም በማድረግ የጨረታ ሰነዱን መመለስ ይኖርባችኋል። ነገር ግን ክፍል 6 ላይ በተጫራቾች የሚሞላውን ቅፅ ያልሞላ ተጫራች እና የጨረታ ሰነዱን ካልመለሰ ተመላሽ ካላደረገ ከላይ የተጠቀሱትን ያላሟላ ተጫራች ጨረታው ውድቅ ይሆንበታል።
  • ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያም ሆነ ለውል ማስከበሪያ የምታሲዙት CPO ብቻ ነው። ከሲፒኦ ውጪ በቼክና በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አይቻልም። ካስያዛችሁም ከውድድር ውጪ ትሆናላችሁ።

 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የወረዳ 5 አስተዳደር ፋይናንስ /ቤት

 

Save Tender