የአርሲ ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 የበጀት ዓመት በዞኑ ለሚገኙ ጽ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ ፈርኒቸር ፣ የጽህፈት መሣሪያዎች ፣ የጽዳት እቃዎች፣ የሠራተኞች የደንብ ልብስ፤ እና የመኪና ጎማና ባትሪ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ ቁ-01/2018
የአርሲ ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 የበጀት ዓመት በዞኑ ለሚገኙ ጽ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ ፈርኒቸር ፣ የጽህፈት መሣሪያዎች ፣ የጽዳት እቃዎች፣ የሠራተኞች የደንብ ልብስ፤ እና የመኪና ጎማና ባትሪ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም:-
- ለተጠየቁት የግዥ እቃዎች የንግድ ስራ ፈቃድ መስጫ መዳብ ኮድ / * Licensing Category Code ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ከፍለው የንግድ ፈቃዳቸውን ያሳደሱ ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (Tax Payer Registration No.) የተጨማሪ እሴት ታከስ ተመዝጋቢ የሆኑ እና በፌደራል፣ በክልል ወይም በዞን ገንዘብ ጽ/ቤት ወይም በግዢዎችና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ያላቸው ዋናውንና ኮፒውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች ለቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ለመኪና ጎማና ባትሪ እቃዎች እና፣ ለጽህፈት መሣሪያዎች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 800.00 (ስምንት መቶ) ፤ ለቋሚ የቢሮ ፈርኒቸር እቃዎች የማይመለስ ብር 450.00 (አራት መቶ ሀምሳ) ፤ ለጽዳት እቃዎች ፣ እና ለደንብ ልብስ ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 600.00 (ስድስት መቶ) በአርሲ ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት ስም ስንቄ ባንክ በሂሳብ ቁጥር 1071378041218 ገቢ በማድረግ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ኮፒ እና የጽሁፍ ማመልከቻ በመያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት የጽ/ቤቱ የግዥ፤ ንብረት አስተዳደር ፤ ማስወገድና ጠቅላላ አገልግሎት ቢሮ ቁጥር 106 ድረስ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ከግብር ሰብሳቢው መ/ቤት የዘመኑን ግብር አጠናቀው ለመክፈላቸው እና ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን ደብዳቤ ከግብር ሰብሳቢው መ/ቤት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ በመሙላት በዝግ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ 16ኛው የሥራ ቀናት ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን፤ ጨረታው በ16ኛው የሥራ ቀን ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከቀኑ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጽ/ቤቱ የስብሳባ አዳራሽ የሚከፈት ሲሆን ዕለቱ ቅዳሜና እሁድ ወይም ህዝባዊ በዓላት ከሆነ በሚቀጥላው የስራ ቀን በተማሳሳይ ቀን፤ ሰዓትና ቦታ ይከፈታል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ለቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ፤ እና ለመኪና ጎማዎችና ባትሪ ለእያንዳንዱ ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 160.000.00 (አንድ መቶ ስልሳ ሺህ) ፤ ለጽህፈት መሣሪያዎች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 118,000.00 (አንድ መቶ አስራ ስምንት ሺህ) ፤ ለደንብ ልብስ ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 66,000.00 (ስልሳ ስድስት ሺህ) ፤ ለጽዳት እቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 42,000.00 (አርባ ሁለት ሺህ) እንዲሁም ለቋሚ የቢሮ ፈርኒቸር እቃዎች ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 25,000.00 (ሀያ አምስት ሺህ) ፤ በአቅራቢያችሁ በሚገኝ የታወቀ ባንክ በክፍያ ማዘዣ (C.P.O.) ብቻ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- አሸናፊው ተጫራች ያለምንም የአቅርቦት ችግር አስተማማኝ የሆነ የዕቃ ከምችት ያለውና እቃዎቹን በራሱ የማጓጓዣ ወጪ አሰላ ከተማ ውስጥ በሚገኘው የዞኑ ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ አምጥቶ ማስረከብ ይኖርበታል፡፡
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ ስ.ቁጥር 0222381142 ይጠይቁ።
የአርሲ ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት
