በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተለያዩ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት:-
- የተለያዩ የደንብ ልብሶች፣ አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ የጽዳት ዕቃዎች፣ የቢሮ ፈርኒቸሮች፣ የአይሲቲ ዕቃዎች የቢሮ ፈርኒቸሮች ጥገና፣ የአይሲቲ ዕቃዎች ጥገና፣ የመስተንግዶ አገልግሎት፣ የህትመት፣ የዲኮር እና የዲጄ አገልግሎት የጉልበት ስራ አገልግሎት፣ የፊኒሺንግ ስራዎች፣ የመስተንግዶ አገልግሎት፣ የልብስ ስፌት አገልግሎት የብረታ ብረት ስራ፣ መጠነኛ የፋይል መደርደሪያ ስራ፣ የትራንስፖርት ኪራይ አገልግሎት እና የጄነሬተር ጥገና በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም
በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች፡-
-
-
- ተጫራቾች በመንግስት ግዥ በዕቃ አቅራቢነት ውስጥ የተመዘገቡ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- እኛ ከሰጠነው የጨረታ ሰነድ የዋጋ ዝርዝር ማቅረቢያ ውጪ ሞልቶ የሚያቀርብ ተጫራች ተቀባይነት አይኖረውም።
- ተጫራቾች ህጋዊ የሆነ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ሠነድ /ክሊራንስ/ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ከስር ከተጠቀሱት ሎቶች ውጪ ለእያንዳንዱ ሎቶች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና አጠቃላይ ያቀረቡትን ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ CPO ብቻ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ለመስተንግዶ አገልግሎት፣ ለህትመት አገልግሎት፣ ለትራንስፖርት አገልግሎት፣ ለፈርኒቸር ጥገና አገልግሎት፣ ለአይሲቲ ዕቃዎች ጥገና አገልግሎት፣ ለጉልበት ስራ አገልግሎት፣ ለዲጄ አገልግሎት፣ ለልብስ ስፌት አገልግሎት እና ለጄኔሬተር ጥገና አገልግሎት ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር ብቻ) በባንክ በተረጋገጠ CPO ወይንም ቅድመ ሁኔታ እና የጊዜ ገደብ የሌለው ቢድ ቦንድ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- አሸናፊው ተጫራች የውል ማስከበሪያ የውሉን 10% ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
- ገዥው መስሪያ ቤት በጨረታው ወቅት 25% ሊጨምርም ሊቀንስም ይችላል ።
- በተጨማሪም ገዥው ከአሸናፊው ተጫራች ጋር ውል ከተዋዋለበት ቀን ጀምሮ 20% እስከ 6 ወር ባለው ጊዜ ውስጥ ሊጨምር ይችላል፡፡
- ተጫራቾች በተሰጣቸው የንግድ ዘርፍ ብቻ መሳተፍ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች ናሙናቸውን ከጨረታ መክፈቻው በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብቻ) በመክፈል በቂ/ክ/ከ/የወረዳ 07 ፋይናንስ ጽ/ቤት ውስጥ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቻቸውን ዋናውንና ኮፒውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት እለት አንስቶ እስከ 10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታው ያቀረቡት ዋጋ የሚቆይበትን ጊዜ ቢያንስ ለ 60 ቀን መሆኑን መግለጽ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት በዓል ከሆነ በቀጣዩ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቂ/ክ/ከ/የወረዳ 07 ፋይናንስ ጽ/ቤት ውስጥ ይከፈታል፡፡
- የወረዳው ፋይናንስ ጽ/ቤት የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
-
ማሳሰቢያ፡-
በአ/አ/ከ/አስ/የመንግስት ግዥ እና ንብረት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 17/2002 አንቀፅ 17 ንዑስ 2 እና የግዥ አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 3/2002 አንቀጽ 15 ንዑስ አንቀፅ 20.5 በተደነገገው መሰረት ለጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የጨረታ ሰነድ በነፃ የምንሰጠው በሃገር ውስጥ ምርት ማምረት ዘርፍ ላይ ለተሰማሩ ብቻ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-515-88-38 አድራሻ፡- ብሄራዊ ከበድሉ ህንጻ በስተጀርባ ቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 7 አስተዳደር ጽ/ቤት 1ኛ ፎቅ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
