በልደታ ክፍለ ከተማ ስር የሚገኘው ወረዳ 04 ጤና ጣቢያ የሚከተሉትን እቃዎች መግዛት ይፈልጋል።
1ኛ ዙር የጨረታ ማስታወቂያ
በልደታ ክፍለ ከተማ ስር የሚገኘው ወረዳ 04 ጤና ጣቢያ የሚከተሉትን እቃዎች መግዛት ይፈልጋል፤ የህትመት ስራዎች ፤ የፈርኒቸር ዕቃዎች፤ የህንፃ መሳሪያ ዕቃዎች፤ የህክምና ዕቃዎችና መድሃኒቶች፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ የደንብ ልብስና የደንብ ልብስ ስፌቶች፤ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፤ ቋሚ ዕቃዎች፤ ጥገና እና በጤና ጣቢያ ውስጥ ክፍት ቦታ መስፋፍፊያ እና የካፌ አቅርቦት።
ስለሆነም ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር ይችላሉ።
- ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን የታደሰ ንግድ ፈቃድና የዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር /Suppliers list/ መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ ከመንግስት ግዥ ኤጀንሲ የተሰጠ የምስክር ወረቀት እንዲሁም የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 120 /አንድ መቶ ሃያ ብር/ በመክፈል ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የሥራ ቀናት በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 ጤና ጣቢያ 4ኛ ፎቅ ግዢ ክፍል በአካል ቀርቦ መግዛት ይቻላል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ለህክምና ዕቃ ብር 20,000 /ሀያ ሺህ ብር/፤ እና መድኃኒት ብር 20,000 /ሀያ ሺህ ብር/፣ ቋሚ ዕቃ ብር 20,000 /ሀያ ሺህ ብር/፣ ለጥገና 20,000 /ሀያ ሺህ ብር/ ፣ ለኤሌክትሮኒክስ 20,000 (ሀያ ሺህ ብር) እና ለሌሎች ለእያንዳንዳቸው ሎት 5,000 ብር /አምስት ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ /CPO/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዕቃ ዝርዝር ዋጋና መለያ ቁጥር በተራ ቁጥር 1 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ማህተምና ፊርማ በማኖር በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት የጨረታውን ሰነድ (የተሞላ ሙሉ ሰነድ) 4ኛ ፎቅ ግ/ን/አስ/ደጋፍ የስራ ሂደት ባለው በታሸገ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- የመወዳደሪያ ዋጋ በጨረታ ሰነዱ ለዋጋ መስጫ በተዘጋጀው ቦታ ያለ ቫትና ከቫት ተለይተው መስጠት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች ጨረታው ከመከፈቱ ሁለት ቀናት በፊት ኦርጅናል እና ደረጃቸውን የጠበቁ ናሙና በልደታ ክፍለ ከተማ የወረዳ 04 ጤና ጣቢያ 4ኛ ፎቅ ሜዲካል ዳይሬክተር ቢሮ አጠገብ ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታው ሳጥን ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ የወጣበትን 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት በአሥረኛው ቀን በ11፡00 ሰዓት ታሽጎ በቀጣዩ ቀን በ4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል ዕለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው በመንግስት ስራ ቀን ሆኖ ሰዓቱ እንደተጠበቀ ይሆናል። በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ያለመገኘት የጨረታ ሳጥን መክፈቻ ሥነ- ስርዓትን አያጓትትም፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- 0113692872 መካኒሳ አቦ መዞሪያ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ /ፒስ ህንጻ/ ወደ ውስጥ 400 ሜትር ገባ ብሎ 4ኛ ፎቅ ላይ ቢሮ ቁጥር 403
በልደታ ክፍለ ከተማ የወረዳ 04 ጤና ጣቢያ
