የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት ለዞኑ ዐቃቤ ህግ ጽ/ቤት በ2018 በጀት አዲስ ላስገነባው G+2 ህንጻ የተለያዩ ጥራታቸው የተጠበቁ የቢሮ ውስጥ መገልገያ ዕቃዎችን ማለትም ሎት አንድ ቋሚ የቢሮ ፈርኒቸሮች እና ጥራቱ የተጠበቀ ሻተር መጋረጃ ከነማስገጠሚያው ዋጋ ጨምሮ፣ ሎት ሁለት ልዩ ልዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን ከሃገር ውስጥ ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የግዢ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡- BFEWAA/01/2018
የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት ለዞኑ ዐቃቤ ህግ ጽ/ቤት በ2018 በጀት አዲስ ላስገነባው G+2 ህንጻ የተለያዩ ጥራታቸው የተጠበቁ የቢሮ ውስጥ መገልገያ ዕቃዎችን ማለትም ሎት አንድ ቋሚ የቢሮ ፈርኒቸሮች እና ጥራቱ የተጠበቀ ሻተር መጋረጃ ከነማስገጠሚያው ዋጋ ጨምሮ፣ ሎት ሁለት ልዩ ልዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን ከሃገር ውስጥ ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ስለሚፈልግ በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መመሪያዎች አሟልተው መገኘት ይኖርባቸዋል፡፡
- በንግድ ዘርፉ ወይም መስኩ የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ፤
- የመንግስት ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ከግብር ሰብሳቢ መሥሪያ ቤት ወቅታዊ /ጊዜው ያላለፈበት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- በመንግስት ዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተካተቱና የቲን እና የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የራሱ የሆነ የተጠየቁ የዕቃዎችና በቂ ማከማቻ ቦታ /Store/ ያላቸው እና የዕቃዎቹን ናሙና ማሳያ /Show room/ ሊኖረው ይገባል፡፡
- በጨረታው ላይ የሚሳተፍ ማንኛውም ተወዳዳሪ ዓመታዊ የሽያጭ መጠን ቢያንስ እስከ 20,000,000.00 /ሃያ ሚልዮን ብር/ መሆን አለበት፡፡
- ለጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና ለሎት አንድ 200,000.00 ብር (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና ለሎት ሁለት 100,000.00 ብር (አንድ መቶ ሺህ ብር) ሕጋዊ ከሆነ ባንክ የተረጋገጠ CPO ከሚያቀርቧቸው ሰነዶች ጋር ማያያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የዕቃዎቹን ዝርዝር በየዕቃው ምድብ አይነት (LOT) የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት ወሊሶ ከተማ የቢሮ ቁጥር 16 እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዋጋ ሰነድ አንድ ኦሪጅናል እና አንድ ኮፒ እስፔስፊኬሽኑ (Specification) ሳይቀየር ለየብቻው በታሸገ ኤንቨሎፕ ከላይ በተራ ቁጥር 7 በተጠቀሰው አድራሻ ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ እስከ ነሐሴ 12 ቀን 2017 ዓ.ም 5፡30 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ነሐሴ 12 ቀን 2017 ዓ.ም 6፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተራ ቁጥር 7 በተገለፀው ቦታ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዕቃዎች በተቀመጠው እስፔስፊኬሽን እና ካታሎግ መሰረት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ከተቀመጠው መስፈርት በታች ያቀረበ ተወዳዳሪ ከውድድር ውጪ ይሆናል፡፡
- አሸናፊው ባሸነፈባቸው ጠቅላላ እቃዎች ላይ 10% /አሥር በመቶ/ የውል ማስከበሪያ በሕጋዊ ባንክ የተረጋገጠ CPO በማስያዝ ማሸነፉ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ በ10 ቀናት ውስጥ በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት በመገኘት ውል መፈረም ይኖርበታል፡፡
- ከላይ በተራ ቁጥር 11 ላይ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ውል የማይፈፅም አሸናፊ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለመንግስት ገቢ የሚደረግ ሆኖ ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ መጠቀም ይችላል፡፡
- አሸናፊው ውል ፈርሞ በውል ስምምነቱ መሰረት ከላይ በተገለፀው አድራሻ በራሱ መጓጓዣ እቃዎቹን አቅርቦ ማስረከብ እና ገጠማ የሚያስፈልጋቸውን ዕቃዎች ማስገጠም ይኖርበታል፡፡
- በጨረታው ውል መሠረት እቃዎቹን በሙሉ ካስረከበ ክፍያው ወዲያው ይፈፀማል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ:- 011-3-66-46-34 / 011-3-41-14-01
የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት
