በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በኢሉባቦር ዞን ያዮ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በወረዳው ለሚገኙ መሥሪያ ቤቶች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በኢሉባቦር ዞን ያዮ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በወረዳው ለሚገኙ መሥሪያ ቤቶች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
-
የፅህፈት መሣሪያ
-
የሞተር ሳይክል
-
የሠራተኛ ደንብ ልብስ
-
የተለያዩ ጎማዎች ከእነ ከለመዳሪ
-
የቢሮ ቋሚ ዕቃዎች / Furniture/
-
የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች
ከዚህ በታች የተዘረዘረውን መስፈርት የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
-
በስራው ዘርፍ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ እና የ2017 ግብር ከፍሎ ፍቃዱን አሳድሶ ያጠናቀቀ፡፡
-
የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያለው፡የቫት/ ወይም ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ ፡፡
-
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚመለሰ 30,000 (ሰላሳ ሺህ) ብር በሲፒኦ (Cpo )ለእያንዳንዱ ዶክመንት ማስያዝ የሚችል
-
የጨረታውን ዝርዝር መግልጫ ሰነድ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ባሉት 15 (አስራ አምስት) የሥራ ቀናት የማይመለስ 500 (አምት መቶ) ብር በመከፈል ከያዮ ወረዳ ገ/ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ ቤት መውሰድ ይችላሉ፡፡
-
የሚወዳደሩበት ሰነድ ስርዝ ድልዝ የሌለው እና የሚነበብ መሆን አለበት ስርዝ ድልዝ ካለው ውድቅ ይሆናል፡፡ ተወዳዳሪዎች ዋጋን የሚገልፅ ሰነድ ኦርጂናል እና ኮፒውን ለየብቻ ፍቃድ እና የተለያዩ ተፈላጊ ሰነዶችን አያይዞ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
-
የጨረታ አሸናፊ የሆኑ ድርጅቶች ሆነው የተመረጡ የጨረታው ውጤት በደብዳቤ ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በአስር ቀናት ውስጥ በመቅረብ ያሸነፉበትን ዋጋ 10 % ለመልካም ሥራ አፈፃፀም ዋስትና በማስያዝ ውል መፈረም አለባቸው፡፡
-
ጨረታው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ 60 (ስልሳ )ቀናት ይሆናል፡፡
-
ተጫራቾች የዕቃ ዝርዝር ጨረታ መወዳደሪያ በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ቫት ጨምሮ ወይም ያለቫት በማለት በመጨረሻው ገጽ ላይ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል መስሪያቤቱ የዕቃውን ብዛት 20% ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል ፡፡
-
የሰራተኛ ደንብ ልብስ ለማቅረብ የሚወዳደሩ ተወዳዳሪዎች የእቃውን ናሙና ከጨረታው ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
-
የፈርኒቸር ዕቃዎች ላይ የምትወዳደሩ ድርጅቶች እስከ መግጠም ድረስ ይሆናል፡፡
-
በራሱ ወጪ ወይም ትራንስፖርት እስከ ያዮ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት አቅርቦ ማስረከብ አለበት፡፡
-
ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነድ ዘወትር በሥራ ሰዓት ዋጋ በመሙላት ለጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን በያዮ ወረዳ ገንዘብ ት/ጽ/ቤት እስከ በ15ኛው ቀን እስከ11፡30 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
-
ጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ቆይቶ በ16ኛ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተጠናቆ በዚያው ቀን 4፡30 ሰዓት ላይ ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታ ፡፡
-
ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡ጨረታው በሚከፈትበት ዕለት በዓል ከሆነ ወደ ሚቀጥለው የሥራ ቀን ተላልፎ ጨረታው ይከፈታል፡፡
-
መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0913353270/0964708848
በኢሉአባቦር ዞን የያዮ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
