ሕዳሴ ቴሌኮም አክሲዮን ማህበር የተለያዩ ያገለገሉ ዕቃዎች ባሉበት ሁኔታ ለሕጋዊ ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ያገለገሉ ዕቃዎች ሽያጭ ግልጽ ጨረታ
የጨረታ ቁጥር LT/HT/HO/07/2025
ሕዳሴ ቴሌኮም አ.ማ
ሕዳሴ ቴሌኮም አክሲዮን ማህበር የተለያዩ ያገለገሉ ዕቃዎች ማለትም፣
- ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች
- የጣውላ እንጨቶች (የተሰባበሩ ጠረጴዛዎች እና ወንበሮች)
- ያገለገሉ የተሽከርካሪ ጎማዎች፤
- ያገለገሉ የብረት ካዝና ባሉበት ሁኔታ ለሕጋዊ ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ለመግዛት በሚመጡበት ወቅት የንግድ ድርጅት ከሆኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃዳቸውን ዋናው እና ቅጅ፣ ግለሰብ ከሆኑ የታደስ የቀበሌ መታወቂያ ወይም የመንጃ ፍቃድ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል።
ለጨረታ የቀረቡት ዕቃዎች የሚገኙበት ቦታ የሕዳሴ ቴሌኮም በቅሎ ቤት ቴሌ ጋራዥ ውስጥ በሚገኘው የሕዳሴ ቴሌኮም ዕቃ ግምጃ ቤት ነው።
- ተጫራቾች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ከነሐሴ 07 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ጠዋት ከ2:30 - 6:00 ከሰዓት ከ7:30-10:00 ከቤተሳይዳ ሕንጻ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 306 የማይመለስ ብር 200.00 በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ውጤቱ እንደታወቀ የሚመለስ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 15,000 (አስራ አምስት ሺህ ብር) የባንክ ክፍያ ማዘዣ /C.P.O/ ለሕዳሴ ቴሌኮም አ.ማ በሚል ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
- ተጫራቾች ያገለገሉ ዕቃዎችን የሚገዙበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ ሙሉ አድራሻውን እና የጨረታውን ቁጥር በመጥቀስ ቤተሳይዳ ሕንጻ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 306 ነሐሴ 16 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት የሚዘጋ ሆኖ በዕለቱ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ በ4፡30 ሰዓት ቤተሳይዳ ሕንጻ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 306 ይከፈታል።
- ተጫራቾች በጨረታው በከፊል መጫረት የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
- አክሲዮን ማህበሩ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 096825111/0912036524 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
ሕዳሴ ቴሌኮም አክሲዮን ማህበር
