በቡኖ በደሌ ዞን የገቺ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 ዓ/ም በጀት ዓመት በወረዳችን ላሉት 1 ሴክተር መ/ቤቶች የሚውሉ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር:- 1/2018
በቡኖ በደሌ ዞን የገቺ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 ዓ/ም በጀት ዓመት በወረዳችን ላሉት 1 ሴክተር መ/ቤቶች የሚውሉ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ 1. የአላቂ ዕቃዎች እና እስቴሽነሪዎች 2. የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች 3. የሰራተኞች የደንብ ልብስ 4. ሞተር ሳይክሎች 5. የፈርኒቸር ዕቃዎች 6. የመኪና እና ሞተር ሳይከል ጎማዎች 7. የግንባታ ዕቃዎች ማቅረብ የሚችል፡፡ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶችን ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
-
ሕጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
-
ተወዳዳሪዎች በአከባቢያቸው ከሚገኘው የገቢዎች ባለሥልጣን ጽ/ቤት የ2017 የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚገልጽ የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ ፡፡
-
በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ተመዝጋቢ መሆናቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
-
ማንኛውም ተወዳዳሪ ለእያንዳንዱ ሰነድ 10,000 ( አስር ሺህ ) በአቅራቢያችን ከሚገኝ ባንክ የተመሰከረ CPO ከጨረታው ሰነድ ግዥ ጋር አያይዞ ማቅረብ ይኖርበታል ፡፡
-
አሸናፊ ተጫራቾች የውል ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋን 10% በባንክ በተመሰከረ CPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
-
አሸናፊ ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሰነድ ያስያዙትን CPO ያሸነፉበት የዕቃ ሰነድ ሙሉ በሙሉ ካላቀረቡ ያስያዙት CPO የማይመለስ ይሆናል፡፡
-
ጨረታው ጸንቶ የሚቆይበት ጊዜ 90 (እስከ ኅዳር 30/2018 )ቀናት ይሆናል፡፡
-
ዕቃውን ማስረከቢያ ቦታ ገቺ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ሆኖ ጠቅላላ ወጪ የሻጩ ግዴታዎች ናቸው፡፡
-
አሸናፊ ደርጅት ጥራት የሌላቸውና ያልተጠየቁ እቃዎችን ካቀረቡ ተቀባይነት የለውም፡፡
-
በሌላ ተጫራቾች ላይ ተንተርሶ ዋጋን ማቅረብ አይቻልም ፡፡
-
የዕቃው ብዛት 20% ሊቀንስም ሊጨምርም ይችላል፡፡
-
አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈባቸውን እቃዎች ናሙና ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
-
ተወዳዳሪው የእቃውን ዋጋ ሲሞላ ቫት ጨምሮ መሙላት አለበት ፡፡ ካልሞላ ግን ቫት እንደተጨመረ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡
-
በደንብ ልብስ ላይ የሚወዳደሩ ተጫራቾች ሰነዱን ሲያስገቡ የእቃዎችን ናሙና ማቅረብ አለባቸው፡፡
-
ፈርኒቸር እቃዎች ተወዳድረው ያሸነፉ ተጫራቾች እቃውን ገጣጥመው ማስረከብ አለባቸው፡፡
-
አሸናፊ ድርጅት በእያንዳንዱ ሴክተር መ/ቤት ደረሰኝ መስጠት አለበት ፡፡
-
ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ሲያቀርቡ ቴክኒኩን ኦርጅናል እና ኮፒውን በተለያዩ ፖስታ እንዲሁም የፋይናንስ ዋጋ ኦርጅናል እና ኮፒውን በተለያዩ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው፡፡
-
ተጫራቾች የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ለተከታታይ ለı5 የሥራ ቀናት 7/12/2017 ዓ.ም እስከ 28/12/2017 ዓ.ም አየር ላይ የሚቆይ ሲሆን፤ የጨረታውን ሰነድ ከገቺ ወረዳ ገቢዎች ባለሥልጣን ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 7 የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) ብቻ በመግዛት ዋጋቻውን ሰነዳቸው በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ በወረዳው ገ/ጽ/ቤት በቢሮ ቁጥር 7 ማስገባት ይችላሉ፡፡
-
ጨረታው በ15ኛው የሥራ ቀናት 8፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥን ተዘግቶ በዚሁ ቀን 8፡ 30 ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው _ ባይገኙም _ ጨረታውን አያስተጓጉልም፡፡
-
መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው፡፡
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፦ 0473400475/0913518638 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ።
በቡኖ በደሌ ዞን የገቺ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
