Tender Detail

Tender Details


የኮልፌ ቀራኒዮ ከ/ከተማ ወረዳ 07 ፋይናንስ ጽ/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መመሪያዎች እያንዳንዱ ተጫራች እንዲያከብር ይጠይቃል።


የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 001/2018

የኮልፌ ቀራኒዮ ከ/ከተማ ወረዳ 07 ፋይናንስ ጽ/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መመሪያዎች እያንዳንዱ ተጫራች እንዲያከብር ይጠይቃል።

1. ከላይ በርዕሱ ለመጥቀስ እንደተሞከረው በኮልፌ ቀራኒዮ ከ/ ከተማ ወ/7 አስተዳደር ፋ/ጽቤት በ2018 በጀት ዓመት ገኛ ዙር ግልጽ ጨረታ ሎት1/ ደንብ ልብሶች ሎት/2 የጽዳት እቃዎች ሎት/3 አላቂ የቢሮ እቃዎች ሎት/4 ልዩ ልዩ እታዎች ሎት/5 የኤልክትሮኒከስ ጥገና ሎት/6 የትራንስፖርት እና የጭነት አገልግሎት ሎት 7 የህትመት ስራ ሎት 8 መስተንግዶ አገልግሎት ሎት 9 የዲኮር እና የድንኳን ኪራይ ሎት10/ የፈርኒቸር ጥገና ሎት 11/ቋሚ እቃዎች ሎት 12 የጉልበት ስራ አወዳድሮ ለመግዛትና ለማሰራት ይፈልጋል። ተጫራቾች በዚሁ መሰረት ከዚህ በታች የተጠቀሰውን መስፈርት የሚያሟሉ ድርጅቶችና ግለሰቦች በጨረታው እንድሳተፉ ይጋብዛል።

2 የሚወዳደሩ ተወዳዳሪዎች በመስኩ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና በአቅራቢነት መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ቲን (TIN) ሰርትፍኬት ኮፒውን ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችል ይሆናል። ተጫራቶች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ለእያንዳንዱ የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ/ ብር ብቻ በመክፈል የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት ከፋይናንስ ጽ/ቤት መግዛት ይችላሉ።

3. ተጫራቾች በቅዲሚያ በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ(CPO) የሚጫረቱበት ሎት የደንበ ልብሶች ግዢ ብር 18,000 ሎት/2 የጽዳት እታዎች 24,500 ሎት/3 አላቂ የቢሮ እቃዎች 28,000 ሎት/4 ልዩ ልዩ እቃዎች 17,500 ሎት/5 የኤልክትሮኒከስ ጥገና 1,400 ሎት/6 የትራንስፖርት አና የጭነት አገልግሎት 12,000 ሎት/7 የህትመት ስራ 4.600ሎት/8 የመስተንግዶ አገልግሎት1,800 ሎት/9የዲኮር እና የድንኳን ኪራይ 10,000 ሎት/10 የፈርኒቸር ጥገና 1,400 ሎት11 ቋሚ እቃች 35,000 ሎት 12 /የጉልበት ስራ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

4. የመጫረቻ ሰነዱ በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦርጅናልና ኮፒ በመለየት እና ለየብቻ በማሸግ ከጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት በፊት የጨረታ ማስገቢያ ቦታ ኮ/ቀ/ክ/ከ/ወ/07 ፋ/ጽ/ቤት 3ኛ ፎቅ ለዚህ ተበሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው።

5. ጨረታው በ11 ኛው ቀን ላይ ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ታሽጎ በዚያው እለት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በፋ/ጽ/ቤት 3ኛ ፎቅ ይከፈታል። ይህ ቀን የበዓል ቀን ወይም የአረፍት ቀን ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን ይከፈታል።

6. በግዥ አዋጁ መሰረት ለጥቃቅንና አነስተኛ ልማት ልዩ አስተያየት የሚደረግ ሲሆን በጥቃቅንና አነስተኛ ስለመደራጀታቸው የሚገልፅ ከአደራጃቸው ተቋም በጽ/ቤቱ ሃላፊ የተረጋገጠ የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርበታል።

7. የአንዱ ዋጋ የማይለወጥ በመሆኑ ተጫራቾች በትከከል መሙላት ይጠበቅባቸዋል። እንዲሁም የዕቃው ጥራትና ዋጋ ከግምት በማስገባት እንዲሞሉ እንገልጻለን።

8. የትራንስፖርት አገልግሎት አቅራቢው ወረዳው እስቶር (ዕቃ ግምጃ ቤት) ድረስ አምጥቶ የሚያስረክብ መሆኑን ከግንዛቤ ውስጥ እንድታስገቡ።

9. የዕቃውን 20 ፐርሰንት መጨመር ወይም መቀነስ መ/ቤቱ የሚችል መሆኑን እና ጠቅላላ ዋጋውን 25 ፐርሰንት ለ6ወር ድረስ ጨምሮ ሊያዝ የሚችል መሆኑን።

10. ተጫራቹ ለተወዳደሩባቸው ሎቶች ሳምፕል(ናሙና) ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

11. ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ማሳሰቢያ፦ የጉልበት ለሚወዳደሩት በስራ እድል ፈጠራ የተደራጁ ቢሆን ደብዳቤ እና የቲን ቁጥር ብቻ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

አድራሻ፡-ኮ/ቀ/ከ/ከ/ወ/ 07 ቤቴል እሳት አደጋ ሬት ሰፌት በ40 ሜትሩ መንገድ በኩል ነው። ሰበስm መረጃ የስልክ ቁጥር 0113696634 ደደmሱ።

የኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ወረዳ 07 ፋይናንስ ጽ/ቤት

Save Tender