በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በወላይታ ዞን የባይራ ኮይሻ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በመደበኛ በጀት 2018 በጀት ዓመት በፑል ለታቀፉ ሴር መ/ቤቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድረን ግዥ ለመፈፀም እንፈልጋለን።
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በወላይታ ዞን የባይራ ኮይሻ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በመደበኛ በጀት 2018 በጀት ዓመት በፑል ለታቀፉ ሴር መ/ቤቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድረን ግዥ ለመፈፀም እንፈልጋለን።
ሎት 01 ጽሕፈት መሳሪያና አላቂ የቢሮ ዕቃዎች 15,000 /አስራ አምስት ሺህ/
ሎት 02 የመኪና ሞተር ሳይክል ጎማ ሎት 30,000 /ሠላሳ ሺህ ብር/
ሎት 03 የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች 50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር/
- ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ ያሳደሱ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያላቸው፣ ለመንግስት 3% ለመክፈል ፈቃደኛ የሆኑ እና ከሚመለከተው ክፍል የተሰጠ ታክስ ከሊራንስ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችሉ፣
- በፌዴራል ግዥና የመንግስት ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአቅራቢነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚገልጽ መረጃ የያዙ መሆናቸው፣
- ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታውን ሠነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ለሰነዱ በየሎት የማይመለስ 300 /ሶስት መቶ ብር ብቻ/ ወደ ባይራ ኮይሻ ወረዳ ገቢዎች ባለሥልጣን ቅ/ጽ/ቤት ሄደው ሂሳቡን በመክፈል ከባይራ ኮይሻ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ከግዥና ንብረት አስ/ር ቢሮ ቁጥር-7 ሰነድ መውሰድ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያውን ሰነድ ኦርጅናሉንና ሁለት የኦርጅናሉን ፎቶ ኮፒ ለየብቻው በታሸገ ኤንቨሎፕ ፖስታ ሙሉ አድራሻቸውን በመጥቀስ በባኮ/ወፋ/ጽ/ቤት ለጨረታው በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ መክተት ይኖርባቸዋል፣
- የጨረታው ሳጥን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ለ15 የሥራ ቀናት ቀጥሎ በሚውለው በ16ኛ በሥራ ቀን ከጧቱ በ4፡30 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 5፡00 ላይ በባ/ኮ/ወ/ፋ ጽ/ቤት በግዥና ንብረት አ/ር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 7 የሚከፈት መሆኑን።
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት የነጠላ ዋጋ ላይ የማይነበብና ስርዝ ድልዝ ያለበትን ሰነድ ከሆነ ተቀባይነት የለውም።
- አሸናፊ ድርጅት ውል ከመፈረሙ በፊት የሚገዙ እዕቃዎች ናሙና በድርጅቱ ማህተም አስደግፈው ማቅረብ የሚችሉ፣
- አሸናፊው ተጫራች ውል ማስከበሪያ 10% ማስከበሪያ በባንክ የተመሰከረለት የጥሬ ብር/ሲፒኦ/ ከታወቀባንክ የተረጋገጠ የተመሰከረለት የጥሬ ብር /ሲፒኦ/ ለየብቻ ለማስያዝ ፍቃደኛ የሆነ መሆናቸው፣
- ተጫራች የሚያቀርቡት ነጠላ ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስ/VAT/TOT የሚጨምር ወይም የማይጨመር መሆኑን ተለይቶ ሊቀመጥ ይገባዋል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ መሆኑን።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 56 445 021/09 16 414 097 ደውለው ማነጋገር ይችላሉ።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በወላይታ ዞን የባይራ ኮይሻ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
