የዴራ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 የበጀት ዓመት በከተማው ውስጥ ለሚገኙ ሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የጽህፈት መሣሪያዎች፣ የቢሮ ውስጥ ልዩ ልዩ አላቂ ዕቃዎች፣ የጽዳት ዕቃዎች እና የሰራተኞች ደንብ ልብስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡- 01/2017
የዴራ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 የበጀት ዓመት በከተማው ውስጥ ለሚገኙ ሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የጽህፈት መሣሪያዎች፣ የቢሮ ውስጥ ልዩ ልዩ አላቂ ዕቃዎች፣ የጽዳት ዕቃዎች እና የሰራተኞች ደንብ ልብስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም፡-
- ለተጠየቁት የግዢ እቃዎች ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ከፍለው የንግድ ፈቃዳቸውን ያሳደሱ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ፤ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (Tax payer Registration number) ያላቸው እና በፌዴራል፣ በክልል ወይም በዞን ገንዘብ ጽ/ቤት ወይም በግዢዎችና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ያላቸው ዋናውና ኮፒውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች ለቋሚ የቢሮ ዕቃዎች፣ ለኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ለጽሕፈት መሣሪያዎች፣ ለጽዳት እቃዎች እና ለሠራተኞች የደንብ ልብስ ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በጽሕፈት ቤቱ የሲንቄ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1071392621217 ገቢ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት እለት ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት የጽሕፈት ቤቱ የግዢና ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 4 ድረስ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ በመሙላት በዝግ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ 15ኛው የሥራ ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት በ4:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጽ/ቤቱ የግዢና ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 44 ይከፈታል።
- እለቱ የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተራ ቁጥር 3 በተጠቀሰው መሰረት ጨረታው ይከፈታል።
- ማንኛውም ተጫራች ለእያንደንዱ ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5,000 (አምስት ሺህ) በአቅራቢያችሁ በሚገኝ የታወቀ ባንክ በክፍያ ማዘዣ (CPO) ብቻ ማቅረብ ይኖርባችኋል።
- አሸናፊው ተጫራች ያለ ምንም የአቅርቦት ችግር አስተማማኝ አስፈላጊ የሆነ የዕቃ ክምችት ያለውና ዕቃዎቹን በራሱ የማጓጓዣ ወጪ ዴራ ከተማ ውስጥ በሚገኘው የከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ አምጥቶ ማስረከብ ይኖርበታል።
- ማንኛውም ተጫራች እስክርቢቶዎች፣ ፕሪንተር ቀለምዎች እና ደንብ ልብስ ላይ የሚወዳደር ለሚወዳደሩበት እቃ ናሙና (ሳምፕል) ማቅረብ አለበት።
- ተጫራቹ አሸናፊ ከሆነ ላሸነፈበት ዕቃ ከመስሪያ ቤቱ ጋር ውል መግባት ይጠበቅበታል። ለውል ማስከበሪያ ያሸነፈበትን ዕቃ ዋጋ 10% በካሽ ወይም በCPO ማስያዝ ይጠበቅበታል፡፡
አድራሻ፡- ዴራ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት አርሲ ዴራ ከአዳማ በአሰሳ መስመር 25 ኪ.ሜ
ተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡- 09-12-26-33-11/ 09-62-11-94-47/ 09-82-51-74-09 ደውለው ይጠይቁ።
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በአርሲ ዞን የዴራ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት
