Tender Detail

Tender Details


የጨረታ ማስታወቂ በአርሲ ዞን የስርካ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 የበጀት ዓመት በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ ጽ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የጽሕፈት መሳሪያዎች የጽዳት እቃዎች፣ ትናንሽ ቋሚ እቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ፣ የቢሮ እቃዎች (ፈርኒቸሮች)፣ የሠራተኞች የደንብ ልብስ እና የመኪና ጎማ በግልፅ ጨረታ እወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡


የጨረታ ማስታወቂ

በአርሲ ዞን የስርካ ወረዳ ገንዘብ /ቤት 2018 የበጀት ዓመት በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ /ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የጽሕፈት መሳሪያዎች የጽዳት እቃዎች፣ ትናንሽ ቋሚ እቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ፣ የቢሮ እቃዎች (ፈርኒቸሮች) የሠራተኞች የደንብ ልብስ እና የመኪና ጎማ በግልፅ ጨረታ እወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች እንዲወዳደሩ ይጋብዛል።

1. ለተጠየቁት የግዢ እቃዎች የንግድ ፊቃድ መስጫ መደብ ኮድ /"licensing category code"/ሕጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር ከፍለው የንግድ ፈቃዳቸውን ያሳደሱ፤ የግብርከፋይነት መለያ ቁጥር (Tax registration No.) የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና በፌዴራል በክልል በዞን ገንዘብ /ቤት ወይም በግዢዎችና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ያላቸው ዋናውንና ኮፒውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

2. ተጫራቾች ከግብር ሰብሳቢው /ቤት የዘመኑን ግብር አጠናቀው ለመከፈላቸው እና ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን ደብዳቤ ከግብር ሰብሳቢውው /ቤት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤

3. ተጫራቾች ለጽሕፈት መሳሪያዎች፣ የኤሌክትሮኒከስ እቃዎች፣ የቢሮ ፈርኒቸሮች፣የመኪና ጎማና የሠራተኞች የደንብ ልብስ ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ) ለትናንሽ ቋሚ እቃዎችና ለጽዳት እቃዎች፤ 300 (ሦስት መቶ)ብር በስርካ ወረዳ ገንዘብ /ቤት ስም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሂሳብ ቁጥር 1000065220133 ገቢ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ 15ኛው ተከታታይ የሥራ ቀናት ድረስ በጽ/ቤቱ የግዢና የንብረት አስተዳዳር የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 7 ድረስ በመቅረብ ብሩን ገቢ ያደረጉበትን የባንክ ስሊፕ አድቫይስ/እና ሕጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ኮፒውን ይዞ በመምጣት ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡

4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ 15ኛው የሥራ ቀናት በመሙላት በተለያዩ ፖስታዎች በኦርጅናልና በኮፒ በማዘጋጀት ከጨረታው መዝጊያ ሰዓት በፊት ማቅረብ አለባቸው፡፡

5. የተጫራቾች ሙሉ ስም፣ ፊርማ፣ የድርጅቱ ማህተምና አድራሻ የሌለው ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡

6. የጥቃቅንና አነስተኛ ማይክሮ ኢንተርፕራይዞች ለዚህ የጨረታ ሰነድ ማስከበሪያ እንደዋስትና የሚያገለግል ከጥቃቅንና አነስተኛ ልማት ሥራዎች /ቤት ብቻ የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ ይችላሉ፡፡

7. አሸናፊው ተጫራች የእቃዎቹ ናሙና ቀርቦ እንዲታይ ከተፈለገ የተፈለገውን ዕቃ ለማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡

8. ተጫራቾች የእቃዎቹን ዋጋ ከዚህ ሰነድ ውጪ በሌላ ዋጋ መስጫ ላይ ሞልተው መመለስ አይችሉም፡፡

 

9. ተጫራቾች የሃገሪቱን የፌዴራልና የክልሉን የግዥ አዋጆች ደንቦችንና መመሪያዎችን የማከበርና ከማንኛውም የሙስና ድርጊቶች ነፃ የሆኑ እንዲሁም፣ በእቃ አቅርቦት ወቅት ከዚህ ሰነድ ጋርየተያያዘውን የውል ሰነድ መፈረም ይኖርባቸዋል፡፡

10. አሸናፊ ተጫራቾች ለያንዳንዱ እቃ የሰጡት ነጠላ ዋጋ እስከ መጋቢት 30/2018 .. ድረስ ፀንቶ የሚቆይ መሆኑን አውቀው /ቤቱ ተጨማሪ የግዢ ጥያቄ ፍላጎት ባቀረበበት ወቅት ለማቅረብ ፍላጎት ያላቸውና ውል መፈፀም የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል::

11. አሸናፊ ተጫራች ጽ/ቤቱ ከሚያደርገው የግዢ ውል 20% ጨምሮ ወይም ቀንሶ መግዛት የሚችል መሆኑን ማወቅ ይኖርበታል፡፡

12. ተጫራቾች የሠራተኞች የደንብ ልብስ ዓይነቶችን (ብትን ጨርቅ፤ የተዘጋጀ ልብስና ጫማዎችን) ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ናሙና ማቅረብ አለባቸው፡፡

13. ማንኛውም ተጫራች የጽሕፈት መሳሪያዎች፣ የኤሌክትሮኒከስ እቃዎች፣ የቢሮ ፈርኒቸሮች፣ የመኪና ጎማና የሠራተኞች የደንብ ልብስ ለእያንዳንዱ ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) ብር30,000.00 (ሠላሳ ሺህ) የጽዳት እቃዎችና ትናንሽ ቋሚ እቃዎች 15,000 (አስራ አምስት ሺህ) ብርበአቅራቢያችሁ በሚገኝ የታወቀ በባንከ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ ወይም ሲ.ፒ.ኦ. (C.P.O.) በስርካ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ስም በማሠራት ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ ተጫራቾች ሲ.ፒ.ኦ. (CPO)ውን ለብቻ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው፡፡

14. አሸናፊ ተጫራች ለውል ማስከበሪያ ያስያዘው የገንዘብ መጠን እስከ ሦስት ወር የጊዜ ገደብ ድረስ ገቢ ያደረጋቸው ዕቃዎች ለተጠቃሚው መ/ቤት ደርሰው የብቃት ደረጃቸው ትክክለኛነት እስኪረጋገጥ ድረስ የማይመለስ መሆኑን ማወቅ ይኖርበታል፡፡

15. ተጫራቾች በማንኛውም ሁኔታ የጨረታውን አካሄድ ሥነ-ሥርዓት ለማስቀየርም ሆነ ለማሳሳት ከሞከሩ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ተደርጎ ወደፊት በሚወጣ የጨረታ ማስታወቂያ ላይ እንዳይሳተፉ ይደረጋል፡፡

16. ተጫራቾች ለሚያቀርባቸው የእቃ ዋጋዎች (የመወዳደሪያ ሃሳቦች) የተጨማሪ እሴት ታከስ ማካተቱንና ኣለማካተቱን በግልጽ መግለጽ ይኖርባቸዋል:: ይህ ያልተገለጸ ከሆነ፤ የተሰጠው ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታከስን እንዳካተተ ይወሰዳል፡፡

17. አሸናፊው ተጫራች ያለምንም የአቅርቦት ችግር አስተማማኝ የሆነ የዕቃ ከምችት ያለውና እቃዎቹን በራሱ ወጪ በማጓጓዝ የታዘዘውን ዕቃ በአንድ ላይ ስርካ ወረዳ ጎቤሳ ከተማ ውስጥ በሚገኘው የወረዳው ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ አምጥቶ ማስረከብ ይኖርበታል፡፡

18. ጽ/ቤቱ ተጫራቾችን ሲያጫርት ለጨረታው ቅድመ ግምገማ ከዚህ በላይ የተጠቀሱትን የተጫራቾች መመሪያ መሠረት በማድረግ ለቀረቡት የዕቃ የቴከኒከ ዝርዝር መግለጫ የዕቃዎቹን ጥራትና ብቃት በማረጋገጥ ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበ ድርጅት አሸናፊ ይሆናል፡፡

19. በጨረታው ማስታወቂያ ውስጥ ያልተገለጹ መመሪያዎች ካሉ ሥራ ላይ ባሉት የመንግስት የግዥ አዋጆች ደንቦችንና መመሪያዎች መሠረት የሚፈጸሙ ይሆናሉ፡፡

20. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ በ15ኛው ተከታታይ የሥራ ቀን ጠዋት 5፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ጠዋት በ5፡30 ሰዓት ጽ/ቤቱ ውስጥ ለአመቺነቱ በተመረጠው ቦታ ይከፈታል፡፡ ዕለቱ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ ጨረታው በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ የሚከፈት ይሆናል፡፡

21. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡- (022 446 0311) (022 446 0086) ይጠይቁ::

በአርሲ ዞን የስርካ ወረዳ ገንዘብ/ ጽ/ቤት

 

Save Tender