የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ፐብሊከ ሰርቪስና ሰው ሃብት ልማት ፑል አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 የበጀት ዓመት የተለያዩ ሎቶች ላይ ህጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር 001/2018
የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ፐብሊከ ሰርቪስና ሰው ሃብት ልማት ፑል አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 የበጀት ዓመት የተለያዩ ሎቶች ላይ ህጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሰረት፤
ሎት 1፡- የመኪና ጎማና ባትሪ
ሎት 2፡- የህትመት ስራዎች
ሎት 3፡- የዲኮር እና መድረክ ዝግጅት
ሎት 4፡- የመኪና ኪራይ
ሎት 5:- የጉልበት ስራ
ሎት 6፡- የከባድ መኪና ጥገና
ሎት 7፡- የከባድ መኪና ጎማ ጥገና (ጎሚስታ)
ሎት 8:- የከባድ መኪና እጥበት
ሎት 9:- ኮምፒውተርና ፎቶ ኮፒ ጥገና
ሎት 10፡- የመስተንግዶ አገልግሎት
ሎት 11፡- መኪና ጥገና /የቢሮ/
ሎት 12፡- የምድረ ግቢ ጽዳት አገልግሎት
በጨረታ መሳተፍ የሚፈልጉ ማንኛውም ህጋዊ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርት አሟልተው በጨረታው መወዳደር ይችላል፡፡
- የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድና የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት እና ክሪላንስ ማቅረብ የሚችሉ እንዲሁም አቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተካተቱ መሆን ይኖርባቸዋል ፣
- ከወጣው ጨረታ ውስጥ ብር 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ በላይ ዋጋ በማቅረብ በጨረታው የሚሳተፍ ማንኛውም የአገር ውስጥ ተጫራች የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ወረቀት ኮፒ ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታ ሰነዱን በስራ ሰዓት ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ፐብሊከ ሰርቪስና ሰው ሃብት ልማት ፑል የአስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን 7ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 705 ተጫራች የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የስራ ቀናት ውስጥ ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነዱ ቴክኒካል ዋናውን አንድ (1) እና ፎቶ ኮፒ አንድ (1) ፣ ፋይናሽያል ሰነድ ዋናውን አንድ (1) እና ፎቶ ኮፒ አንድ (1) ለየብቻ በፖስታ ታሽጎ በድምሩ 4 (አራት) ፖስታ በአንድ ተጠቃሎ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ኦርጅናል፣ ኮፒ ቴክኒካል እና ፋይናንሻል በሚል በፖስታው ላይ በግልጽ በመጻፍ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ኮ/ቀ/ክ/ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን 7ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 705 ማስገባት ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሎት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሎት 1 100,000 /አንድ መቶ ሺ ብር/፤ ሎት 6 እና 11 20,000 /ሃያ ሺ ብር/፣ ከሎት 2፣3፣4፣5፣9፣ እና 10 10,000 /አስር ሺ ብር/ ሎት 7 እና 8 5,000 /አምስት ሺ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ብቻ በኮ/ቀ/ክ/ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ፑል አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት በሚል በማዘጋጀት ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች በስራ ኢንተርፕራይዝ እና እንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት የተደራጁ ከሆነ ከተደራጁበት ተቋም የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ አለባችሁ፡፡
- ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጥዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚያው ቀን ጥዋት 4፡30 የሚከፈት ሲሆን ነገር ግን 11ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች ሎት 1 የመኪና ጎማና ባትሪ እና በሎት ሎት 2 የህትመት ስራዎች ላይ የሚጫረቱ የዕቃ ናሙና /sample/ የጨረታ ጊዜው ሳያልቅ የማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የሚያቀርበው ጨረታ ሰነድ ስርዝ ድልዝ ኖሮት ካልተፈረመ፣ ፍሉድ ተጠቅሞ በጉልህ የማይነበብ ከሆነ ከውድድር ወጪ ይሆናሉ፡፡
- መ/ቤቱ ከአሸናፊው ተጫራች ውል ከመፈረሙ በፊት በአሸናፊ ተጫራች አቅርቦት መጠን ላይ የተገኘው ዋጋ ሳይቀየር እስከ 20% መጨመር ወይም የመቀነስ የሚችል ይሆናል ፡፡
- የጨረታውን አካሄድ ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታው ውጪ እንደሚሆኑ፤ ለወደፊትም በመንግስት ግዥ እንዳይሳተፉ እና ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና እንደሚወረስ ማወቅ አለባቸው።
አድራሻ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍስ ከተማ ህንጻ 7ኛ ፎቅ ቢ/ቁ 705 የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን
አድራሻ፡- ቤቴል አደባባይ ወረድ ብሎ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አጠገብ
ስልክ ቁጥር 0118340591
የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ፑል አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት
