Tender Detail

Tender Details


በልደታ ክፍለ ከተማ የወረዳ 08 ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት የአንደኛ ዙር ግልጽ ጨረታ አላቂ የቢሮ እቃዎች የደንብ ልብስ፣ የጽዳት እቃዎች የቋሚ አላቂ እቃዎች፣ ቋሚ እቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ የአገልግሎት ግዥዎችን አቅራቢዎችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡


የአንደኛ ዙር ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 001/2018

በልደታ ክፍለ ከተማ የወረዳ 08 ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት የአንደኛ ዙር ግልጽ ጨረታ አላቂ የቢሮ እቃዎች የደንብ ልብስ፣ የጽዳት እቃዎች የቋሚ አላቂ እቃዎች፣ ቋሚ እቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ የአገልግሎት ግዥዎችን አቅራቢዎችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚህ መሰረት

1. ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆኑን አግባብ ያለው የታደሰ ንግድ ፈቃድ እና ከግዥ ኤጀንሲ በእቃ አቅራቢነት በኦን ላይን የተመዘገቡበትን ምስክር ወረቀት እና የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ መረጃ ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማስገባት ይኖርባቸዋል።

2. ተጫራቾች ከጨረታ መዝጊያ ቀን እና ሰዓት ቀደም ብለው ናሙና የሚያስፈልጋቸው እቃዎችን እንዲሁም የፎቶ ናሙና የሚያስፈልጋቸው እቃዎች በፎቶ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የሚታሰብ 10/አስር/የስራ ቀናት ውስጥ የማይመለስ 500/አምስት መቶ ብር/በመከፈል ሰነዱን መግዛት ይኖርባቸዋል።

3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንከ የተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ ማስያዝ የሚቻል ሲሆን ለሎት /አ/ አላቂ የቢሮ እቃዎች 15000/አስራ አምስት ሺህ ብር/ ለሎት /2/ ደንብ ልብስ 10000/አስር ሺህ ብር/ ለሎት /3/ የጽዳት እቃዎች 15000/አስራ አምስት ሺህ ብር/ለሎት /4/ቋሚ እቃዎች 7500/ሰባት ሺህ አምስት መቶ ብር/ ለሎት /5/የቋሚ አላቂ እቃዎች 3000/ሶስት ሺህ ብር/ ለሎት/6/የአገልግሎት ግዥ 5000/አምስት ሺህ ብር/ሲሆን የሁሉም ሎት በባንክ የተረጋገጠ ሲፒአ ማስያዝ ይኖርባቸዋል። ከሲፒኦ ውጪ ሌላ የጨረታ ማስከበሪያ አንቀበልም፡፡

4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበት የጨረታ አይነት ውስጥ የተዘረዘሩ እቃዎችን ዋጋ ሲሞሉ ከቫት ጋር እያንዳንዱ እቃ ዋጋ ድምር በጨረታ ሰነዱ ላይ በአለው የዋጋ መጠየቂያ ረድፍ በግልጽ ስርዝ ድልዝ ሳይኖር ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል።

5. ተጫራቾች በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ብቻ በመጠቀም የመወዳደሪያ ዋጋቸውን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በሌላ ቅጽ የሚጠቀሙ ተጫራቾች ጨረታ ውስጥ እንዳይሳተፉ ይደረጋሉ፡፡

6. ተጫራቾች ሙሉ ስማቸውን አድራሻቸውን የድርጅቱን ሙሉ ስም በእያንዳንዱ ሰነድ ላይ

በመፈረም ማቅረብ ይኖርባቸዋል ሰነዶችን በማህተም ማረጋገጥ አለባቸው፡፡

7. የጨረታውን አካሄድ ለማዛባት የሚሞከሩ ተጫራቾች ከጨረታ ውጪ ይደረጋሉ፡፡ ለወደፊቱም የመንግስት ግዥ ጨረታ ላይ እንዳይሳተፉ ይደረጋሉ፡፡ የአስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ወዲያውኑ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል።

8. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች በአቀረቡት የጨረታ መወዳደሪያ ሀሳብ ወይም ማሻሻያ ማድረግ እንዲሁም ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡

9. ተጫራቾች ከላይ የተጠየቁትን ማስረጃዎች አሟልተው አሽገው አንድ ኦርጅናልና አንድ ኮፒ ልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ፋይናንስ ጽ/ቤት 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 25 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

10. ተጫራቾች የአቅራቢነት ሰርተፍኬት ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማስገባት ይኖርባቸዋል።

11. ጨረታው በአስረኛው የስራ ቀን 10:30 ተዘግቶ በአስራ አንደኛው ቀን በስራ ቀን 4:30 ላይ ህጋዊ ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ሳጥኑ ይከፈታል።

12. ጨረታውን ያሸነፈ አካል ማሸነፉ እንደተገለፀለት ከ7 የቅሬታ ቀናት በኋላ ከመስሪያ ቤቱ ጋር ውል መፈፀም ይኖርበታል፡፡

13. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ በተጠቀሱ እቃዎች ዝርዝር በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ መጫረት ይችላሉ፡፡

14. ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚቀርቡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም፡፡

15. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

16. ተጫራቾች በሚወዳደሩበት የእቃ አይነት ለአንድ እቃ አንድ ሳምፕል ብቻ ማቅረብ ይኖርበታል በአንድ እቃ አይነት ሁለት ሳምፕል ያቀረበ ተጫራች ከውድድር ውጪ ይደረጋል፡፡

አድራሻ

ብስራተ ገብርኤል ቤተከርስቲያን ወረድ ብሎ ከብሩክ ክሊኒክ 200 ሜትር ገባ ብሎ ልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 አስተዳደር 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 25

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 0118329662

በልደታ ክፍለ ከተማ ወርዳ 08 ፋይናንስ ጽ/ቤት

Save Tender