በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ስር የሚገኘው የአለም ባንክ ጤና ጣቢያ ለ2017/2018ዓ.ም አንደኛ ዙር ጨረታ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
ከላይ በርዕሱ ለመግለፅ እንደተሞከረው በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ስር የሚገኘው የአለም ባንክ ጤና ጣቢያ ለ2017/2018ዓ.ም አንደኛ ዙር ጨረታ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
|
ተ.ቁ |
የአገልግሎት አይነቶች |
ሎት |
የጨረታ ማስከበሪያ |
|
1 |
ህትመት ስራዎች |
1 |
5,000.00 |
|
2 |
ቋሚ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች |
2 |
50,000.00 |
|
3 |
የፅዳት እቃዎች |
3 |
5,000.00 |
|
4 |
የደንብ ልብስ ስፌት |
4 |
20,000.00 |
|
5 |
የጭነትና የትራንስፖርት አገልግሎት |
5 |
5,000.00 |
|
6 |
የመኪና ጥገና ወይም የጋራዥ አገልግሎት |
6 |
5,000.00 |
|
7 |
የተለያዩ አላቂ የቢሮ እቃዎች (የጽህፈት መሣሪያዎች) |
7 |
5,000.00 |
|
8 |
ደንብ ልብስ |
8 |
15,000.00 |
|
9 |
ቋሚ ፈርኒቸር ዕቃዎች |
9 |
15,000.00 |
|
10 |
ሞንታርቦ ኪራይ |
10 |
50,000.00 |
|
11 |
የጥገና እቃዎች |
11 |
15,000.00 |
|
12 |
የጉልበት ስራዎች |
12 |
5,000.00 |
|
13 |
የድንኳን እና የወንበር ኪራይ |
13 |
5,000.00 |
|
14 |
የዲኮር አገልግሎት |
14 |
5,000.00 |
|
15 |
የመኪና መደበኛ ሰርቪስ ለአንድ አመት |
15 |
5,000.00 |
|
16 |
ትራንስፖርት አገልግሎት |
16 |
2,000.00 |
ስለሆነም መወዳደር የምትፈልጉ ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር ትችላላችሁ።
- ተጫራቾች በተሰማሩበት የስራ መስክ ምዝገባ ያላቸው የዘመኑ ግብር ለመክፈላቸው ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ አቅራቢ ዝርዝር ውስጥ የተመዘገበ ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- አነስተኛ ጥቃቅን ተቋማት በአዋጁ መሠረት የተቋቋሙ አምራች በሆኑበት ዘርፍ ብቻ ወይም በሚያመርቱት እቃ ብቻ ካደራጃቸው አካል በሚሰጥ የዋስትና ደብዳቤ መወዳደር ይችላሉ፡፡ ተቋማቱ አምራች ባልሆነበት ዘርፍ በዋስትና ደብዳቤ አናስተናግድም፡፡
- የጨረታ ሰነዱን በእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በግዥ ክፍል ቢሮ ቀ.7 መውሰድ ይቻላል።
- ከላይ በተገለፀው መሰረት የጨረታ ማስከበሪያ በአለም ባንክ ጤና ጣቢያ ስም በታወቀ ባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነድ ጋር በማያያዝ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የወሰዱትን ሰነድ የምትወዳደሩበትን ዋጋ ቫትን ጨምሮ በመሙላት በየሎቱ ኦርጅናሉንና ኮፒውን በሁለት ፖስታ አሽገው ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 11ኛ ቀን 3፡30 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ሁሉም ዕቃ ናሙና /ሳምፕል/ማንዋል/ፎቶግራፍ/ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ከገዙት ጨረታ ሰነድ ውጭ ተሞልቶ የሚመጡ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም፡፡
- ጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት በ11ኛ ቀን በ3፡30 ሠዓት ታሽጎ 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 አለም ባንክ ጤና ጣቢያ በግልፅ ይከፈታል፡፡
- ጤና ጣቢያው የተሻለ አማራጮች ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለጨረታ የቀረበ ሳንፕል ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ባለ በሁለት ወር ውስጥ ሳንፕሉን ካልወሰዱ ለተቋሙ ገቢ ይደረጋል።
- በሎት 2 እና 9 ሳንፐል በካታሎማ ወይም በፎቶ ግራፍ አጉልቶ በሚያሳይ ማቅረብ ይኖርባቸዋል ካላቀረቡ መወዳደር አይችሉም፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ናሙና ሲያመጡ በካርቶን ወይም በማዳበሪያ አሽጎ ማቅረብ አለባቸው። በፌስታል የሚመጣ ናሙና ተቀባይነት የለውም፡፡
- ተጫራቾች የወሰዱት የጨረታ መመሪያ ሰነድ በየገፁ ፈርመው ክብ ማህተም በማድረግ ከኦርጅናል ሰነድ ጋር በማሸግ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
አድራሻ፡- በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ የአለም ባንክ ጤና ጣቢያ ልዩ ቦታ ትሮፒካል የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጀርባ
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 0118-32-59-69
በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ የአለም ባንክ ጤና ጣቢያ
