አራዳ ከ/ከተማ ወረዳ 05 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 ዓ.ም በጀት አመት የአንደኛ (iኛ) ዙር ጨረታ፡- በሎትı፡- የጽዳት ዕቃዎች ግዥ በሎት2፡- የደንብ ልብስ ግዥ በሎት 1፡- አላቂ የቢሮ ዕቃዎች ግዥ በሎት4፡- የደንብ ልብስ ግዥ በሎት5፡- የመኪና ዕቃዎች ግዥ በጨረታ አውዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል ::
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
አራዳ ከ/ከተማ ወረዳ 05 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 ዓ.ም በጀት አመት የአንደኛ (1ኛ) ዙር ጨረታ፡- በሎትı፡- የጽዳት ዕቃዎች ግዥ በሎት2፡- የደንብ ልብስ ግዥ በሎት 1፡- አላቂ የቢሮ ዕቃዎች ግዥ በሎት4፡- የደንብ ልብስ ግዥ በሎት5፡- የመኪና ዕቃዎች ግዥ በጨረታ አውዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል :: በተጨማሪም በአገልግሎት ስራዎች ፡- በሎት 1፡- የመስተንግዶ ስራዎች በሎት 2፡- የህትመት ስራዎች በሎት 3፡- የኤሌክትሮኒክስ (የአይቲ) እቃዎች ጥገና ስራዎች በሎት4፡- የኤሌክትሮኒክስ (የአይቲ) እቃዎች መለዋወጫ አቅርቦት በሎት 5፡- የልብስ ስፌት ስራዎች በሎት 6፡- የቢሮ ቋሚ ዕቃዎች ጥገና ስራዎች በሎት 7፡- የዲኮር ስራዎችን በሎት 8፡-የትራንስፖርት አገልግሎት ስራዎች አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል ስለሆነም ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ሎቶች መስፈርቱን የምታሟሉ ተወዳዳሪዎች መጫረት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
-
ተጫራቾች በአቅራቢ ዝርዝር የተመዘገቡ መሆኑን እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
-
የታደሰ የንግድ ፈቃድና የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
-
የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡
-
ተጫራቾች የሚያስገቡት ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን አለበት ፡፡
-
የጨረታ ሰነዱ የመወዳደሪያ ዋጋ በሙሉ ታሽጎ ለጨረታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
-
ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ሎት ሁሉ ናሙና ማቅርብ አለባቸው ::
-
ተጫራቾች በአንድ እቃ አይነት ሁለት ናሙና ማቅረብ የለባቸውም::
-
ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ሎት ሁሉ ናሙና ላይ ድርጅታቸውን የሚገልፅ ማንኛውንም ምልክት (ማህተም) ማስቀመጥ የለባቸውም::
-
ተጫራቾች የጨረታው ማስታውቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር በየሎቱ 200 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ከወረዳ 5 ፋይናንስ ጽ/ቤት የጨረታ ሰነዱን መግዛት የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
-
ጨረታው ከወጣበት ቀን አንስቶ በዘኛው ቀን 4፡00 ሰዓት የሚታሸግ ሲሆን 4፡30 ሳጥኑ የሚከፈት ይሆናል፡፡
-
የመወዳደሪያ ዋጋ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት የምትችሉ ሲሆን ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይሆናል ፡፡
-
ተጫራቾች ዋጋቸውን በወሰዱት የጨረታ ሰነድ ላይ ብቻ መሙላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
-
ተጫራቾች በወሰዱት ሰነድ ላይ በእስክሪቢቶ እስፔክ ማስተካከል አይችሉም ፡፡
-
የጨረታ ዋስትና በየሎቱ 2% ሲፒኦ ብቻ ሲሆን የምንቀበለው ቼክ አንቀበልም በተጨማሪም ተጫራቾች ____አሸናፊ ሆነው ሲቀርቡ አሸናፊ የሆኑበትን 10% ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል ፡፡
-
ተጫራቾች የዋጋ የጊዜ ገደብ ማስቀመጥ አይችሉም::
-
መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ማሳሰቢያ፦ ተጫራቾች ለሚኖራቸው ጥያቄ ወይም መረጃ ለማግኘት ቢፈልጉ በስልክ ቁጥር 01111266384 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ ፡፡
አድራሻ ፡- ፒያሳ ገዳም ሰፈር ከጊዮርጊስ ጀርባ ወደ ዳክስን መሄጃ ወረዳ 5 ፋይናንስ ጽ/ቤት 2ኛ ፎቅ ::
የአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 05 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
