Tender Detail

Tender Details

በአራዳ ክ/ከተማ የወረዳ 2 ፋይናንስ ፅ/ቤት በ2018 ዓ/ም በጀት ዓመት በጨረታው ቁጥር001/2018 ዓ.ም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መገልገያ እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ሎት 1-የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ሎት-2-የፅዳት እቃዎች፣ ሎት-3-የሰራተኛ የደንብ ልብስ፣ ሎት.4. የኤሌክትሮኒከስ እቃዎች፣ ሎት-5-የበር ቁልፎች እና የጠረጴዛ መሳቢያ ቁልፎች፣ ሎት.6. የኤሌትሪከ እቃዎች፣ ሎት 7 የሰራተኛ ደንብ ልብስ ስፌት፣ ሎት.8. የቢሮ መገልገያዎች ቋሚ እቃዎች፣ ሎት 9. የተለያዩ ትራንስፖርት አቅርቦት፣ ሎት 10 የኤሌከትሮኒከስ ጥገና ባለሙያ፣ ሎት 1. የኤሌከትሮኒከስ መለዋወጫ እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

የዕቃዎች ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

1. ተጫራቾች በሙያው የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፣ የተጨማሪ እሴት ታከስ ተመዝጋቢ የሆኑና በተሰማሩበት የስራ መስክ የዘመኑን ግብር መከፈላቸውን የሚያረጋግጥ እና ወቅታዊ ከሊራንስ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

2. በመንግስት የግዥ ጨረታ ላይ ለመሳተፍ የሚያስችል የተሟላ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉና በአቅራቢነት ሊስት ውስጥ ተመዝጋቢ የሆኑ፤

3. የጨረታውን ዝርዝር የያዘ ሰነድ የማይመለስ 500 ብር በመከፈል ማግኘት ይችላሉ፡፡

4. የጨረታ ሰነዶቻችሁን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የስራ ቀናት ውስጥ በመሙላት ለጨረታ ማስከበሪያ የሚያገለግል የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለእያንዳንዱ ለተጫረቱበት ሎቶች 2% በባንከ በተረጋገጠ ሲፒአ/CPO/ ብቻ በአራዳ ከ/ከተማ ወረዳ 2 ፋይናንስ ጽ/ቤት ስም አሰርተው በታሸገ ኤንቨሎፕ ሞልተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

5. ጨረታው በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በእዛው እለት በ4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአራዳ ክ/ከተማ በወረዳ 2 አስተዳደር መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።

6. የጨረታ ሰነዱን ቴከኒካል እና ፋይናሻል በኦርጅናል እና ኮፒ ሞልተው ማቅረብ አለባቸው፡፡

7. ከገዙበት ጨረታ ሰነድ የዋጋ መሙያ ፎርም ውጭ ዋጋ ተሞልቶ የሚመጣ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡

8. ዋስትና ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች ዋስትና ማቅረብ የሚችል፣

9. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡- ከጎጃም በረንዳ በዩሃንስ የሚወስደው መንገድ አራት መንታ ሐግቤስ አካባቢ በስልክ ቁጥር 0111-55-32-16/ 0111-26-54-20

በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 2 ፋይናንስ ጽ/ቤት

Save Tender