የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የተሸከርካሪ መለዋወጫ፣ የመኪና ጎማና ባትሪ፤ የመኪና አልባሳትና ጌጣጌጥ እንዲሁም ለመኪና ጥገና ስራ የሚያግለግሉ የተለያዩ የኤሌክትሪክ እና ተዛማጅ ዕቃዎች ግዥ በጨረታ መለያ ቁጥር ፌ.ቤ.ኮ/ብ.ግ.ጨ/ዕቃ/11/12/2017 ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
ፌ.ቤ.ኮ/ብ.ግ.ጨ/ዕቃ/11/12/2017
- የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የተሸከርካሪ መለዋወጫ፣ የመኪና ጎማና ባትሪ፤ የመኪና አልባሳትና ጌጣጌጥ እንዲሁም ለመኪና ጥገና ስራ የሚያግለግሉ የተለያዩ የኤሌክትሪክ እና ተዛማጅ ዕቃዎች ግዥ በጨረታ መለያ ቁጥር ፌ.ቤ.ኮ/ብ.ግ.ጨ/ዕቃ/11/12/2017 ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- ኮርፖሬሽኑ ለሚያከናውነው የተሸከርካሪ መለዋወጫ ለመኪና ጥገና ስራ የሚያገለግሉ የተለያዩ የኤሌከትሪክ እና ተዛማጅ ዕቃዎች ግዥ ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውንና የዕቃውን ዋጋ በተለያዩ በታሸጉ ኢንቨሎፖች ማቅረብ አለባቸው።
|
ሎት |
የግዥው ዓይነት |
የጨረታ ማስከበሪያ |
|
1 |
የተሽከርካሪ መለዋወጫ |
40,000 |
|
2 |
የመኪና ጎማና ባትሪ፤ የመኪና አልባሳትና ጌጣጌጥ |
30,000 |
|
3 |
ለመኪና ጥገና ስራ የሚያገለግሉ የተለያዩ የኤሌክትሪክ እና ተዛማጅ ዕቃዎች |
20,000 |
- ጨረታው የሚከናወነው በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ሥነ-ሥርዓትና ይህንኑ አስመልክቶ በፈዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የግዥ መመሪያ መሠረት ሲሆን ከሚፈለገው ግዥ ጋር የተዛመደ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የግብር ከፋይ ማስረጃ የሚያቀርቡ መሆን ይኖርበታል፡፡
- የተሟላ የአማርኛ የጨረታ ሰነዶችን ማንኛውም ፍላጎት ያለው ተጫራች ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 400.00 /አራት መቶ ብር/ በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ለገሀር በሚገኘው በተለምዶ የስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 201 በኮርፖሬሽኑ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በአካል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቻቸውን በኮርፖሬሽኑ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬከቶሬት ቢሮ ቁጥር 201 ለዚሁ ታሽጎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ የጨረታ ማስታወቂያው በመጀመሪያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ወይም መስከረም 7 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ እንዲያቀርቡ ሆኖ በባንክ በተመሰከረለት ቢድ ቦንድ ወይም ሲፒአ በፈዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ስም ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡ ዘግይቶ የቀረበ የጨረታ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል፣ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት መስከረም 7 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት በኮርፖሬሽኑ ግዥና ንብረት አስተደደር ዳይሬክተር ቢሮ ይከፈታል፡፡
- በሚያወጣው ፕሮግራም መሠረት አሸናፊው ተጫራች በኮርፖሬሽኑ በግንባር በመገኘት ዕቃውን ያስረከባል፡፡
- ኮርፖሬሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 011-8-55-36-17
P.O. Box 299
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን
