በደጃዝማች ገረሱ ዱኪ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ የ2018 በጀት ዓመት ከዚህ በታች በሰንጠረዥ በዝርዝር የተገለፁትን ነገሮች በ1ኛ ዙር ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የመደበኛ እቃ ግዥ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 001/2018
በደጃዝማች ገረሱ ዱኪ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ የ2018 በጀት ዓመት የ1ኛ ዙር ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች እንድትወዳደሩ እንጋብዛለን።
|
ተ.ቁ |
የእቃው ዓይነት |
የሎት አይነት |
የጨረታ ማስከበሪያ ብር መጠን (በኢትዮጵያ ብር) |
|
1 |
ስቴሽነሪ እና ቶነሮች |
ሎት 1 |
30,000 ብር |
|
2 |
የፅዳት እቃዎች |
ሎት 2 |
40,000 ብር |
|
3 |
የደንብ ልብስ |
ሎት 3 |
20,000 ብር |
|
4 |
የቢሮ ቋሚ ኤሌክትሮኒክስ እና ፈርኒቸር እቃዎች |
ሎት 4 |
50,000 ብር |
|
5 |
የመኪና አላቂና ቋሚ እቃዎች |
ሎት 5 |
20,000 ብር |
|
6 |
የኤሌክትሪክና የቧንቧ ጥገና እቃዎች |
ሎት 6 |
10,000 ብር |
|
7 |
የእንጨት ስራ ት/ክፍል አላቂ እና ቋሚ የስልጠና እቃዎች |
ሎት 7 |
50,000 ብር |
|
8 |
የኤሌክትሪክሲቲ ት/ክፍል አላቂ የስልጠና እቃዎች |
ሎት 8 |
10,000 ብር |
|
9 |
የቆዳ ት/ክፍል አላቂ እና ቋሚ የስልጠና እቃዎች |
ሎት 9 |
50,000 ብር |
|
10 |
የኮንስትራክሽን ት/ክፍል አላቂ የስልጠና እቃዎች |
ሎት 10 |
20,000 ብር |
|
11 |
የማኑፋክቸሪንግ ት/ክፍል አላቂ የስልጠና እቃዎች |
ሎት 11 |
20,000 ብር |
|
12 |
የጋርመንት ት/ክፍል አላቂ እና ቋሚ የስልጠና እቃዎች |
ሎት 12 |
50,000 ብር |
|
13 |
የአውቶሞቲቭ ት/ክፍል አላቂ እና ቋሚ የስልጠና እቃዎች |
ሎት 13 |
50,000 ብር |
|
14 |
የከተማ ግብርና ት/ክፍል አላቂ እና ቋሚ የስልጠና እቃዎች |
ሎት 14 |
20,000 ብር |
|
15 |
የሆቴል ምግብ ዝግጅት፤ ፀጉር ስራ ት/ክፍል አላቂ እና ቋሚ የስልጠና እቃዎች |
ሎት 15 |
40,000 ብር |
|
16 |
የአይሲቲ ት/ክፍል አላቂ እና የጥገናና የስልጠና እቃዎች |
ሎት 16 |
15,000 ብር |
ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች
- (ከላይ በተጠቀሱት የዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር መለያ ቁጥርና የተጨማሪ እሴት ታክስ /የቫት ሰርትፍኬት) ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- በአቅራቢዎች መመዝገቢያ ላይ ራሳቸውን የመዘገቡ፤
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአሥር /10/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በሥራ ሠዓት በደጃ ዝማች ገረሱ ዱኪ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ መ/ግ/ቡድን የማይመለስ ለእያንዳንዱ ሎት 200 ብር (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ለመግዛት ይችላሉ፡፡ ሰነዱን ለመግዛት ሲመጡ በሚወዳደሩበት ሎት የተጠየቀውን ሰነድ ዋናውን ይዘው መምጣት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ሲፒአ (C.P.O) ደጃዝማች ገረሱ ዱኪ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ስም ማሰራት ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራች የሚያቀርቡት ዋጋ በእያንዳንዱ ላይ ቫትን ያጠቃለለ መሆን አለበት፡፡ ዋጋው ቫትን ያላጠቃለለ ከሆነ ከጨረታ ውድቅ ይሆናል፡፡
- ማንኛውም ተጫራቾች የሚያቀርበው የጨረታ ሰነድ ስርዝ ድልዝ ኖሮት ካልተፈረመ ፍሉድ የተጠቀመ ከሆነ እና በጉልህ የማይነበብ ከሆነ ከውድድር ውጪ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ተወዳድረው የሚያስገቡት ዕቃ ደረጃውን የጠበቀ መሆን አንዳለበትና በተወዳደረባቸው ሎቶች በሙሉ ከጨረታው ቀደም ብሎ የዕቃዎች ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ናሙና ያልቀረበባቸው የዕቃ ዓይነቶች ከውድድር ውጪ ይሆናሉ፡፡
- ተጫራቾች የወሰዱትን የገዙትን/ የጨረታ ሰነዱን በእያንዳንዱ ገጽ ላይ ፊርማና የድርጅቱን ማህተም በማድረግ ሰነዱን ሙሉ በሙሉ መመለስ ይኖርባቸዋል፡፡ ሰነዱን ሙሉ በሙሉ ካልተመለሰ ከጨረታ ውጪ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የመደበኛ ጨረታ ሰነዱን ቴክኒካል ሰነድ እና ፋይናሻል ሰነድ ዋናውንና ኮፒውን በታሸገ ኤንቨሎፕ /ፖስታ/ በማሸግ በአንድ ፖስታ በማጠቃለል አሽገው ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- አሸናፊው ተጫራቾች ያሸነፈውን ጠቅላላ ዕቃዎች በደጃዝማች ገረሱ ዱኪ ኢንዱስትረያል ኮሌጅ ንብረት ክፍል ድረስ በማምጣት ገቢ ማድረግ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ሲያሸንፍ 10 (%) ፐርሰንት የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታው ሳጥኑ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሠዓት ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ጨኪሎቻቸው በተገኙበት በኮሌጅ መ/ግ/ቡድን ይከፈታል፡፡
- የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ቀን በበዓላት ቀን /እሁድና ቅዳሜ/ ከሆነ ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይሆናል፡፡
- ኮሌጁ 20% ያሸነፉበትን እቃ የመጨመር የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ፡ ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውነ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ደጃዝማች ገረሱ ዱኪ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ መ/ግ/ቡድን ስ.ቁጥር 0112739712
ልዩ ስሙ፡- ከመሳለሚያ ሠፈረ ሠላም ወደ መድሃኒዓለም ት/ቤት በሚወስደው አስፋልት ያኔት ኮሌጅ ከፍ ብሎ
በደጃዝማች ገረሱ ዱኪ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ
