በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የወረዳ 13 ትምህርት ጽ/ቤት የሚኪሊላንድ አንደኛ እና መካከለኛ/ደ/ት/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 01/2018 ዓ.ም
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የወረዳ 13 ትምህርት ጽ/ቤት የሚኪሊላንድ አንደኛ እና መካከለኛ/ደ/ት/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። ሆኖም የጨረታ ማስከበሪያ በተጫረቱበት ዘርፍ የሞሉትን በባንክ በተረጋገጠ CPO ብቻ ማስያዝ አለባቸው
1ኛ. ሎት 1 የደንብ ልብስ ------- 6,000 /ስድስት ሺህ ብር/0.5%/ የተሰራ
2ኛ. ሎት 2 አላቂ የቢሮ ዕቃዎች ------- 4,500 /አራት ሺህ አምስት መቶ ብር/ 0.5%/ የተሰራ
3ኛ. ሎት 3 አላቂ የትምህርት እቃዎች ------- 1,500 /አንድ ሺህ አምስት መቶ ብር/ 0.5%/ የተሰራ
4ኛ. ሎት 4 የፅዳት ዕቃዎች ------- 4,500 /አራት ሺህ አምስት መቶ ብር / 0.5% / የተሰራ
5ኛ. ሎት 5 ለፕላንት ለማሸነሪ እና ለመሳሪያ መግዣ------- ብር 16,000 / አስራ ስድስት ሺህ ብር/ 0.5%/ የተሰራ
6ኛ. ሎት 6 ለህትመት ------- 90.00 /ዘጠና ብር/ 0.5%/ የተሰራ
7ኛ ሎት 7 አላቂ የህክምና ዕቃዎች ------- 20.00 /ሃያ ብር/ 0.5% /የተሰራ
8ኛ. ሎት 8 ለፕላንት ለማሽነሪ እና ለመሳሪያ እድሳት እና ጥገና ---- 500 /አምስት መቶ ብር/ 0.5% / የተሰራ
9ኛ. ሎት 9 ለህንፃ ለቁሳቁስ እና ለተገጣጣሚዎች እድሳት እና ጥገና ------- 1500 /አንድ ሺህ አምስት መቶ ብር/ 0.5%/ የተሰራ
10ኛ. ሎት 10 ለመሰረተ ልማት እድሳት እና ጥገና -------25.00 /ሃያ አምስት ብር/ 0.5% /የተሰራ
11ኛ. ሎት 11 ቆሎ፤ ውሃ እና ኩኪስ -------375.00 /ሦስት መቶ ሰባ አምስት ብር/ 0.5%/ የተሰራ
በዚህ መሰረት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶችና ግለሰቦች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል።
- የንግድ ፈቃድ ሰርተፍኬት ያላቸው
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ (Tin) ቁጥር ያላቸው::
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (የቫት) ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
- የአቅራቢዎች ምዝገባ በ WWW.egp.ppa.gov.et የተመዘገበ
- ናሙና /ሳምፕል/ ለሚጠይቁ ዕቃዎች ማቅረብ የሚችል፡፡
- የጨረታ አሸናፊዎች ማሸነፋቸው ከተረጋገጠበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አሥር) የስራ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ 10% ባሸነፉባቸው ዕቃዎች ላይ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝና ተዋውለው ዕቃዎችን በትምህርት ቤቱ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙበት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቫትን ጨምሮ በመግለፅ ዋናውን እና ኮፒውን በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ ፖስታ ከላይበተጠቀሰው የስራ ቀናት ዘውትር በስራ ሰዓት ቢሮ ቁጥር 6 ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ናሙናዎች ጨረታው ከመከፈቱ ከሁለት ቀን በፊት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- በጥቃቅን እና አነስተኛ የተደራጁ አካላት ከሆኑ በሚያመርቱበት ምርት ብቻ በመወዳደር እና ሰነድ ለመውሰድ በሚመጡበት ጊዜ ከሚመለከተው አካል ወቅታዊ የሆነ፣ በጽ/ቤቱ ስም የተፃፈ የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ከ2፡30 እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ የሚኪሊላንድ አንደኛ እና መካከለኛ/ደ/ት/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 በመገኘት 200 ብር (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በ10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ላይ ያልቃል ፡፡
- ጨረታው በ11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚመጣ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
- ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
አድራሻ፡- ወደ አስኮ በሚወስደው መንገድ ብርጭቆ ኮንዶሚኒየም ጊቢ ውስጥ
ስልክ ቁጥር፡- 0112731807 /0112731701
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የወረዳ 13 ትምህርት ጽ/ቤት የሚኪሊላንድ አንደኛ እና መካከለኛ/ደ/ት/ቤት
