በአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሌጅ በ2018 በጀት ዓመት በኮሌጁ ለሚገኙ የተለያዩ የስራ ክፍሎች መገልገያ እና በአመቱ በተለያዩ ወቅት ለሚሰጣቸው ልዩ ልዩ ስልጠናዎች ለሰልጣኞች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ እቃዎች ግዥ በማስፈለጉ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር AAPPC 001/18
በአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሌጅ በ2018 በጀት ዓመት በኮሌጁ ለሚገኙ የተለያዩ የስራ ክፍሎች መገልገያ እና በአመቱ በተለያዩ ወቅት ለሚሰጣቸው ልዩ ልዩ ስልጠናዎች ለሰልጣኞች አገልግሎት የሚውሉ፡-
- ሎት 1 የምግብ እህሎች ፣ ጥራጥሬዎች እና አትክልቶች፤
- ሎት 2 የመመገቢያ እቃዎች / ቁሳቁስ /1
- ሎት 3 ልዩ ልዩ አልባሳት ፤
- ሎት 4 የተለያዩ የጽህፈት መሳሪያዎች ፤
- ሎት 5 የተለያዩ የፅዳት እቃዎች ፤
- ሎት 6 የበሬ ስጋ ለወጥ የሚሆን ምንም አይነት አጥንት የሌለው ፤
- ሎት 7 የባህር ዛፍ ማገዶ እንጨት ፤
- ሎት 8 የተለያዩ የኤሌክትሪክ እና የግንባታ እቃዎች ግዥ በማስፈለጉ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም በዚሀ ጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች
- ጨረታው የሚከናወነው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ግዥ አዋጅ በተገለፀው ግልፅ ጨረታ ስነ-ስርዓት መሰረት ይፈጸማል ፤ የምግብ እህሎች፤ ጥራጥሬዎች እና አትክልቶች፤ የመመገቢያ እቃዎች /ቁሳቁስ/፤ ልዩ ልዩ አልባሳት ፤ የተለያዩ የጽህፈት መሳሪያዎች፤ የተለያዩ የጽዳት እቃዎች ፤ የበሬ ስጋ ለወጥ የሚሆን ምንም አይነት አጥንት የሌለው ፤ የባህር ዛፍ ማገዶ እንጨት እና የተለያዩ የግንባታ እና የኤሌክትሪክ እቃዎች ጨረታው የሚያከናውነው ብቁ ከሆኑ ተጫራቾች እና ከስራው ጋር አግባብነት ያለው ሆኖ በ2018 ዓ/ም የታደሰ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ ያለው ፤ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚገልፅ ወቅታዊ ደብዳቤ /Tax clearance/ ከሀገር ውስጥ ገቢ ባለስልጣን በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ መመዝገባቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ከገንዘብ እና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር እንዲሁም ተ.እ.ታ /VAT/ ሰርተፊኬት እና ቲን /TIN/ ሰርተፊኬት ኮፒውን ማቅረብ የሚችል ይሆናል፡፡ በሁሉም ሎቶች ላይ የሚወዳደሩ አቅራቢዎች የሚያቀርቡት ሰነድ በአጠቃላይ የታደሰ መሆን አለበት።
- ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ለመግዛት የኢትዮጵያ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ ከፍለው የጨረታውን ሰነድ ቢሮ ቁጥር 28 በስራ ቀናት ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡ በአነስተኛ እና ጥቃቅን ተቋማት አዋጅ መሰረት የተቋቋሙ ተቋማት ለጨረታው የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በአነስተኛ እና ጥቃቅን ተቋማት የተቋቋሙበት የህጋዊነት ማስረጃ በማሳየት ያለ ክፍያ በነፃ ይሰጣቸዋል፡፡ በአደራጃቸው አካል የሚጫረቱበት ሎት በዘርፉ መሰማራታቸውን የሚገልፅ የቅርብ ጊዜ ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች በሎት 1. ብር 10,000.00 /አስር ሺህ ብር/ 1 በሎት 2. ብር 7,000.00 /ሰባት ሺህ ብር / ፤ በሎት 3 ብር 7,000.00 /ሰባት ሺህ ብር/ ፣ በሎት 4. ብር 5,000.00 /አምስት ሺህ ብር/ ፤ በሎት 5. ብር 5,000.00 /አምስት ሺህ ብር/ ፤ በሎት 6. ብር 15,000.00 /አስራ አምስት ሺህ ብር/ ፤ በሎት 7. ብር 7,000.00 /ሰባት ሺህ ብር/ እና በሎት 8. ብር 8,000.00 /ስምንት ሺህ ብር/ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠለት ሲፒኦ በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሌጅ ስም አዘጋጅቶ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት በኮሌጁ ፋይናንስና ግዥ ዲቪዚዮን በመቅረብ ለዚህ ሲባል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በሁለት ፖስታ ፋይናንሺያል ኮፒና ኦሪጂናል እንዲሁም በሁለት ፖስታ ቴክኒካል ኮፒና ኦሪጂናል በድምሩ በ4 ፖስታ ሰነዶችን በመለየት ማስገባት አለባቸው።
- ዘግይተው የቀረቡ የጨረታ መልሶች ተቀባይነት የላቸውም፡፡ የጨረታው ሳጥን በ11ኛው ቀን በ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያኑ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮሌጁ አዳራሽ ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ሲሆን ይከፈታል፡፡ የመዝጊያውና የመክፈቻው ቀን የመንግስት ስራ ቀን ወይም ካላንደር /የቀን መቁጠሪያ/ የሚዘጋው በዓል ከሆነ በሚቀጥለው ስራ ቀን ይሆናል ፡፡
- ተጫራቾች በሚጫረቱበት ሎት ላይ በግምጃ ቤታቸው በቂ የሆነ የእቃዎች ክምችት መኖር አለበት፡፡
- ሌሎች ደጋፊ ሰነዶችን እንደ የመልካም ስራ አፈፃፀም እና የመሳሰሉትን ማቅረብ የተሻለ ውጤት አለው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ ፡- ኮልፌ ሉኳንዳ አዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሌጅ ማሰልጠኛ ማዕከል /የቀድሞ ፈጥኖ ደራሽ ግቢ/ አጠገብ።
ለበለጠ መረጃ 0112-73-94-86 ፤ 0112-73-95-48 ወይም 251-118-33-38-45
አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሌጅ
