Tender Detail

Tender Details


የሀዋሳ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን የተተዉና ተወርሰው የሚገኙ መገናኛ መሣሪያዎች ኤሌክትሪክ ዕቃዎች አልባሳትና ጨርቃ ጨርቅ፣ የመዋቢያና የንፅህና መጠበቂያዎች፣ የቤትና ቢሮ ዕቃዎች የኤሌክትሮኒክስ መሣሪያ (YAMAHA Digital key board የሞተር ሳይክል መለዋወጫ የመኪና መለዋወጫዎች ያገለገለ ሞተር ሣይክሎች እና ምግብ ነክ በግልፅና በሃራጅ ጨረታ ባለበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።


የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 10/2018

በጉምሩክ ኮሚሽን ሀዋሳ //ቤት የተተውና የተወረሱ ዕቃዎች ሽያጭ

 

የሀዋሳ ጉምሩክ ኮሚሽን //ቤት በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን የተተዉና ተወርሰው የሚገኙ መገናኛ መሣሪያዎች ኤሌክትሪክ ዕቃዎች አልባሳትና ጨርቃ ጨርቅ፣ የመዋቢያና የንፅህና መጠበቂያዎች፣ የቤትና ቢሮ ዕቃዎች የኤሌክትሮኒክስ መሣሪያ (YAMAHA Digital key board የሞተር ሳይክል መለዋወጫ የመኪና መለዋወጫዎች ያገለገለ ሞተር ሣይክሎች እና ምግብ ነክ በግልፅና በሃራጅ ጨረታ ባለበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በመሆኑም በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል።

  1. ማንኛውም ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው/ያላት የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ /ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣ ግምታዊ ዋጋው ከብር 500ሺህ በታች የሆነውን ማንኛውንም ዕቃ ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አያስፈልግም።
  2. ማንኛውም የሞተር ሣይክል ተጫራች ዕድሜው 18 ዓመት የሞላው ኢትዮጵያዊ መታወቂያ በማቅረብ መጫረት ይችላል።
  3. ማንኛውም ተጫራች የጨረታውን ሰነድ በጨረታ ማስታወቂያው ላይ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ጠዋት 200 እስከ 600  ከሰዓት 700 እስከ 1100 ሰዓት፡ ቅዳሜ  200 እስከ 600 ሰዓት ድረስ ብቻ በተጫራቹ ስም የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶበመክፈል በቅ//ቤቱ ከገቢ ሂሳብና ዋስትና አስተዳደር ቡድን መውሰድ ይችላሉ።
  4. ማንኛውም የግልፅ ጨረታ ተጫራች ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆን የሚጫረትበትን ጠቅላላ ዋጋ 500(አምስት በመቶበኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተመሰከረለትን CPO የጨረታ ሰነድ እና አጠቃላይ መረጃዎችን ጨረታው ከመከፈቱ በፊት በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል።
  5. ማንኛውም የሃራጅ ጨረታ ተጫራቾች የዕቃው ዓይነት እና የጨረታ ማስከበሪያ CPO በጨረታ ሰነድ ላይ የሚገለፅ ይሆናል።
  6. ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን በመግዛት እስከ 5ኛው (አምስተኛውቀን ድረስ የንብረቶቹን ናሙና በመደበኛ የስራ ሰዓት በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን ማየት የሚችሉ ሲሆን ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን 6ኛው (ስድስተኛውቀን ግልጽ ጨረታው ጠዋት 400 ሰዓት በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን ይካሄዳል የሃራጅ ጨረታው የግልፅ ጨረታው ከተጠናቀቀ 10 ደቂቃ በኋላ ይካሄደል። ነገር ግን የጨረታው ቀን እሁድ ወይም በበዓላት ቀን ከዋለ በተመሳሳይ ሰዓት በሚቀጥለው የስራ ቀን ይካሄዳል።
  7. ማንኛውም የግልፅ ጨረታ ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታ ሰነድ ላይ የሰጠውን ዋና መግለጫ መለወጥ እና ማሻሻል አይችልም።
  8. ማንኛውም ተጫራች የሰጠው የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታው ሂደት ተጠናቆ //ቤቱ የጨረታውን ውጤት እስከሚያሳውቅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል።
  9. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ራሱን ከጨረታ ውድድር ማግለል አይችልም።
  10. በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት CPO በዕለቱ የሚመለስላቸው ሲሆን አሸናፊው ያስያዘው ዋስትና ግን ከሽያጭ ጋር የሚታሰብለት ይሆናል።
  11. ተጫራቾች ዕቃውን ሳያዩ ዋጋ ቢሰጡና ቅሬታ ቢፈጠር //ቤቱ ተጠያቂ ኣይሆንም።
  12. ለጨረታው የቀረበው ዕቃ ሽያጭ የሚፈፀመው ባለበት ሁኔታ ነው።
  13. አሸናፊው ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በውስጥ ማስታወቂያ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ አምስት ቀናት ውስጥ የአሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃዎችን ማንሳት ይኖርባቸዋል። ይህንን ባያደርጉ ጨረታው ተሠርዞ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለቅ//ቤቱ ገቢ ተደርጎ ዕቃው በድጋሚ በጨረታ ላይ ይወጣል።
  14. ቅጽ ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ የስልክ ቁጥር፡-046 212 5396

 

በጉምሩክ ኮሚሽን የሀዋሳ //ቤት

Save Tender