በኮ/ቀ/ክ/ከተማ የወረዳ 02 የህዳሴ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በ2018 ዓ ም በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 001/2018
በኮ/ቀ/ክ/ከተማ የወረዳ 02 የህዳሴ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በ2018 ዓ ም በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ሎት1. የደንብ ልብስ ፣ ሎት 2. አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ ሎት 3. የህትመት ሥራ፣ ሎት 5. አላቂ የትምህርት እቃዎች፣ ሎት 6. የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 7. የት/ት መሣሪያዎች መግዣ፣ ሎት 8. ፕላንት ማሽነሪ፣ ሎት 9. የተገጣጣሚ እና ቁሳቁስ መግዣ፣ ሎ10. ኤሌክትሮኒክስ ጥገና፣ ሎት 11. የተገጣጣሚ እና ቁሳቁስ ጥገና፣ ሎት12. መሰረተ ልማት፣ ሎት 13. የጉልበት እና የትራንስፖርት፣ ሎት15. ልዩ ልዩ ክፍያዎች በዚህ መሰረት
ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈረት የምታሟሉ ተጫራቾች መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- ተጫራቾች ከሥራው ዘርፍ ጋር አግባብነት ያለው የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው የዘመኑ ግብር መክፈላቸውን የሚገልጽ ወቅታዊ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል፤
- ት/ቤቱ በሚሸጠው ሰነድ ላይ ያለውን ማንኛውንም መመሪያ በማጤን እና የሚመለከተውን በመሙላት፣ ማህተም በማድረግ፣ ሰነዱን በሙሉ በታሸገ ፖስታ ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን በተለያየ ፖስታ በማድረግ በኮ/ቀ/ክ/ከተማ የወረዳ 02 የህዳሴ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ቢሮ ቁጥር 7 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅበታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለመግዛት በየሎቱ የማይመለስ 100 ብር /አንድ መቶ ብር/ ከፍለው መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታዎች ለመሳተፍ የጨረታ ማስከበሪያ /cpo/ የብር መጠን በየሎት ለእያንዳንዱ ሎት1. 18,000፣ ሎት2. 21,000፣ ሎት3. 2,000፣ ሎት5. 14,000 ሎት6.18,000፣ ሎት7. 13,000፣ ሎት8. 17,000፣ ሎት9. 18,000፣ ሎት10. 2,000፣ ሎት11. 9,000፣ ሎት12. 12,000፣ ሎት13. 6,000፣ ሎት15. 3,000 ማስያዝ አለባቸው።
- በጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በጨረታ ማስከበሪያ በውል ማስከበሪያ እና በቅድሚያ ክፍያ ዋስትና ምትከ ካደራጀው ተቋም በኃላፊ ብቻ የተፈረመ የዋስትና ደብዳቤ ተቀባይነት ሲኖረው በሥራ ሂደት የሚፈረም ደብዳቤ ተቀባይነት የለውም፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የሚጫረቱበት እቃ ላይ የሚያቀርቡት የእቃ ናሙና በግልጽ የሚታይ ፎቶ፣ ቦታው ላይ እና የሚሸጠው ሰነድ ላይ በወጣው መሰረት ማሳየትና ማቅረብ አለበት፡፡
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት ማንኛውም ናሙና ላይ ምንም አይነት የድርጅቱ ስም፣ ኮድም ሆነ ማህተም የሚገልጽ ነገር ቢያስቀምጡበት ከውድድር ውጪ እንደሚሆኑ እንገልጻለን፡፡
- የኤሌክትሮኒክስ ጥገና ፣ የቁሳቁስ ጥገና፣ የትራንስፖርት እና ጉልበት ላይ አሸናፊ የሚሆኑት ውላችን የአንድ ዓመት መሆኑ ይታወቅ።
- ጨረታው ከወጣበት 23/01/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት በአየር ላይ ቆይቶ በ11ኛው ቀን በ3፡30 ሰዓት ታሽጎ በ4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት በፋይናንስ ክፍል ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜ እና እሁድ /የበዓላት ቀን/ የሚውል ከሆነ ቀኑን አሳልፈን የምንከፍት መሆኑን ማወቅ አለባቸው፡፡
መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፈል /በሙሉ/ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ካራ ቆሬ ወደመደኃኒዓለም ቤተክርስቲያን መሄጃ ፖሊስ ጣቢያውን አለፍ ብሎ
ተጨማሪ መረጃ:- 0113695428/0113695841/
በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ የወረዳ 02 የህዳሴ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ፋይናነስ ግዥ/ ቢሮ፡፡
በኮ/ቀ/ክ/ ከተማ የወረዳ 02 የህዳሴ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
