የ2018 ዓ.ም የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 001/2008 ዓ.ም የጎፋ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የ2018 ዓ.ም የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 001/2008 ዓ.ም የጎፋ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ሎት 1 የኮምፒውተርና ተጓዳኝ ዕቃዎች ........................................ 100,000 ብር
ሎት 2 የማኑፋክቸሪንግ ዲፓርትመንት ዕቃዎች ............................. 100,000 ብር
ሎት 3 የጋርመንት ዲፓርትመንት ዕቃዎች ..................................... 100,000 ብር
ሎት 4 የፈርኒቸር ዲፓርትመንት ዕቃዎች ....................................... 100,000 ብር
ሎት 5 የኤሌክትሪክ ዲፓርትመንት ዕቃዎች .................................. 100,000 ብር
ሎት 6 የአውቶሞቲቭ ዲፓርትመንት ዕቃዎች ............................... 100,000 ብር
ሎት 7 የሌዘር ዲፓርትመንት ዕቃዎች ............................................. 70,000 ብር
ሎት 8 የኮንስትራክሽን ዲፓርትመንት ዕቃዎች .............................. 70,000 ብር
ሎት 9 የሆቴል ዲፓርትመንት ዕቃዎች ........................................... 70,000 ብር
ሎት 10 የከተማ ግብርና ዲፓርትመንት ዕቃዎች ........................... 100,000 ብር
ሎት 11 የደንብ ልብስ ..................................................................... 100,000 ብር
ሎት 12 የአላቂ የጽዳት ዲፓርትመንት ዕቃዎች ............................. 100,000 ብር
ሎት 13 የጽህፈት መሳሪያዎች ........................................................ 100,000 ብር
ሎት 14 የህትመት ስራዎች .............................................................. 50,000 ብር
ከላይ ያሉትን የግዥ አይነቶች መሰረት በማድረግ በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች
- ለሚጫረቱበት ዘርፍ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆናቸው የሚገልጽ ማረጋገጫ፤ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የምዝገባ ሰርተፍኬት እና በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ መመዝገባቸው የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
- የጨረታው ሰነድ ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመከፈል ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በስራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡00 በኮሌጁ የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን መሪ ቢሮ ቁጥር 4 በመቅረብ መውሰድ ይቻላል።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዕቃ ኮሌጁ ባስቀመጠው ሎት መሰረት ለዘርፉ በአቅራቢነት መመዝገባቹን በማረጋገጥ ዋጋቸውን በመሙላት የፅዳት፤ ጽህፈት እና የደንብ ልብስ ዕቃዎች ሎቶች ላይ ብቻ በቅድሚያ ሳንፕል በማቅረብ በየሎቱ በአራት /4/ በፖስታ በማሸግና በግልፅ በመጻፍ ኦርጅናል ቴክኒካልና ፋይናንሻል እንዲሁም ቴክኒካልና ፋይናንሻል ፎቶ ኮፒ ሰርተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ናሙና ሳንፕል/ ያልተጠየቀባቸውን ሎቶች በዕቃው ዝርዝር / እስፔስፊክሽን/ መሰርት በሁለት /2/ ፖስታ መቅረብ አለበት፤
- ዋጋ ሲሞላ በኮሌጁ ኦርጅናል ሰነድ ላይ መሆን አለበት።
- ዋጋው ከነቫቱ መሞላት አለበት።
- ጥቃቅንና አነስተኛ ተወዳዳሪዎች በጨረታ እንድትሳተፉ ከአደራጃችሁ ተቋም በኮሌጁ ስም ደብደቤ መቅረብ አለባት።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከላይ በየሎቱ በተገለጸው መሰረት በባንክ የተረጋገጠ ሲፒ ኦ /CPO/ ብቻ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ውጤት በኮሌጁ ውስጥ ከተለጠፈ እና ደብዳቤ ከደረሳችሁ ቀን ጀምሮ ቅሬታ ካላችሁ በሰባት (7) ቀን ውስጥ በጽሁፍ መቅረብ አለበት።
- በጨረታ አሸናፊ የሆነ ድርጅት ያሸነፈበትን ንብረት በራሱ የትራንስፖርት ወጪ በኮሌጁ ንብረት ክፍል ግቢ ማስድረግ ይኖርበታል።
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣ በ11ኛው የስራ ቀናት 4፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥን ተዘግቶ በዛው ቀን በ4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮሌጁ ላይብረሪ ይከፈታል። የጨረታ መክፈቻ ቀኑ በስራ ቀን ያልዋለ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
- ኮሌጁ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ እንዲሁም ከቀረቡት ዝርዝሮች ውስጥ መርጦ የመግዛትና 20 ፐርሰንት ብዛት ለመጨመር ለመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ፡-
ጥቃቅን እና አነስተኛ ተደራጅታችሁ የምትወዳደሩ አቅራቢዎች በምታመርቱት ዘርፍ ወይም ለምታመርቱት ምርት ላይ 35% አድ ቫሊዩ ያለው መሆን አለበት ከዚህ ውጪ ኢምፖርት የተደረጉ ዕቃዎች ላይ ከተወዳደራችሁ እንደ መደበኛ ተጫራች ሲፒአ ማስያዝ ይጠበቅባችኋል እንዲሁም ሰነዱ ላይ የተቀመጡ መመሪያዎችን ተግባራዊ እንዲደረጉ።
አድራሻ፡
ጎፋ ካምፕ ወረዳ 5 ልዩ ስሙ የድሮ ገና ት/ቤት ከ20ቴ/ሙ/ማ/ ተቋም በአሁኑ ጎፋ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ
ስልክ ቁጥር፡-
0114-70-41-50 እና 0114-66-61-13/12
በአዲስ አበባ አስተዳደር ስራና ክህሎት ቢሮ የጎፋ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ
