በኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የመልካሣ ግብርና ምርምር ማዕከል ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል ።
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር ግ.ጨ 01/2018
በኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የመልካሣ ግብርና ምርምር ማዕከል ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል ።
- ሎት 1. አላቂ የፅህፈት መሳሪያዎችና የኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ዕቃዎች
- ሎት 2. አላቂ የፅዳት፣ የኤሌክትሪክ፣ የመስክ መገልገያ ዕቃዎች፣ የግሪን ሀውስ ኔት እና መሸፈኛ ፕስቲኮች
- ሎት 3. አነስተኛ የመስክና የእጅ መሣሪያዎች
- ሎት 4. የሰብል መከላከያ ፀረ ተባይና ፀረ አረም ኬሚካሎች
- ሎት 5. የላብራቶሪ ኬሚካሎችና የላብራቶሪ ዕቃዎች
- ሎት 6 አላቂ የወርክ ሾፕ ዕቃዎች
- ሎት 7. በቲሹ ካልቸር ላብራቶሪ ውስጥ የላብራቶሪ ዕቃ አቅርቦትና የገጠማ ሥራ
- ሎት 8. ቋሚ የቢሮ፣ የላብራቶሪና የወርክ ሾፕ ዕቃዎች
ስለዚህ ተጫራቾች ከዚህ በታች ከተራ 1 እስከ 5 የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ:
- የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ
- በዘርፉ የዘመኑን የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድና የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ ስለመሆናቸው ክሊራንስ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ።
- በኢፌዲሪ የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአቅራቢዎች ዝርዝር ላይ የተመዘገቡ ስለመሆናቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ። ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ16 (አስራ ስድስት) ተከታታይ የሥራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስክ አርብ ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት ከሰዓት በኋላ ከ7:00 ሰዓት እስከ 10:30 ሰዓት ድረስ ለጨረታ ማስከበሪያ ብር ለእያንዳንዱ ሎት 5000.00 /አምስት ሺህ ብር/ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ የተመሰከረ ቼክ CPO በማስያዝ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከአዳማ ወደ አሰላ በሚወስደው መንገድ 17 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በሚገኘው የመልካሣ ግብርና ምርምር ማዕከል ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ _ ብር 800 (ስምንት መቶ) በመግዛትና የመወዳደሪያ ዋጋቸውን በመሙላት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ መልካሳ ግብርና ምርምር ማዕከል ግ.ጨ.01/2018 ተበሎ በሕግና በደንቡ መሠረት ታሽጎ መግባት ይኖርበታል።
ጨረታው ለ16 ተከታታይ የሥራ ቀናት ክፍት ሆኖ በ16ኛው ቀን ከቀኑ 7፡00 ሰዓት ታሽጎ በእዛው እለት ከቀኑ 7፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በማዕከሉ መሰብሰቢያ አዳራሽ በግልፅ ይከፈታል።
ጨረታው የሚከፈትበት ዕለት የበዓላት ቀን ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ የጨረታው መክፈቻ ቀን በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይዘዋወራል። ዘግይተው ለሚመጡ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም።
ማዕከሉ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። አሸናፊ ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች ላሸነፉባቸው ዕቃዎች በራሳቸው ወጪ ማዕከሉ ድረስ የማቅረብ ግዴታ አለባቸው።
ናሙና መቅረብ ያለባቸውን ዕቃዎች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ተጫራቾች የማቅረብ ግዴታ አለባቸው።
ለበለጠ መረጃ :-
በስልክ ቁጥር 022 225 02 16 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
በኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የመልካሣ ግብርና ምርምር ማዕከል መልካሣ
