የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት ጤና ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት ለቢሮ የሚያስፈልጉ የተለያዩ ዕቃዎችንና አገልግሎቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ምግዛት ይፈልጋል።
ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት ጤና ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት ለቢሮ የሚያስፈልጉ የተለያዩ ዕቃዎችንና አገልግሎቶችን በግልፅ ጨረታ-
➢ በሎት-1 ጽህፈት መሣሪያ
➢ በሎት-2 የጽዳት ዕቃዎች
➢ በሎት-3 የኤሌክትሮኒከስ ዕቃዎች
➢ በሎት-4 የቢሮ ፈርኒቸር
➢ በሎት 5 ህትመት
➢ በሎት-6 የሀንፃ ቀለም
➢ በሎት-7 የስልጠና አዳራሽ እና ሪፍሬሽመንት አገልግሎት በክልሉ ክላስተር ማዕከል ከተሞች
➢ በሎት-8 የመስከ መኪና ኪራይ
➢ በሎት-9 የመኪና ባትሪ፧የተለያዩ የመኪና ሸራ፧ የመኪና ወንበር ጨርቅ እና ኬሪ ቦይ/የመኪና የኋላ መሸፈኛ/ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል::
ስስዚህ ተጫራቾች
1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል/የምትችል
2. የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል/የምትችል
3. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /ቲን/ ማቅረብ የሚችል/የምትችል
4. የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል/የምትችል
5. የእቅራቢነት ምዝገባ ምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችል/የምትችል ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ መግዣ በእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ከልላዊ መንግሥት ጤና ቢሮ ቀርበው በመከፈል ዘወትር በመንግሥት ሥራ ሰዓት በ 15 /አስራ አምስት/ የሥራ ቀናት በቢሮ ግዥ ከፍያ ን/አስ/ር ዳይሬክቶሬት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በእያንዳንዱ የዘጠና ቀን /90/ በባንክ በተረጋገጠ የባንከ ዋስትና ወይም ሲፒኦ/CPO/ ለሎት-1 ብር 50,000.00/ሃምሳ ሺህ/ ለሎት-2 ብር20,000.00 /ሃያ ሺህ/ በሎት3- ብር 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ በሎት-4 ብር100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ በሎት-5 ብር 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ ብር/ በሎት-6 ብር 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ ብር/ በሎት-7 ብር 20,000.00 /ሃያ ሺህ ብር/ በሎት-8 ብር 20,000.00 /ሃያ ሺህ ብር/ በሎት-9 ብር 30,000.00 /ሰላሳ ሺህ ብር/ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ከልላዊ መንግሥት ጤና ቢሮ ሥም በማሠራት ከጨረታ ሰነድ ጋር በማዘጋጀት አያይዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ ሰነዱ ላይ በመፃፍ በሰም/ሙጫ/ በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 /አስራ አምስት/ በመንግሥት ሥራ ቀናት በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ከልላዊ መንግሥት ጤና ቢሮ ግዥ ከፍያ ን/አስ/ር ዳይሬክቶሬት በመቅረብ ለዚህ ሥራ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ በማስገባት መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የጨረታ ሰነድ አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ ለየብቻ በሦስት ፖስታዎች በሰም/ሙጫ/ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት ሰነድ ላይ ስማቸውን አድራሻቸውን ማህተም እና ፊርማቸውን በማሟላት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።የጨረታው ሳጥን በ16 ኛው ቀን በ8፡00 ታሽጎ በዚያው ዕለት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- የጨረታው መከፈቻ እና መዝጊያ ቀን ዝግ የሚሆን ከሆነ በሚቀጥለው ሥራ ቀን ከላይበተገለፀው ሰዓት ይሆናል፡፡
- የተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ያለመገኘት የጨረታ መከፈቻውን አያስተጓጉልም፡፡
ማሳሰቢያ፦ ቢሮ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር:- +251-4-73-45-08-79 በመደወል መረጃ ማግኘት ይቻላል።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት ጤና ቢሮ
