በአብክመ የከሚሴ ከተማ እና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት በጽ/ቤቱ ሥር ለሚገኙት ለሁሉም ሂደቶች የቢሮ ቋሚ እና አላቂ እቃዎች ግዥ ለመፈፀም በዘርፉ የንግድ ፈቃድ ያላቸውን ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የቢሮ አላቂ እና ቋሚ እቃዎች ግዥ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በአብክመ የከሚሴ ከተማ እና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት በጽ/ቤቱ ሥር ለሚገኙት ለሁሉም ሂደቶች የቢሮ ቋሚ እና አላቂ እቃዎች ግዥ ለመፈፀም በዘርፉ የንግድ ፈቃድ ያላቸውን ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ ፍቃደኛ የሆኑ-
- የቢሮ ቋሚ እና አላቂ እቃዎች ግዥ ህጋዊ ፈቃድ ኖሯቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉና ያሳደሱ፤ ለሥራው የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው፤ የቫት ተመዝጋቢ የሆነና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው።
- የጨረታው ሰነድ ከከሚሴ ከተማ እና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 33 በግዢ/ፋይ/ንብ/አስ/ዋና የሥራ ሂደት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ 21 /ለሃያ አንድ ተከታታይ ቀናት ከላይ የተዘረዘሩትን መረጃዎች ዋናና ኮፒ በመያዝ ዘወትር በሥራ ቀንና ሰዓት ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ የኢትዮ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋና እና ኮፒ በማድረግ በታሸገ ኤንቨሎፖች በአብክመ የከሚሴ ከተማ እና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት በግዢ/ፋይ/ንብ/አስ/ዋና የሥራ ሂደት ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሃያ ሁለተኛው/22/ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 4፡00 ሰዓት ድረስ የቢሮ ቋሚ እና አላቂ እቃዎች ግዥ ጨረታ ሰነድ ባለው ጊዜ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው 18/02/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 የቢሮ ቋሚ እና አላቂ እቃዎች ግዥ ላይ በግዢ/ፋይ/ንብ/አስ/ዋና የሥራ ሂደት ቢሮ ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ተጫራቾች ተመላሽ የሚደረግ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ገንዘብ የቢሮ ቋሚ እና አላቂ እቃዎች ግዥ ከጠቅላላው ድምር 2% በጥሬ ገንዘብ ወይንም በባንክ ትእዛዝ /CPO/ ማስያዝ አለባቸው።
- ለቢሮ ቋሚ እና አላቂ እቃዎች ግዥ የጨረታ አሸናፊ የሆነው ድርጅት ውል በሚዋዋልበት ጊዜ የውለታ ማስከበሪያ ከአጠቃላይ ድምር ዋጋ 10% ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ፤ በከሚሴ ከተማ እና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት በግንባር በመቅረተ ወይንም በስልክ ቁጥር 033 554 0255 ደውለው መረዳት ይችላሉ፡፡
በአብክመ የከሚሴ ከተማ አስተዳደር ከተማ እና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት
