በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የአለልቱ ወረዳ ፍርድ ቤት በ2018 የበጀት ዓመት የተለያዩ ቋሚና አላቂ ቃዎች፣ የጽዳት እቃዎች፣ የኤሌክትሮኒከስ እቃዎች፣ የተለያዩ የመኪና ጎማዎች፣ ህትመት እና የጽህፈት መሳሪያዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የአለልቱ ወረዳ ፍርድ ቤት በ2018 የበጀት ዓመት የተለያዩ ቋሚና አላቂ ቃዎች፣ የጽዳት እቃዎች፣ የኤሌክትሮኒከስ እቃዎች፣ የተለያዩ የመኪና ጎማዎች፣ ህትመት እና የጽህፈት መሳሪያዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ የሚከተለውን የጨረታ መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾችን እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፡፡
1. እቃዎቹን በጥራት ለማቅረብ የሚያስችል ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የ2017 ዓ.ም ግብር የከፈሉ፣ ንግድ ፈቃዳቸውን ያደሱ፣ ለዚህም ከሊራንስ ከሚመለከተው አካል ማቅረብ የሚችሉ ፡፡
2. ለጨረታ ማስከበሪያ /ቢድ ቦንድ/ብር 5000 /አምስት ሺህ ብር / ከታወቀ ባንከ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ወይም በጥሬ ገንዘብ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችሉ፡፡
3. በግልም ሆነ በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
4. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በo ተከታታይ የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 200/ ሁለት መቶ ብር / በመከፈል አለልቱ ወረዳ ፍርድ ቤት ቀርበው መውሰድ ይችላሉ ፡፡
5. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋና እና ኮፒ በታሸገ ኤንቨሎኘ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
6. የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 የሥራ ቀን ቆይቶ በ18/2/2018 ዓ.ም ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው እለት ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ እለቱ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል፡፡
7. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው::
ማሳሰቢያ፡- ተጫራቾች እቃዎቹን ጥራታቸውን የጠበቁ ሆነው በተባለው ጊዜና ቦታ ውስጥ አጠናቀው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
በስልክ ቁጥር፡- 0116310127/ 0924783034 /0913947513/0941070332 አለልቱ ወረዳ ፍርድ ቤት ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
አድራሻ፡- በደሴ/ደ/ብርሃን መንገድ በዋናው አስፓልት ከአ/አ 55 ኪ.ሜ ከዋነው አስፓልት በስተግራ 100 ሜትር ገባ ብሎ ነው::
በኦሮሚያ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን የአለልቱ ወረዳ ፍርድ ቤት
